Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴ ማዉራት የምትፈልጋቸዉ ነገሮች ከአፍ አልወጣም ብለዉ ይተናነቁሀል ማድረግ የምትፈልገዉን ነ | እግር ኳስ Meme™

አንዳንዴ ማዉራት የምትፈልጋቸዉ ነገሮች ከአፍ አልወጣም ብለዉ ይተናነቁሀል ማድረግ የምትፈልገዉን ነገር በሙሉ ማረግ እስኪያቅትህ ድረስ ትተሳሰራለህ።
ምንም ትርጉም የሚሰጥ ነገር እስክታጣ ድረስ ሁሉም ትርጉም የለሽ ይሆናል ማን እንደተሳሳተ ግራ ይገባኛል እኔ ወይስ እኔን የፈጠረዉ መልስ የማይኖራቸዉ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ይኖራሉ ጊዜ የሚፈታቸዉ ግን እዛ ጊዜ ላይ እደርሳለሁ ወይ የሚለዉ ሌላ ጥያቄ ነዉ ።
ለሌሎች በመፍራት መወሰን የነበረብን ነገሮች ሳንወስን ስንቶቻችን ህመም ዉስጥ ተዘፍቀናል ከኔ በላይ ሌላዉ ይጎዳል ብለን እነሱ ከሚጎዱት እጥፍ እየተጎዳን ያለን እልፎች ነን ይሄ ህመም መቼ እንደሚያበቃ ሁላ የማናቅ ፅኑ ህመምተኞች በሌሎች አይን ግን ሁሉ የሞላልን ምንም ጉድለት የሌለብን በሳቃችን በፈገግታችን ህይወት የሚመዘንልን በየቤታችን የሚቆጥር ይቁጠረን።
ተስፋ የሚባል ስንቅ እስከዛሬ ያኖረዉ ወደር የለዉም ተስፋ እራሱ በተስፋ ተስፋ አያረግም ይሆናል ግን በተስፋ የሚኖር እንደ ጉድ ነዉ ተስፋ ተስፋ የሚሆነዉ ምን ሲኖረዉ ነዉ ? በምን መንገድስ በየትኛዉ ሚዛንስ ሲመዘን ነዉ ዋጋ ኖሮት ህይወት የሚያስቀጥለዉ? ማንስ ለማን ተስፋ ይሆናል ማን በማንስ ተስፋ መኖር ይቀጥላል ? ነገ ምን ያመጣል የእዉነትስ በነገ ላይ ሀይል እና አቅም ያለዉ ማን ነዉ ? ህይወት ላይ ማን እርግጠኝነት ይሰጣል ? እርግጠኝነትን የሚሰጠዉስ በራሱ ምን ያህል እርግጠኛ ነዉ ?
በዙ ጥያቄ አለ አጥጋቢ መልስ የሌለዉ ጥያቄ መሆኑንም የረሳነዉ ማንን መጠየቅ እንዳለብን እንኳን ያላወቅነዉ ብዙ ጥያቄ ?!

@pome_merry
@mikotad2