Get Mystery Box with random crypto!

ከባዱ እና ቀላሉ ዛሬ ቀለል ቀለል ያሉ ምርጫዎችንና መንገዶችን ብቻ ስትከተሉ፣ ነገ ሕይወታችሁ | እግር ኳስ Meme™

ከባዱ እና ቀላሉ

ዛሬ ቀለል ቀለል ያሉ ምርጫዎችንና መንገዶችን ብቻ ስትከተሉ፣ ነገ ሕይወታችሁ ከበድ ይላል፡፡ በተቃራኒው፣ ዛሬ ከበድ ከበድ ያሉ ምርጫዎችንና መንገዶችን ስትከተሉ፣ ነገ ሕይወታችሁ ቀለል ይላል፡፡ ስሌቱ ይኸው ነው፡፡

ዛሬ በርትቶ የመማር ምርጫ፣ ጠንክሮ የመስራት ምርጫ፣ ጨክኖ ለሕይወታችሁ ከማይሆኗችሁ ሰዎች የመለየት ምርጫ . . . እነዚህ ምርጫዎና መንገደች ዛሬ ከባድ ናቸው፣ ነገ ሕይወታችሁ ቀለል እንዲል ግን በቂ የሆን ክፍያን ከፍላችሁ እንድታልፉ መንገድን ይጠርጉላችኋል፡፡

ዛሬ አለመማር፣ አለመስራት፣ ትክክለኛ ወዳጅን ለመመርጥ ጊዜ አለመውሰድ፣ በየማሕበራዊ ሚዲያው ላይ ተጥዶ መዋልና የመሳሰሉት ምርጫዎችና መንገዶች በጣም ቀላል ናቸው፣ ብዙም ጥረት አይጠይቁም፡፡ እዚህ ምርጫዎ ግን የነገ ሕይወታችንን እጅግ ከባድ ያደርጉብናል፡፡

ዛሬ ከባዱን ምርጫና መንገድ ምረጡና ነገ ቀላሉን ሕይወት ኑሩ!   

መልካም ቀን!

ሀሳብ አስተያየት እንዲሁም ለማማከር @buchula36 ላይ አውሩኝ

@poem_merry
@yegetemkalat