Get Mystery Box with random crypto!

ግጥምና ወግ Eyob Z Mariam

የቴሌግራም ቻናል አርማ poeteyobzmariam — ግጥምና ወግ Eyob Z Mariam
የቴሌግራም ቻናል አርማ poeteyobzmariam — ግጥምና ወግ Eyob Z Mariam
የሰርጥ አድራሻ: @poeteyobzmariam
ምድቦች: ስነ-ጽሁፍ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.36K
የሰርጥ መግለጫ

...Poet, writer & film maker🎬🎥
@Eyob567

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-09 13:53:04
ለ ሬድዮ አፍቃሪዎች! ዛሬ በ fm Addis 97.1 ከምሽት 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት በቀጥታ ስርጭት በእንግድነት ከ አድማጮች ጋር ቆይታ እንደርጋለን

Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
871 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 09:29:52
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
3.0K views06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 12:30:10
ከባላገሩ ቲቪ “ለምሳሌ” ፕርግራም ጋ ቆንጆ ቆይታ አድረገናል ነገ (ማክሰኞ) ምሽት 2:30 ላይ ጠብቁን

Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
902 views09:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 21:03:57
Join

@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
3.1K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 10:04:30
ሌላ አዲስ አመት ተጨመረልኝ

እግዚአብሔር ይመስገን
1.1K viewsedited  07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 14:19:48
Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
4.1K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 15:32:38 ወደ ፌስቡኬ ስገባ “አለማቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት” የሚል ነገር አየሁ! Wow ከሳምንቶች ሁሉ የተባረከ ሳምንት አልሁ በልቤ ወዲያው ፍቅረኛዬ ጋ ደወልሁና…

‘እንኳን አደረሰሽ የኔ ፍቅር’ (በመሰረቱ እንኳን አደረሰኝ ነበር ማለት የነበረብኝ )

“ለምኑ?”

‘አለም አቀፍ የጡት ማጥባት ሳምንት እኮ ነው ዛሬ’

“ሌላ ነገር ሲከበር… ‘የእንትን ቀን ‘ አነበር እንዴ ሚባለው ምነው ለጡት ሲሆን ሳምንት አደረጉት?”

‘እንዴ ሳምንት አይደለም አመትስ ቢሆን ለጡት ሲያንስበት እኮ ነው!… በይ አሁን ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ!’

“ማለት ምን ልትሆን?”

‘ልጠባ ነዋ’

“ኧረ በናትህ ዝም በል ሰውዬ baby እያልኩ ስጠራህ የእውነት ህፃን የሆንክ መሰለህ እንዴ?”

‘እኔስ እናት እያልኩ የምጠራሽ ዝም ብዬ ነው እንዴ? እንድታጠቢኝ መስሎኝ!’

ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ተስማማን! ቤት ሄድኩና ይሄን የ አሜሪካ ላም የመሰለ ጡት እያቀያየርሁ ይዤ መመጥመጥ ጀመርሁ! ወተት የለውም እንጂ አንባሻ እየገመጥሁ ብጠባው ደስ ባለኝ ነበር! … እስክጠግብ ከመጠመጥሁ በኋላ ከ አልጋ ልወርድ ስል ፍቅረኛዬ እጄን ያዝ አደረገችኝና ….

“Babye “

“ወዬ…”

“አለማቀፍ የ*ላ ማጥባት ቀን መቼ ነው?

(እዮብ ዘ ማርያም)

@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
1.1K viewsedited  12:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 22:24:26 ዛሬ በጣም የተደሰትሁበትና በጣም ያዘንኩበት ቀን ነበር

ቤት ስገባ ባለቤቴ መፅሀፍ እያነበበች ደረስሁ! ደነገጥሁ! ከተጋባን ጀምሮ ስታነብ አይቼ አላውቅም! ንባብ ከመጥላቷ የተነሳ ጠዋት ጠዋት ፀሎት ስታደርስ ራሱ ውዳሴ ማርያም በaudio ከፍታ ነው! ባለቤቴ ማንበብ ጀመረችልኝ ብዬ ፈነደቅሁ! … በደስታ ልስማት “babye የኔ ቆንጆ” ብዬ ስጠጋት ደስታዬ ወዲያው ወደ መሪር ሀዘን ተቀየረ! ለቅሶ ቤት ስሄድ የማይመጣልኝ እንባ ወዲያው አይኔ ላይ ግጥም ሲል ታወቀኝ! የመፅሀፉን ርዕስ አየሁት…

“የወንድ ብልትን የሚያስረዝሙ ቤት ውስጥ በቀላሉ የሚዘጋጁ ምግቦች“ ይላል

(እዮብ ዘ ማርያም)

@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
1.1K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 10:32:30 በቤት ኪራይ መማረሬን ያወቀ አንድ ጴንጤ ጓደኛዬ ቤቴ መጣና (የተከራየሁት ቤት ማለቴ ነው ) ቸርች ካልሄድን ብሎ ይጨቀጭቀኝ ጀመር!…የተኛሁበት አልጋ ጋ ቆሞ ቁልቁል እያየኝ…

“ሰው ስንት ቦታ ደርሷል አንተ ዛሬም እዚህ አልጋ ላይ ተጣብቀሀል? ስምህ እኮ እዮብ ሳይሆን መፃጉ ነበር መሆን የነበረበት!”…የለበስሁትን ብርድ ልብስ ከላዬ ላይ ገፈፈውና…

“በጌታ በየሱስ ስም የመጋደም መንፈስ እንደዚህ ብርድ ልብስ ከላይህ ላይ ይገፈፍ” ብሎ ጮኸ!

