ለምን??? አየሁት ህመምን የፍቅርን ክፋት ለሌሎች መድኃኒት ለኔ ሲሆን ጥፋት ለሌሎቹ ሀሴት ድርብርብ ያለ ፀጋ ለኔ ግዜ እርግማን የናፍቆት አለንጋ አየሁ ሌሎችንም.... በውቡ ዋርካ ስር በናፍቆት ሲያወሩ ፊታቸው ይደምቃል፣ የተቀመጡበት ያ የፍቅር ምድር ይባስ ውበቱ ያድጋል፣ እኔም እንደነሱ ደስታን ለማግኘት ሄድኩ መላልሼ ፣ ደንዳናውን ልቤን በፍቅር ላርሰው ቅንጣቱን ቀምሼ፣ ግና...... ብፀልይ ብሞክር ለኔ ካላደለው ልፋት ምን ያደርጋል፣ ጥንዶቹ ያስዋቡት ያ ለምለሙ ቦታ ገና እግሬ ሲረግጠው የኔ ግዜ ይደርቃል። kidst @poem_merry @yegetemkalat 2.1K viewsMerry G, edited 17:13