Get Mystery Box with random crypto!

አጭር ወግ (በሰሚር) ዲያስፖራው ሀገር ቤት ሄዶ ጎረቤት ሊጠይቅ ሄዶ ነው:: 'ውይይ እማማ ታመ | እግር ኳስ Meme™

አጭር ወግ (በሰሚር)

ዲያስፖራው ሀገር ቤት ሄዶ ጎረቤት ሊጠይቅ ሄዶ ነው::

"ውይይ እማማ ታመው ነበር?? በጣም ከሱኮ... በስመአብ ድሮኮ ጢም አድርጎ የጫነ አይሱዙ ይከልሉ ነበር ሃሃሃሃሃ"

"ምን ታደርገው ልጄ ታምሜ ከረምኩና እንዲህ ውልቅ አልኩ!" (በሆዳቸው ጥርስህ ይውለቅ ይሉታል መቼም)

"ጠዋት ተነስተው ሙዝ: ስትሮበሪ: ከተገኘ ብሉቤሪ : እላዩ ላይ የለውዝ ቂቤ ጣል አድርገው በወተት ጁስ እየፈጩ ቢጠጡ ሰውነቶ ይመለሳል:: ከእድሜዎምጋ ስለማይሄድ ስኳር አያድርጉበት:: በማር ይሻልዎታል::"

"አሄሄሄ ልጄ ለአፍ ዳገት የለው አለች ያቺ እናትህ እውነቷንኮ ነው! ስኳሩ የሞት መድሃኒት እንኳን ቢሆን ከየት እንደልብ ተገኝቶ!"

"ይቅርቦት አይጠቅሞትም! ስኳር: ጨው: ጮማ ... መርዛማ ናቸው:: ስጋውንም ቀይ ቀዩን ይብሉ:: በተጨማሪ እንቅልፍ ጥሩ ነው... ትኩስ ወተቶትን ጠጥተው ለሽ ቢሉ ምናለ ይበሉኝ .. በ2 ወር ሰውነቶ ይመለሳል:: ብቻ ይሞክሩት!"

እማማ ያው ይሄን ሁሉ የሚቦተረፈው የ2 ወሯን ሊዘጋት ነው ብለው ወደ አፍ ሁሉ የሚገባውን ሲያስቆጥራቸው ሰሙት.... ሲወጣ 500 ብር ቆጥሮ 'ለአንዳንድ ነገር' ብሎ ሲሰጣቸው ምን አሉ??

"አንዳንድ ነገሮቹንስ በዚህ ገዛኃቸው... ዋና ዋናዎቹን በምን ልግዛቸው?? የጠራሃቸውን የአንድ አትክልት ተራ ገበያ ፍራፍሬዎችስ : ቀይ ቀዩን: ወተቱን: ማሩን... በምን ልግዛቸው?? ምናል ከአፍህ ቆጠብ አድርገህ ከእጅህ ጨመር ብታደርገው??" አሉት.....

እና ምን ለማለት ነው??

አንዳንዶቻችሁ ብቸኛ መፍትሄያችሁ እኔ ያልኩት ነው የምትሉትን እሺ ይሁን... በዛው መዳረሻውንም እየጠቆማችሁን!!! ምነው ?!!!


ሰላሙን ያምጣልን ውብኛ ዋሉልኝማ

Semir ami