Get Mystery Box with random crypto!

ከእስራት ልትፈታ አይገባምን ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓ | THE PRESENCE OF GOD

ከእስራት ልትፈታ አይገባምን

ይህችም የአብርሃም ልጅ ሆና ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ሰይጣን ያሰራት በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? በዚያም የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጒበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር። ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ “አንቺ ሴት፤ ከሕመምሽ ነጻ ወጥ ተሻል” አላት፤ እጁንም በላይዋ ጫነ፤ እርሷም ወዲያው ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።
ነገር ግን የምኵራቡ መሪዎ የእነርሱ ልጃቸው ወይም በሬው በጒድጓድ ቢገባበት  ወይም ውሃ ቢጠማው በሰንበት ቀን ፈጥኖ ያወጣል፥ ከማደሪያው ፈትቶ ውሃ ሊያጠጣ ይወስደል። ግን ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ ተቈጥተው ሕዝቡን፣ “ሥራ ሊሠራባቸው የሚገባ ስድስት ቀኖች አሉ፤ ስለዚህ በእነዚያ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይደለም” አሉአቸው። ኢየሱስ በየትኛውም ቀን ወይም ሰዓት ከእስራት ይፈታል። አሜን

  — ሉቃስ 13፥10-17
@myblogshub