Get Mystery Box with random crypto!

ፍልስፍና

የቴሌግራም ቻናል አርማ philosophyeth — ፍልስፍና
የቴሌግራም ቻናል አርማ philosophyeth — ፍልስፍና
የሰርጥ አድራሻ: @philosophyeth
ምድቦች: መዝናኛዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.66K
የሰርጥ መግለጫ

Welcome to the world of philosophy
For any information contact us:
@Hisandphilobot

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-01 22:28:31 በጣም ደስ የሚል ታሪክ ነው።በብሎገራችን ላይ ያገኙታል።ገብተው ያንብቡ።
አንብባችሁ አስተያየት ለሰጣችሁን እናመሰግናለን

https://lamprosmagazine.blogspot.com/2023/01/blog-post_30.html?m=1
427 viewsMY STRUGGLE, 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 21:50:15 ጨዋ ሰው ማለት ንግግርና ተግባሩ የገጠመለት ነው።
          -- Confucius --

JOIN US
425 viewsMY STRUGGLE, 18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 17:20:42 የበታችነት ስሜት (Inferior complex)

ሰው በሁለት ነገሮች ተጠምዶ ህይወቱን ያባክናል። ወይ በበታችነት ስሜት ወይ ደግሞ በበላይነት ስሜት ይሰቃያል።

አንድ ሰው በበታችነት ስሜት ከተያዘ ውስጡ በጥልቀት ይታመማል፡፡ ከንቱ እንደሆነ እያሰበ ከኖረ በህይወት የመቆየቱ ጉዳይ አስቸጋሪ ይሆናል። በህይወት እየኖረ ቢሆንም ሙት ነው፡፡ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ በህይወት የሚቆዩ በጣም ጥቂት ሰዎች አሉ። አብዛኞቹ ግን ከመሞታቸው በፊት የሚሞቱ ናቸው። በሰባ አመታቸው ቢቀበሩም የሞቱት ግን ቀደም ብለው ነው። በሞታቸውና በቀብራቸው መሀል የሰላሳ፣ የአርባ ወይም የሃምሳ ዓመታት ክፍተት ሊኖር ይችላል፡፡

በዙሪያችሁ የተንሰራፋውን ግዝፈተ ተፈጥሮ ስትመለከቱ የበታችነት ሊሰማችሁ ይችላል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሰው ምንም ነው። በውቅያኖስ ሞገዶች ላይ እንደተንሳፈፈ ገለባ ነው። ምንም አይነት ሃይልም ሆነ አቅጣጫ የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት የበታችነት ስሜት አይምሮን ጨምድዶ ከያዘ የሰው ህይወት በመከፋት የተሞላ ይሆናል። በህይወት የሚኖር ሙት ይሆናል፡፡ ህይወቱ አመድና ትቢያ ይሆናል። የህይወታችሁ ነበልባል ከውስጣችሁ ከጠፋ፣ የፋኖሳችሁ ነበልባል ከጠፋ፣ በፀሃይ ብርሃንም ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ ለናንተ ፀሃይ ምንም ጥቅም አይኖራትም፡፡

በሰው ውስጥ መላው ግዝፈተ ተፈጥሮ እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በሰው ውስጥ መለኮት እንደሚገኝ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም ሰው የበታች አይሆንም፡፡ በጣም የሚገርመው ሰው የበታችነት ስሜቱን ለማውደም አስቦ በበላይነት ስሜት መጃጃሉ ነው። የበታችነት ስሜቱን ለማፈን የተለያዩ መንገዶችን መፈለግ ይጀምራል። ውስጡን የበታችነት ስሜት ሲሰማው ሃብት በማከማቸት ለአለም ህዝብ ከንቱ አለመሆኑን ሊያሳይና ከሌላው የበላይ የመሆን ስሜት ሊሰማው ይችላል። ከበታችነት ስሜቱ የተነሳ ጭንቅላቱ ላይ ዘውድ ደፍቶ ከንቱ አለመሆኑን ለማሳየት ይሞክራል። የበላይነት ፉክክር ውስጥ የሚከተው የበታችነት ስሜት ነው። እናም የበላይ ለመሆን በሚደረግ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ያሉ ሰዎች ያለጥርጥር ውስጣቸው በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ ነው።

ከዚህ አንፃር አድለር ብዙ አስገራሚ ነገሮችን ተናግሯል። ገለፃዎቹ አስፈላጊ ናቸው። እንደ አድለር ገለፃ ከሆነ በሩጫ ውድድር አንደኛ የሚወጡ ሰዎች በልጅነታቸው በትክክል መራመድ የማይችሉ ነበሩ። ልዩ የሙዚቃ ክህሎት ያላቸው በልጅነታቸው መጠነኛ የመስማት ችግር የነበረባቸው ናቸው፡፡ ርዕሰ ብሔር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት ደግሞ በትምህርት ቤት ህይወታቸው ኋላ ወንበር ላይ የሚቀመጡ የነበሩ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በልጅነት በደረሰባቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ሳቢያ ከንቱ አለመሆናቸውን ለዓለም ለማሳየትና ለማረጋገጥ ይፈልጋሉ። አንድ ፖለቲከኛ በበታችነት ስሜት ቢሰቃይ አያስገርምም፡፡ ከንቱ ነኝ የሚል የበታችነት ስሜት ውስጡን እንደ ትል ይበላዋል፡፡ በዚህም አይምሮው ተጐድቶ ችግር ውስጥ ይከተውና የበላይ መሆኑን ለማሳየት ወደ ውድድር እንዲገባ ያነሳሳዋል።

