Get Mystery Box with random crypto!

የግጥም ቃላቶች: ​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━ | እግር ኳስ Meme™

የግጥም ቃላቶች:
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​─━━─━━ ⊱✿⊰ ━━━━━━──


እባክህ አንድዬ

ከወለዱት በላይ እዝነትህ ይልቃል
ቢሰወርም ከኛ ላንተ ይታወቃል...
ጎርፉን አድርቅና መንጥረህ ጫካውን
ገላልጠህ እውነቱን አስገኘው ጨቅላውን

እባክህ አንድዬ....
በጆችህ ነውና መኖሩም መሞቱ.....
ያለበትን አውቃ ልቧ እንዲያርፍ እናቱ
ይሄውና በለን አሳየን ማርኮንን.......
በኛ አቅም አልሆነም ደከምን ባከንን
እባክህ አንድዬ ሳታድር ሳትውል.....
በረቂቅ ጥበብህ ጠቁመን አንድ ውል
አስሩን እያሰብን ተምታተናል እኛ ....
ካለበት አውጥተህ አምጣልን ወደኛ..

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━


@poem_merry
@poem_merry