Get Mystery Box with random crypto!

https://vm.tiktok.com/ZMNnTaUEB እረኛዬ /ክርስቶስ/ ብዙ ጊዜ እረኛዬ የሚለው | ታታ አፍሮ -Tata Afro

https://vm.tiktok.com/ZMNnTaUEB

እረኛዬ /ክርስቶስ/

ብዙ ጊዜ እረኛዬ የሚለውን ቃል ለሰው ለመስጠት ቃሉ በጣም ስለሚገዝፍብኝ ልክ መስሎ አልታይ ይለኛል። በቅዱስ መጽሐፍም ላይ እግዚአብሔር መልካም እረኛ እንደሆነ በመጠቀሱ ጭምር ቃሉን ስሰማው ወደ መንፈሳዊነት ያዘነብልብኝ ነበር። የፊልሙንም እርዕስ ስለምን ሌላ አላደረጉትም እያልኩ እብሰለሰል ነበር። ይኼን አይነት አመለካከት ያላቸው ሌሎች ሰዎችንም አስተውያለሁ። ለዚህም ነው ይኼንን ጽሁፍ ለመጻፍ የተነሳሁት።

አንድ ቀን እኔ የወንድሜ ጠባቂ ከሆንኩ የእርሱ እረኛ ብባል ምን ነውር አለው ስል እራሴን ጠየኩ...? ወንድሜስ ስለኔ በመጨነቅ እኔን የሚጠብቀኝ ከሆነ እርሱ እረኛዬ /ጠባቂዬ/ ነው ብል ምን ነውር አለው...? ስል ከራሴ ጋ ተማከርኩ። መጠባበቅ የሚመጣው መጀመሪያ ፍቅር ስለኖረ ነው። እግዚአብሔር በራሱ ፍቅር ስለሆነ እኛን ፈጠረን። ፈጥሮ ዝም አላለንም። ምክኒያቱም ጽኑ ፍቅር ስላለበት ይጠብቀን ጀመር። መልካም እረኛም ሆነን። ከፍጥረታቱ ሁሉ እኛ አጥፍተን እኛው ብንጠፋ እኛን ፍለጋ ወጣ። አጥፍተዋል ይጥፉ ሳይል በደላችንን እርሱ ተሸክሞ የኛን ግርፋት ተገርፎ እኛን በፍቅር ወደበረቱ መለሰን። እኛንም በዚህ ደረጃ እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ አዘዘን። አንዳችን የአንዳችን ጠባቂ /እረኛ/ ብንሆን የእርሱ ፍቃድ ነውና ስህተት የለውም። እኛ ዓለምን ሁሉ እንደ ክርስቶስ የመጠበቅ አቅሙ የለንም። ቤተሰባችንን፣ አካባቢያችንን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችንን ግን የመጠበቅ አቅሙ አለን። ለነርሱ እረኛ መሆን እንችላለን።

በጥቅሉ እረኛ ማለት ከክፉ ነገር የሚጠብቅ ማለት ነው። ስለዚህ ቃሉን ወስጄ ለእናቴ ብሰጣት ነውር አይሆንም። እናቴ እረኛዬ ነች። እናቴ ጠባቂዬ ነች።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/