Get Mystery Box with random crypto!

ባሱ አረ ባሱ ባሱ ህዝቤን አስጨረሱ ምስኪን አስለቀሱ አረግ እነዚህስ እጅግ በጣም ባሱ | እግር ኳስ Meme™

ባሱ
አረ ባሱ ባሱ
ህዝቤን አስጨረሱ
ምስኪን አስለቀሱ
አረግ እነዚህስ
እጅግ በጣም ባሱ
ከሄዱት አነሱ
ሀይ ይበልልን እርሱ
ለነገሩስ እነርሱ ለሱ
አዬ ሊመለሱ
እኛማ ደከመን
እጅጉን አመመን
ሟች መቁጠር ሰለቸን
አረ ሰሚው ስማን
ሰላም ሰማይ ሆነ
ፈተናው ፈጠነ
መከራችን በዛ
ሳቃችን ጠነዛ
ሀገር ወዟን አጣች
በባሱት ገረጣች
ነፃ አውጪው በዛባት
ከሰላም አነፃት
ነፃ ላውጣ ብሎም
በሴት ደም አጠባት
በህፃን ልጅ ለቅሶ
ዳንስ እየደነሰ
ያለ ሽማግሌ
እርቃኗን አስቀሯት
አረ ውይ ውይ ውይ ውይ
ምን አጥፍተን ይሆን
ለድፍን ሶስት አመት
ይህን ሁሉ ስቃይ
ይሄንን ሁሉ መአት
መችነው ህዝቧን በልተው
መቼስ ነው ሚጠግቡት
እስኪጠግቡ ስ ድረስ
ነብስን ሚገበቱት
ወታደር ባለበት
ሀገር የሚያፈርሱት
የባሱስ ሚብሱት? ።?

ካልታደለው ትውልድ
ከ ረቂቅ መላኩ የተፃፈ