ጠብቀኝ በህልምህ ጠብቀኝ በህልምህ ፤ እመጣለሁ ማታ አልቀርም አትስጋ ፤ አለሁ ለሰላምታ ያን የምሽት ጥቁረት ፤ ያን የሌት ፀጥታ እንደ መብረቅ ጮኬ ፤ ጨለማን ልረታ እመጣለሁ ማታ ፤ በህልምህ አልቀርም አንተን እረስቼ ፤ ሌላ ቤት አላድርም ኧረ አይሆንም! ቀኑም ሲጨላልም…… አይኖችህ ተከድነው ፤ በናፍቆት ሊያልሙ በምኞት ጭንቅ አዝለው ፤ እያግደመደሙ ከጠበቁኝ እማ ፤ መች እኔ እቀራለሁ አንድ ነገር ብቻ ፤ በእጅግ እፈራለሁ የጠበከው ጊዜ ፤ የህልም አለም ወቅትህ ከደረሰ ወዲያ ፤ አይኔን እንደናፈቀህ ሃሳብና ናፍቆት ፤ እንቅልፍ እንዳይነሱህ @yegetemkalat @poem_merry 637 viewsMerry G, 11:18