Get Mystery Box with random crypto!

በጥናታዊ ጽሁፍ Meta Analysis ምንድን ነው? Meta-analysis ሌሎች አጥኚዎች መረጃ ሰ | Research-ሪሰርች(ጁፒተር-Jupiter)

በጥናታዊ ጽሁፍ Meta Analysis ምንድን ነው?
Meta-analysis ሌሎች አጥኚዎች መረጃ ሰብስበው ያገኙትን የጥናት ውጤት እርስ በእርስ በማነጻጸር ብቻ በአማካኝ የመጣውን ውጤት መውሰድ የሚቻልበት የጥናት ዘዴ ነው፡፡ Meta-analysis የሚለው ቃል ሲተረጎም analysis of analyses ማለት ነው::
ሁላችሁም እንደምታውቁት ጥናታዊ ስራዎችን ለማከናወን በዋናነት ከ Primary source (መጠይቅ በመሰብሰብ (Questionnaire)፤ ቃለ መጠይቅ (Interview) በማድረግ እና የጋራ ውይይት በማካሄድ (Focus Group Discussion) ወይም ከ Secondary source ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በጽሁፍ ያለ ጥሬ መረጃ በማሰባበስ የሚፈለገው ውጤት ላይ መድረስ የተለመደ አሰራር ነው፡፡ Meta-analysis የ Secondary source መረጃ ዘዴ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
በተቃራኒው ሌሎች አጥኚዎች ከላይ የተዘረዘሩትን መንገዶች ተጠቅመው መረጃ በማሰባሰብ ያገኙትን የጥናት ውጤት (በተመሳሳይ ርዕስ ላይ የተደረገ ጥናት መሆን አለበት) የአንዳቸውን ግኝት ከሌላኛው ግኝት ጋር እርስ በእርስ በማነጻጸር ብቻ በአማካኝ የመጣውን ውጤት መውሰድ የሚቻልበት የጥናት ዘዴ ነው፡፡
በዓለም ላይ የመጀመሪያው የተለያዩ ጥናቶችን በማነጻጸር የተሰራው ጥናት 1904 ነበር (115 ዓመታት አልፎታል)፤ Karl Pearson የተባለ ስታትሽያን በታይፎይድ ላይ የተሰሩ ጥናታዊ ስራዎችን በማሰባሰብ እና ውጤታቸውን በማነጻጸር የማጥናት አካሄድን ጀምሮ ነበር፡፡ ነገር ግን Meta-analysis የሚለውን ስያሜ በ1976 እንዲያገኝ ያደረገው እና ለጥናቱ ዘዴ ህጎችን በማውጣት በፈጣሪነት የሚጠቀሰው Gene V. Glass የተባለው ስታትሽያን ነው፡፡
የ Meta-analysis ጠንካራ ጎን
ለእውነት የተጠጋ ውጤት የማግኘት እድሉ ሰፊ ነው፡፡
ብዙ ዳታ የመዳሰስ እድል ይፈጥራል (#ለምሳሌ:- የ300 ሰው መረጃ የወሰዱ 10 ጥናቶችን በ Meta-analysis ዘዴ የሚመለከት አጥኚ በቀላሉ የ3000 ሰዎችን መረጃ እንደሰበሰበ ይቆጠራል)፡፡
ናሙና ከመውሰድ የሚመጣን ስህተት (Sampling error) የመቀነስ አቅም አለው፡፡
Meta-analysis ለመጠቀም በመጀመሪያ ለማረጋገጥ በፈለጉት ሃሳብ ዙሪያ የተሰሩ ተቀራራቢ ጥናቶችን በደንብ ማንበብ፤ ጥናቶቹን በርዕሳቸው፤ የተጠቀሙትን Variables እና የተሰሩበት ወቅት መሰረት በማድረግ ማሰባሰብ እና ወደ ማነጻጸሩ መግባት ይጠበቃል፡፡
#ለምሳሌ:- በምስራቅ አፍሪካ ስላለ የስራ አጥነት ምክንያት ለማጥናት የፈለገ አንድ አጥኚ በሁሉም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መዞር ሳይጠበቅት በምስራቅ አፍሪካ ዙሪያ ባሉ ሀገራት #ለምሳሌ:- ከ2010 እስከ 2019 የተጠኑ የስራ አጥነት ምክንያት የሚሉ የጥናት ስራዎችን ማሰባሰብ ይጀምራል፡ #ለምሳሌ:- በኢትዮጲያ፤ በኤርትራ፤ በጅቡቲ፤ በኬኒያ እና በኡጋንዳ የተሰሩ ሁለት ሁለት ጥናት ቢያሰባስብ በድምሩ አስር የጥናት ግኝት ያገኛል ማለት ነው፡፡
ከዚህ በመነሳት በአብዛኛው ሃገራት የተገኘው ውጤት ሲታይ በአማካኝ አብዛኛዎቹ ያገኙት ውጤት ግብርና ላይ ጥገኛ የሆነ ኢኮኖሚ መኖር ተጨማሪ የስራ እድል ለመፈጠር አለመቻሉን እና ለከፍተኛ ስራ አጥነት ምክንያት መሆኑን ካመላከቱ Meta-analysis የሚጠቀመው አጥኚ ከዚህ አማካኝ ግኝት በመነሳት “በምስራቅ አፍሪካ ላለው ከፍተኛ ስራ አጥነት በቀጠናው ባሉ ሀገራት ግብርና ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት በመሆኑ ነው” ብሎ ያስቀምጣል እንደማለት ነው፡፡