Get Mystery Box with random crypto!

ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን

የቴሌግራም ቻናል አርማ phnotesedksenbettmhrtbet — ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን
የቴሌግራም ቻናል አርማ phnotesedksenbettmhrtbet — ፅርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን
የሰርጥ አድራሻ: @phnotesedksenbettmhrtbet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 317
የሰርጥ መግለጫ

ስለ ተዋህዶ
የተለያዮ ኮርሶች ሚሰጡበት
ስለ ሰንበት ትምህርት ቤታችን ወቅታዊ መረጃዎች

ለተዋህዶ ልጆች በመላክ ሀላፊነታችንን እንወጣ
@Emamlaknn

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-29 09:22:33 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


ሠላም የተዋሕዶ ልጆች እንደምን ከረማችሁ እንደተለመደው በዚሕም ወር ጉዞ ወደ ታላቁ ሸንኮራ ቅዱስ ዮሐንስ ገዳም

መነሻ በሠኔ 29
መመለሻ ከንግስ በኋላ


መነሻ ቦታ አራብሣ ቅዱስ ገብርኤል
መነሻ ሠዐት 12:00
መስተንግዶን ጨምሮ 400 ብቻ

0978160422
0965930075
77 viewsMel፰ Yemamlak, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 14:38:23 በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ደብረ ምጥማቅን በፃድቃኔ ማርያም
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ
ወደ ደብረ ምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም እና ደብረ ምህረት አጃና ሚካኤል
ቀን:20/09/2014ዓ.ም መመለሻ 21 ከንግስ በኋላ
መነሻ ሰአት:11:00
የጉዞ ዋጋ መስተንግዶን ጨምሮ:400ብር ብቻ
መነሻ ቦታዎች
1.አራብሣ ቅዱስገብርኤል ቤ/ክ
2,መገናኛ ህዳሴ ህንፃ
ለበለጠ መረጃ:0982851449
0965930075

ሰአት ይከበር
አለባበስዎ ክርስቲያናዊ ይሁን

አዘጋጅ: ማህበረ አሐዱ መንፈሳዊ ማህበር
173 viewsMel፰ Yemamlak, 11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 18:18:20 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን ::
ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ሳማሠንበት መነሻ ቀን መጋቢት 17 መመለሻ መጋቢት 18 መመዘገቢያ ቦታ ቦሌ አረብሳ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አቅራቢያ አሀዱ ንዋይተ ቅዱሳን መሸጫ ለበለጠ መረጃ በ 0978160422 ወይም 0965930075 ይደዉሉ እናመሠግናለን

@menfesawiguzozeahadu
@ahadumezimurbet123
292 views፯፪፩, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 22:00:30

የንግስ በዓል ጥሪ


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ

የቅድስት ሥላሴ አመታዊ በዓለ ንግስ


መቼ:-  ቅዳሜ ጥር 07/05/2014ዓ.ም

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ  ጉባኤ ተዘጋጅቷል።


ቦታ:- በየረር በር ጽርሀ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን


በበአሉ ቀንም ታላላቅ መምህራን፣ ዘማርያን፣እንዲሁም በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ማሪዎች ልዩ የሆነ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ተዘጋጅቷል ።


በመሆኑም በጉባኤው ላይ እንዲሁም በአመታዊ ክብረ በአሉ ላይ በጠዋቱ እና በማታው መርሃግብር ላይ በመሳተፍ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


አድራሻ:- ጎሮ ሰፈራ ወይንም ሰሚት በሁለተኛ በር ገባ ብሎ

ጆሮ ያለው ይስማ ላልሰማ ያሰማ
     

share  share  share
469 views , 19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-21 07:05:51

የንግስ በዓል ጥሪ


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሀዱ አምላክ

የአባታችን የአቡነ አረጋዊ በአለ ንግስ


መቼ:- እሁድ ጥቅምት 14/02/2014ዓ.ም

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ልዩ ጉባኤ ተዘጋጅቷል።


ቦታ:- በኤረር ጽርሀ አርያም ቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን


በበአሉ ቀንም ታላላቅ መምህራን፣ ዘማርያን፣ ሰባኪያን፣እንዲሁም በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ማሪዎች ልዩ የሆነ ያሬዳዊ ዝማሬዎች ተዘጋጅቷል ።


በመሆኑም በጉባኤው ላይ እንዲሁም በአመታዊ ክብረ በአሉ ላይ በጠዋቱ እና በማታው መርሃግብር ላይ በመሳተፍ የበረከቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።


አድራሻ:- ጎሮ ሰፈራ

ጆሮ ያለው ይስማ ላልሰማ ያሰማ


share share share
462 viewsMel፰ Yemamlak, 04:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-20 19:52:50
373 views , 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-07 23:45:19 ልደቱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ

ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም

በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር፤ ሚስቱም ኤልሣቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፤ እርሷም የመውለጇ ዘመን አልፎ ነበር፡፡ ሆኖም ሁለቱም በእግዚአብሔር የታመኑ ጻድቃን ነበሩ፡፡

ከዕለታት በአንድ ቀንም ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት በገባበት ሰዓት በዕጣን መሠውያው በቀኝ በኩል የእግዚአብሔር መልአክ ቆሞ ታየው፤ በዚያን ጊዜም በፍርሃት ተሞላ፤ መልአኩም እንዲህ አለው፤ ‹‹ዘካርያስ ሆይ፥ አትፍራ፤ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ፊት ተሰምቷልና፤ ሚስትህ ኤልሣቤጥም ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡ ደስታና ሐሤትም ይሆንልሃል፤ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጅምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል፡፡ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎቹን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር ይመልሳቸዋል፡፡ እርሱም የአባቶቻችን ልብ ወደ ልጆች፥ የከሓዲያንንም ዐሳብንም ለእግዚአብሔር የተዘጋጀ ያደርግ ዘንድ በኤልያስ መንፈስ ቅዱስና ኃይል በፊቱ ይሄዳል፡፡›› ዘካርያስም መልአኩን እንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅቻአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል፡፡›› መልአኩም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንም እነግርህና አበሥርህ ዘንድ ወደ አንተ ተልኬአለሁ፡፡ አሁንም በጊዜው የሚሆነውንና የሚፈጸመውን ነገሬን አላመንኽኝምና ይህ እስኪሆን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም ይሳንሃል፡፡›› (ሉቃ.፩፥፲፫-፳)

ከዚህም በኋላ ሚስቱ ኤልሣቤጥ ፀነሰች፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፀንሳ እናቱ ኤልሣቤጥን ለመጠየቅ በሄደችበት ወቅት በማሕፀኗ ውስጥ ሳለ ሕፃኑ ለእግዚአብሔር ልጅ ሰገደ፡፡ (ሉቃ.፩፥፴፱-፵፩)

በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈው ኤልሣቤጥ የመውለጃዋ ጊዜ በደረሰ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች፡፡ መውለዷን የሰሙ ዘመዶቿና ጎረቤቶቿም ደስ ተሰኙ፤ ልጁንም ስምንት ቀን በሞላው ጊዜ ሊገረዙት መጡ፤ ስሙንም በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ወደዱ፤ ነገር ግን እናቱ ዮሐንስ ተብሎ መጠራት እንዳለበት ተናገረች፡፡ ሆኖም ግን ከዘመዶቿ መካከል ስሙ ዮሐንስ የሚባል ባለመኖሩ አባቱ እንዲወስን ካህኑ ዘካርያስን በጠየቁት ጊዜ መናገር የተሣነው ዲዳ ነበርና ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ሲጽፍ ሁሉም ተደነቁ፤ በዚያን ጊዜም የዘካርያስ አንደበት ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡ (ሉቃ.፩፥፶፪-፷፬)

ካህኑ ዘካርያስም መንፈስ ቅዱስ በመላበት ጊዜ እንዲህ ብሎ ትንቢት መናገር ጀመረ፤  ‹‹ይቅር ያለን፥ ለወገኖቹም ድኅነትን ያደረገ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ ከባርያው ከዳዊት ቤት የምንድንበትን ቀንድ አስነሣልን፤ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ በቅዱሳን በነቢያት አፍ እንደ ተናገረ፡፡ ከጠላቶቻችን እጅ፥ ከሚጠሉንም ሁሉ እጅ ያድነን ዘንድ፤ ቸርነቱን  ከአባቶቻችን ጋር ያደርግ ዘንድ፤ ቅዱስ ኪዳኑንም ያስብ ዘንድ፤ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ያስብ ዘንድ፤ ከጠላቶቻችን እጅ ያድነን ዘንድ ያለ ፍርሃት፥ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ በዘመናችን ሁሉ እንድናመልከው ይሰጠን ዘንድ፤ አንተም ሕፃን፥ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ መንገዱንም ትጠርግ ዘንድ በፊቱ ትሄዳለህና፡፡ ኃጢአታቸው ይሰረይላቸው ዘንድ መድኃኒታቸውን እንዲያውቁ ለአሕዛብ ትሰጣቸው ዘንድ፤ ከአርያም በጎበኘን በአምላካችን በይቅርታውና በቸርነቱ፤ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩት ብርሃኑን ያሳያቸው ዘንድ፥ እግሮቻቸውንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ፡፡››(ሉቃ.፩፥፷፰-፸፱)

