ባንቺ ሆዬ ቅኝት ፡ አምባሰል መቀኘት ገዘፍኩኝ እያሉ ፡ ዝቅ ብሎ መገኝት ሙሉንትን ደፍቶ ፡ ባዶነትን መልቀም የፈየደን ጎድቶ ፡ የጎዳን ሰው መጥቀም : የሚል እድፋም እውነት ጥይፍ ሐቅን ታቅፎ ፡ ቀን ከሌት መራመድ ለሙቀት በጫሩት ፡ ባነደዱት እሳት ፡ ተ..ቀ..ጣ...ጥ..ሎ ማመድ : ከኑረት ግንድ ላይ ተሰብሮ ለመርገፍ ፡ ለመውደቅ መጣደፍ ከፍካታም ጸዳል ፡ ከውበት ተጋባሁ ፡ ጠራሁ ሲሉ ማደፍ !! : እንዲያ ነው !! **//* ዳግም ሔራን @dagiamen12 @poem_merry @yegetemkalat 5.7K viewsMerry G, 18:00