‘ኧረ በናትህ ሰውዬ አከራዬ የድምፅ ፎቢያ አለባቸው እንዳታስባርረኝ!…ድምፅ ከመጥላታቸው የተነሳ ከሚስታቸው ጋ ሴክስ ሲያደርጉ እራሱ አፏን በፕላስተር አሽገው ነው’!…ምን አልባት ከፕላስተሩ አምልጦ ሚወጣ እንኳን ድምፅ ካለ ለጥንቃቄ ብለው ጆሯቸው ውስጥ ጥጥ ይወትፉሉ!’

“ምን? ይሄማ የሰይጣን መንፈስ ነው ሄጄ ልፀልይላቸው” ብሎ ሊገሰግስ ሲል እግሩን ይዤ አስቆምኩት!….ድንገት ዞር ሲል ኮመዲኖ ላይ የተቀመጠ አምስት ሊትር ዘይት አየና….

“ኦው…ዘይት አለህ እንዴ? በቃ ላንተ ልፀልይልህ የሳቸው ሌላ ግዜ ይደርሳል” ብሎ አፈፍ አድርጎ አነሳውና ወደኔ እያየ “ደግሞ Omar ነው ባክህ?”

ግንባሬን ቋጠር አድርጌ…

‘ማለት የዘይቱ አይነት ፀሎቱ ላይ የሚያመጣው ለውጥ አለ ማለት ነው?’

“እሱስ የለም! በመኪና ዘይትም ቢፀለይ ዋናው እምነት ነው!” …ብሎ ክደኑን ሊከፍተው ሲል መንጭቄ አስለቀኩትና….

‘ቀልደኛ ነህ አንተ ባክህ! በፀሎት የገዛሁትን ዘይት ፀሎት በሚል ተልካሻ ምክንያት ልታባክን ስትነሳ ትንሽ አይከነክንህም? ከቻልክ ዘይቱ ላይ ፀልይልኝና 5 የነበረውን 10 ሊትር አድርግልኝ’… ብየ አፈጠጥሁበት!

“ይህን እንዳደርግ እንኳ ጌታ አልነገረኝም! ላጤ ስለሆነ ብዙ የዘይት ፍጆታ የለበትም ያለው ይበቃዋል ነው ያለኝ”!

ድክም አለኝና….

‘እሺ አሁን ምን ፈልገህ ነው የመጣኸው?’

“ቸርች እንሄዳለን ዛሬ”!

‘ለምን?’

“እዚህ ከተማ ውስጥ የቤት ችግር እንዳንተ ያማረረው ሰው አለ? ሌላው ቀርቶ ቤት የሚመታ ግጥም ስታይ ራሱ እኮ ልብህ ሰፍ ይላል!”

‘እና ምን ይሁን?’

“የቤት ችግርህ ዛሬ ታሪክ ሆኖ ይቀራል ! አሜን!”

‘የቤት ስጦታ ሰጥተህ surprise ልታደርገኝ ነው እንዴ ?እኔ እኮ አለምንህም’

“እሱን እዛው church ስንሄድ ታየዋለህ!…አንኳኩ ይከፈትላችኋል ሲባል አልሰማህም?”

‘እኮ ቤት ሳይኖረኝ ምኑን ላንኳኳ?’

“ካሁን በኋላ ማንኳኳት አያስፈልግህም!…ዛሬ የቤትህን ቁልፍ የዘህ መጥተህ እራስህ ነህ ከፍተህ ምትገባው! ተነስ!!

አለኝና ቸርች ወሰደኝ….

ቸርች ውስጥ እየተዘመረ ነው! አይናቸውን ጨፍነው አንድ እጃቸውን ደረታቸው ላይ ለጥፈው..አንድ እጃቸውን ደግሞ አየር ላይ ዘርግተው እንደ ባንዲራ እያወለበለቡ በሚዘምሩ ሴቶች ውበት ልቤ ተማረከ! አቤት ታፋቸው ደግሞ ቅላቱ! መዝሙሩን ትቼ በአይኔ ማመንዘር ጀመርሁ! … ድንገት መዝሙሩ ቆመና ሱፉን ግጥም አድርጎ የለበሰ….የፀጉሩ የጎን ክፍል ላይ ጭረት አድርጎ በቄንጥ የተቆረጠ ፍሪክ መድረክ ላይ ወጣና ማውራት ጀመረ…

“ቦቦቦቦቦታታሴካ …..ሀሟሏሯሷሿሌማሴኔ…ባርሳማድሪድ ጋላሴሬ….”