ከዚህም በኋላ ንጉሡ ሄሮድስ ጌታችን ኢየሱስን ለመግደል ይፈልገው ስለነበር የተወለደ ወንድ ሁሉ እንዲገደል በወሰነው መሠረት ሕፃኑ ዮሐንስን እንዲገድሉት ጭፍሮችን ወደ ካህኑ ዘካርያስ ላከ፤ በዚህም ጊዜ አባቱ በትክሻው ተሸክሞ ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ በመሠዊያው ጠርዝ ላይ ካኖረው በኋላ ወታደሮቹን መውሰድ ከቻሉ ከዚያ እንዲወስዱት ነገራቸው፡፡ ከመቅጽበትም የእግዚአብሔር መላክ ነጥቆ ወደ በረሀ ወሰደው፡፡ ወታዳሮቹም ሕፃኑን ባጡት ጊዜ አባቱ ዘካርያስን ገደሉት፡፡ ዮሐንስም አድጎ በሀገረ እስራኤል እስከተገለጠበት ጊዜ በበረሀ ኖረ፡፡ ጌታችን ኢየሱስም ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ  ዮሐንስን የሚበልጠው የለም›› ብሎ የመሠከረለት ነቢይ፣ ሐዋርያ፣ ሰማዕት ነው፡፡  (መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ሰኔ ፴ ገጽ ፬፻፸፱- ፬፻፹)

የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ አማላጅነት እና ተራዳኢነት አይለየን፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤ አሜን።
593 viewsMel፰ Yemamlak, 20:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-03 21:26:52 ወዳጆች ሆይ! ማፈር የሚገባን ኃጢአት ስንሠራ እንጂ ንስሐ ስንገባ አይደለም፡፡ ኃጢአት ሕመም ነው፤ ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው፡፡ ከኃጢአት ቀጥሎ ሐፍረት አለ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ፡፡ ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
430 viewsMel፰ Yemamlak, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-02 07:23:10 የአንቺ ሥጋ ይገርመኛል ከሔዋን ተገኝቶ ከመላእክት ይልቅ ንጹህ ሆኗአልና፣ አፈር ነህ ከተባለው ከአዳም ተወልደሽ በሰማይ በአባቱ ቀኝ በተቀመጠው ንጉሥ በክርስቶስ ክቡር ሰውነት ላይ በተለየ ክብር ሆኖ በሰማያት ታይቷልና። ባለ ራዕይው ዮሐንስ ...ከአንቺ በነሳው ሥጋ ከተወጋው ቁስለቱ ጋር ወደ ሰማይ እንደወጣ ቢያየው.. እንዲሁ ይመጣል ብሎ በመጽሐፍ ነገረን ....የወጉትም ሁሉ ያዩታል ተብሎ ተጻፈ ።

