Get Mystery Box with random crypto!

የሰኔ ፊት አይተው አልቃሻ መሆኗን ሲነግሩኝ ቆይተው፣ መሬት ጠቦናል ሲሉ፤ አዳም፥ ዘመነኛው ፥ | እግር ኳስ Meme™

የሰኔ ፊት አይተው
አልቃሻ መሆኗን ሲነግሩኝ ቆይተው፣

መሬት ጠቦናል ሲሉ፤
አዳም፥ ዘመነኛው ፥
ተወደደ መሰል የምድር ጉድጓዱ፣
ሲሻሻጥ ሲነጠቅ ሲሰዋ መሬቱ ፣
እህ እጂ
ሬሳው በሙሉ፥
ሰይጣኑም በሙሉ
ብላቴን በሙሉ ፥
የሰኔ ጎርፍ ነው የሚቀብረው አሉ፣

ምናለ ወይ ታህሳስ፣
ጥርን ለምዶ ድግስ፣
ከቶ ማን ያፅናና ሰኔ ሲደርስ ሲደርስ፣
ሁሉ ዳሱን ጥሎ ከሰኔ ጋ ሲያለቅስ፣

አንቺ ሰኔ ሰኔ አወይ ሰኔ፣
መስከረም እራቀሽ
ይልቁን ለማልቀስ ቀረበሽ ወገኔ፣

ወዴት አቤት ይባል ሰማይ ሲከፍው፣
ቀን እህ ብሎ እህ እህ ብሎ በሌት ካላካፍው፣

መገን ሰኔ አይክፍሽ ፣
ለአራት አመት ስሞሽ
ማነው የደገመው ያንን የጥቁር ሻሽ፣
ይልቁን
ለውሽማሽ ፀሀይ እንዲህ በያት ባክሽ፣

አዬ እመ ብርሃን ምነው ሰው ምትፈሪ ፣
ምን ያሃል እንደከፍ አይተሽ አይድል ሰውነትን ይዘሽ ከአለም ስትኖሪ፣

አደለም ለህፃን
ለውሻ እንኳ ለጥሙ ስትጠልቂ ከውሃው፣
ለኛስ ሲሆን
አስቻለሽስ ምነው፣
ወይስ
ያንቺ እንባ ነው ወይ
ሰኔ ላይ ሚዘንበው፣

እንደው ግራ ገባን ግራ ነው ምሱ፣
ከቶ ማን ያባብል ከቶ ማን ያፅናና
ሰውና ተፈጥሮ እኩል እያለቀሱ፣

መስከረም እስክትመጪ
በእውነት ፀንተሽ ከላይ፣
የዘመናት ድንኳን ተነስተን እስክናይ
በሀምሌ መስኮት ብቅ ጥልቅ በይ፤
መገን የሰኔ.. የነሀሴ ጠሀይ ፣
ሚሽረው እስኪሽር በአንድላይ፣
_
ሰእኔ ሰኔ
____

ግዕዝ ሙላት


@yegetemkalat
@poem_merry