Get Mystery Box with random crypto!

# ለሙዋርታኛ ብቻ!!! ኑሮዬ ግራ #ለሙዋርተኞች አልተገኝሁም ለአጋንንቶች። ተኝቷል ሲባል ብድ | THE PRESENCE OF GOD

# ለሙዋርታኛ ብቻ!!!

ኑሮዬ ግራ #ለሙዋርተኞች
አልተገኝሁም ለአጋንንቶች።

ተኝቷል ሲባል ብድግ እላለሁ፣
ያለቅሳል ሲባል ስቄ እወጣለሁ።
በጌቶች ጌታ እርፍ እላለሁ።

ጠላቴ ዙርያውን ሲዘጋው ጠላቴ፣
ላይዘጋ ከፈተው አባቴ።

ለዚህ ነው ቀና ቀና ማለቴ፣
ለዚህ ነው ሀሌሉያ ማለቴ።

የእግዚአብሔር ወንጌል እንዳይሰበክ፣
በሥጋ ጥበብ ምድሪቱን ያሰርክ።
በክርስቶስ ስም ስራህ ይፈርሳል፣
በዓለም ሁሉ ወንጌል ይነግሳል፣
ሰባሪው እግዚያብሄር ይበትንሀል።

አትሰብክም የምትል ሟርተኛ፣
አትዘምርም የምትል ሟርተኛ፣
አትፀልይም የምትል ሟርተኛ፣
በምድሬ ላይ ወንጌል ነው ተረኛ፣
በዓለም ዙሪያ ወንጌል ነው ተረኛ።

ተራራውን አደላደለው፣
ማዕበሉን ፀጥ በል አለው።

(የደረጀ ሙላቱ ዝማሬ)

ሟዋርትና አስማት በእስራኤል ላይ አይሰራም። ሃሌሉያያያ

@myblogshub