Get Mystery Box with random crypto!

ዝምታ ለምን ዝም እንላለን ? ዝምታ ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል? መልሱን ቀጥሎ ታገኙታላችሁ፡፡ | ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

ዝምታ

ለምን ዝም እንላለን ? ዝምታ ይጠቅማል ወይስ ይጎዳል? መልሱን ቀጥሎ ታገኙታላችሁ፡፡

ዝምታ ሁለት አይነት መልኮች አሉት፡፡

አንዱ ስህተትን በመፍራት፣ ላለመሞከር፣ በሰዎች አይን ውስጥ ላለመግባት፣ ድፍረት የማጣት፣ የፍርሃት ምልክት ነው፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ሌሎችን ማድመጥ ብቻ እንጂ የራሳቸውን ማጋራት፣ መጠየቅ፣ በቂ ምላሽ መስጠት አይችሉበትም፡፡ በዚህም ምክንያት ለራሳቸው ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ የሰዎች ሁሉ ሃሳብ ማጠራቀመሚያ ቋት ይሆናሉ፡፡ የራሳቸውን ሃሳብ በድፍረት መግለጽ አይችሉበትም፡፡ የሚረዳቸው ሰው እንደሌለም ይሰማቸዋል፡፡

ሁለተኛው ዝምታ ደግሞ ባለመቻል ሳይሆን ፈልገን የምናደርገው ነው፡፡ ለማዳመጥ፣ ለመረዳት፣ ለማሰብ፣ ለራሳችን ግዜ ለመስጠት፣ ተራችንን ለመጠበቅ፣ ወዘተ. ስንፈለግ ዝምታን እንመርጣለን፡፡ አንዳንዴም ሁኔታው ልክ እንዳልሆነ እያወቅን ጭቅጭቁን ለማስወድ ወይም ጉዳዩ በኛ ብቻ ሊፈታ እንደማይችል ስለተረዳንና ለማሳለፍ ስንል ዝምታን እንመርጣለን፡፡

ራሳችሁን የትኛውን ዝምታ ስትጠቀሙ አስተውላችሁ ታውቀላችሁ? የመጀመሪያውን ወይንስ ሁለተኛውን? ጻፉልን፡፡

ተመስገን አብይ Psychologist
@psychoet