የታናሿ የአንቺ ገላ ሰማይ ለሚጠበው አምላክ ልብስ ሆነ። መሰወሪያው ከዚህ ነው የማይባለው ልዑል ሥጋሽን ለብሷልና ...ሥጋ ሆነ...ተባለለት። ከባሕሪው እሳት የሆነውን እርሱን ሁሉ ዳሰሰው ሁሉ አቀፈው። መለኮታዊ ክብሩን በአንቺ ሥጋ ውስጥ ቢሰውረው... የወደቀው ሰውም አምላክ ሆነ...ተባለ። ይደንቃል።
ደንግል ሆይ
መላእክት በቤተልሔም በአንቺ ላይ የሆነውን ቢመለከቱ ..ስብሐት ለእግዚአብሔር.. ..አሉ። ሌላ ምን ይባላል? የማይወርደው ከከፍታው ወርዶ ሲታይ በአድናቆት ..ስብሐት ..ነው እንጂ
ሰማይ ከክብሩ የተነሣ የምትጠበው ..በአንቺ ክንድ ላይ ሲያዩት ምን ይበሉ? ኦ ማርያም በአንቺ የሆነውን ለመፃፍ የሚያስብ ቃለ ጸሐፊ ከፍቅሩ የተነሣ ብዕሩ በእንባ ስለሚርስ ስለ አንቺ እንዲህ ነው ለማለት ቃልና አቅም በማጣት ...ሰአሊ ለነ ...ብሎ ጽሑፉን ይዘጋዋል። አይችልምና።
411 viewsMel፰ Yemamlak, 04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-02 07:23:09 ይህች ማን ናት??? ፡-
1.ፀጋን የተሞላች ከሴቶች ተለይታ የተባረከችና እግዚአብሔር
ከእርሷ ጋር የሆነ።
* መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ
ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ
ነሽ አላት።
የሉቃስ ወንጌል 1 : 28
2.በእግዚአብሔር ፊት ፀጋን ሞገስን ያገኘች።
* መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር
ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።
የሉቃስ ወንጌል 1 : 30
3.የሰላምታዋ ድምፅ ፅንስ በደስታ ያዘለለ።
* ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ
በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ
ሞላባት፥
የሉቃስ ወንጌል 1 : 41
4.ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚሏት ።
* የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ
ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
የሉቃስ ወንጌል 1 : 48
5.ፍፁም ትሁት። * የባሪያይቱን ውርደት ተመልክቶአልና።
እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
የሉቃስ ወንጌል 1 : 48
6.ቅዱሳን ያከበሯት።* የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ
እንዴት ይሆንልኛል?
የሉቃስ ወንጌል 1 : 43
7.ሰዎች በተጨነቁ ሰአት የምትማልድ።
* የወይን ጠጅም ባለቀ ጊዜ የኢየሱስ እናት። የወይን ጠጅ እኮ
የላቸውም አለችው።
የዮሐንስ ወንጌል 2 : 3
8.ምልክት ፀሐይን የተጎናፀፈች አህዛብን ሁሉ በብረት በትር
ይገዛ ዘንድ ያለውን ወንድ ልጅ የወለደች።* ታላቅ ምልክትም
በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት
በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት
አንዲት ሴት ነበረች።
የዮሐንስ ራእይ 12 : 1 * አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር
ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ
እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።
የዮሐንስ ራእይ 12 : 5
9.ዘንዶው ያሳደዳት። * ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ
ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
የዮሐንስ ራእይ 12 : 13
10.ዘንዶው በዘሯየተቆጣና ዘሯን ሊዋጋ የሄደ።
* ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት
የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን
ሊዋጋ ሄደ፤
የዮሐንስ ራእይ 12 : 17
11.ውብ የሆነች።* ወዳጄ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ውብ ነሽ፥እንደ
ኢየሩሳሌምም ያማርሽ ነሽ፤ዓላማ ይዞ እንደ ተሰለፈ ሠራዊት
ታስፈሪያለሽ።
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 4
* ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፥ እርሱ ጌታሽ ነውና።
መዝሙረ ዳዊት 45 : 11
12.የወርቅ ልብስ ተጎናፅፋ በእግዚአብሔር ቀኝ የምትቆም።
የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው፤ በወርቅ ልብስ
ተጐናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።
መዝሙረ ዳዊት 45 : 9
13.ንጉስ ዳዊት ልጄ ያላት።* ልጄ ሆይ፥ ስሚ እዪ ጆሮሽንም
አዘንብዪ፤ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤
መዝሙረ ዳዊት 45 : 10
14.ልጆቿን ገዥ አድርጋ የምትሾም።* በአባቶችሽ ፋንታ ልጆች
ተወለዱልሽ፥ በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ
ትሾሚያቸዋለሽ።
መዝሙረ ዳዊት 45 : 16
15.ተዘግቶ የሚኖረው የምስራቁ በር።* እግዚአብሔርም። ይህ
በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።
ትንቢተ ሕዝቅኤል 44 : 2
16.የናቋት ሁሉ የሚሰግዱላት አማናዊት ፅዮን።*
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ
ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤
የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን
ይሉሻል።
ትንቢተ ኢሳይያስ 60 : 14
17.በድንግልና ፈጣሪዋን የወለደች ምልክት
* ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል
ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ
ትጠራዋለች።
ትንቢተ ኢሳይያስ 7 : 14
18.እግዚአብሔር ያስቀረልን ዘር።* የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር
ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም
በመሰልነ ነበር።
ትንቢተ ኢሳይያስ 1 : 9
19.ቅዱስ ጳውሎስ ንፅህት ድንግል ያላት።
* በእግዚአብሔር ቅንዓት እቀናላችኋለሁና፥ እንደ ንጽሕት
ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ
አጭቻችኋለሁና፤
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11 : 2
20.ንገስታት የሚያመሰግንዋት።* ርግቤ መደምደሚያዬም
አንዲት ናት፤ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች
ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ንግሥታትና ቍባቶችም
አመሰገኑአት።
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 9
21.ማን ናት???* ይህች እንደ ማለዳ ብርሃን የምትጐበኝ፥እንደ
ጨረቃ የተዋበች እንደ ፀሐይም የጠራች፥ዓላማ ይዞ እንደ
ተሰለፈ ሠራዊት የምታስፈራ ማን ናት?
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 6 : 10።
በአንቺ የሚኖሩ ሁሉ ደስ እንደሚላቸው ይነግራቸዋል።
መዝሙረ ዳዊት 87 : 7።
393 viewsMel፰ Yemamlak, 04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