ቋንቋው የአልጋ ወይም የበር ጠርዝ የእግሬን ትንሿን ጣት ሲነድለው ከማወራው ቋንቋ ጋ ተማሰለብኝ! ወዲያው…

“የቤት ችግር ያለባችሁ ቅዱሳን ወደ ፊት ኑ “ማለት ጀመረ! ይህን ቃል ከመናገሩ ጓደኛዬ “እስካሁን እዚሁ ነህ ? “ ብሎ ገፈተረኝና ከኋላ የነበርሁት ሰውዬ ፊት ለፊት ተገኘሁ! ፀሎቱ ተጀመረ…

“የቤት ችግር ያለባችሁ ሰዎች በየሱስም ዛሬ አግኙ”

አሜንንንንን

“የቤት ችግር ያለባችሁ ሰዎች ዛሬ ውረሱ”

አሜንንንንንን

“ተሰርቶ ያለቀ ባለሁለት መኝታ ኮንድሚኒየም ውስጥ ግቡ”

‘ኦ ይሄ ሰውዬ ከ አዳነች አቤቤ ጋ ሊያያይዘን ነው እንዴ’ ስል በልቤ አሰብሁ!

ቀጠለ…

“ከአሁኗ ደቂቃ ጀምሮ ተአምራት ይሆናል! የreal estate እና የ apartment ቁልፍ ትረከባላችሁ! በኪራይም የምትኖሩ የተከራያችሁትን ቤት ትወርሳላችሁ”

አሜንንንንንንንን!!!! ሰማይ ምድሩ ተናወጠ!

ማታ! ወንበር ላይ ቁጭ ብዬ ከጓደኛዬ ጋ እያወራሁ ነው!

“በቃ እመን! ካሁን በኋላ ስለ ሌላ ችግርህ አስብ እንጂ የቤት ጉዳይ ያንተ ችግር አይደለም!”… እያለኝ እያለ ድንገት በሬ ተንኳኳ…’ቆይ አንዴ መልሼ ደውልልሀለሁ’ብዬ ስልኩን ዘጋሁና በሩን ከፈትሁት! አከራዬ ናቸው! ወዲያው ፓስተሩ …“በኪራይም የምትኖሩ የተከራችትን ቤት ትወርሳላችሁ” ያለው ቃል ትዝ አለኝ! …’እንዴት ያለ ድንቅ ፓስተር ነው?’ ስል በልቤ አደነቅሁት!

አከራዬ የሸሚዜን ኮሌታ እያስተከከሉ….
“ልጅ እዮብ እንዴት ነህ?”

‘ደህና ነኝ ጋሼ ደህና ነኝ”… ቶሎ ወደ ገደለው እስኪገቡ ቸኮልሁ!

“ያው መቼም እንደ ልጄ እንደምወድህ ታውቃለህ….”

አሁን እርግጠኛ ሆንኩ! “እንደ ልጄ ሰለምወድህ አሁን ያለህበትን ክፍል ጨምሮ ከጎኑም ያለውን ቤት አብሬ በስጦታ መልክ አበርክቼልሀለሁ” ሊሉኝ እንደሆነ በልቤ ደመደምሁ! … ‘አመሰግናለሁ ጋሼ አባቴ ኖት’ ብዬ ልጠመጠምባቸው ስል “ቆይ ቆይ ተረጋጋ እንጂ” ብለው በእጃቸው መለሱኝ…

‘ምነው ጋሼ?’

“እንዴ አስጨርሰኝ እንጂ!…እኔ ልል የፈለግሁት ምንም እንደ ልጄ ብወድህም የኑሮ ውድነት አናት በመውጣቱ የቤት ኪራይ 500 ብር ጨምሬብሀለሁ ልል ነው”!

የሰማሁትን ማመን አቃተኝ! ምን አልባት ከጆሮዬ ከሆነ ብዬ ኮረኮርኩትና ….’ምን አሉኝ ?’ አልኳቸው! እራሱኑ ቃል በደንብ ረገጥ አድርገው ደገሙልኝ!

ንዴቴን መቆጣጠር ተሳነኝ! ወዲያው ጓደኛዬ ጋ ደወልሁና የሆነውን ነገርሁት!! ጓደኛዬ በሚያስተሳዝን ቅላፄ ድምፁን ዝቅ አድርጎ….

“አይዞህ በቃ ክርስቲያን ቤቱ በሰማይ ነው”

ብሎ ስልኩን ዘጋው

“እዮብ ዘ ማርያም”

Join
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
@poeteyobzmariam
1.3K viewsedited  07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 23:09:27
እግዚአብሔር ይመስገን!! በላይ ተለቋል!!

Join
@Poeteyobzmariam
@Poeteyobzmariam
@Poeteyobzmariam
1.2K views20:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