ሌኒን ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ አይደርሱም ነበር፡፡ ከወገቡ በላይ ያለው የሰውነቱ ክፍል ከወገቡ በታች ካለው ይረዝም ነበር። እናም ወንበር ላይ ሲቀመጥ እግሮቹ ወደ ወለሉ መድረስ አይችሉም፡፡

ሂትለር ደግሞ ተራ ንቃተ ህሊና የነበረው ወታደር ነበር። በዚህም የጦር ሰራዊቱ አባል ለመሆን አትመጥንም ተብሎ ተባሮ ነበር። ስታሊንና ሊንከንም የጫማ አዳሽ ልጆች ነበሩ፡፡

የአለማችንን ፖለቲከኞች የኋላ ታሪክ ብንመለከት እንገረማለን። የእሽቅድምድማቸው መንስኤ በልጅነታቸው የገጠማቸው የበታችነት ስሜት ጉዳት ነው፡፡ በዚህም ሳቢያ እንደ እብድ መሽቀዳደም የጀመሩ ናቸው፡፡ ወደ አንድ የከፍታ ጫፍ ላይ መውጣት ካልቻሉ አይረኩም፡፡ እዛ የከፍታ ጫፍ ላይ በመውጣት ከንቱ አለመሆናቸውን ለአለም አሳይተዋል። በውስጣቸው ግን ምንም ነበሩ። ከዚህ አንፃር ሁሉም ስልጣን፣ ሃብት፣ ወይም ዝና ለባለቤታቸው ትርጉም አልባ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ግለሰቡ የፈለገውን በእጁ ቢያስገባም ውስጡን ግን ያው እንደ በፊቱ ሆኖ ያገኘዋል። የበታችነት ስሜቱ አሁንም እንደ ትል ይበላዋል። ትልቁ የስልጣን እርከን እንኳ እርካታን አያመጣም፡፡ እናም ቀድሞ መገኘት ያለው እሽቅድምድም አይጠፋም፡፡ አንድ ሰው አሌክሳንደርን፡- “አለምን ለመቆጣጠር እንደምትፈልግ ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን አለምን ከተቆጣጠርክ በኋላ ምን እንደምታደርግ አስበህበት ታውቃለህ?ምክንያቱም ያለው አንድ አለም ብቻ ነው።” ሲል ጠይቆት ነበር፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ እሌክሳንደር በጣም ተከፍቶ፡- “በዚያ መልኩ አስቤ አላውቅም፤ ትክክል ነህ፡፡ መላውን አለም ከተቆጣጠርኩ በኋላ ምን አደርጋለሁ? ሌላ አለም ያለው የት ነው?” በማለት መልሷል። አለምን ከተቆጣጠረ በኋላ እንኳ አይምሮውን ጠፍሮ ከያዘው የበታችነት ስሜት ማምለጫ አይኖረውም፡፡ ሌላ አለም ቢኖርና ቢቆጣጠረው እንኳ ማምለጫ አይኖረውም፡፡ የበላይነት ስሜት የበታችነት ስሜት ነፀብራቅ ነው።

በኩራት የሚኮፈስና ሌሎች እንዲታዘዙት ሃይል የሚጠቀም ስው ሊታዘንለት ይገባል፤ ምክንያቱም በበታችነት ስሜት እየተሰቃየ መሆኑን ነው፡፡ በዚህ የአይምሮ ጭንቀት ሳቢያም የበላይ ለመሆን በሚደረጉ የእብዶች እሽቅድምድም ውስጥ ተካፋይ ይሆናል።

የበታችነት ስሜት በሽታ ነው፤ ይህን የበታችነት ስሜት ለመደበቅ የሚመጣው የበላይነት ስሜት ደግሞ የባስ በሽታ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ መድሃኒቱ ከበሽታው ይልቅ አደገኛ ነው።

ምንጭ ፦ የንቃት ፀሀይ (ኦሾ)
ተርጓሚ ፦ መርሻ በነበሩ
480 viewsMY STRUGGLE, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 22:15:13
የዚህ ቻናል ትልቁን ውጤት እለቅላችኋለሁ ካስፈለገ
469 viewsMY STRUGGLE, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 19:56:01 ስንፍናን ማሸነፍ!

በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ #ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ #የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተ ነፍ ነው። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ #ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው።

በቀን ውስጥ #አደርጋለው ያልከውን #ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ የምትችለው #በየቀኑ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ #በማድረግ ነው።

“ይህንም ቃሌን ሰምቶ #የማያደርገው ሰው ሁሉ ቤቱን በአሸዋ ላይ የሠራ ሰነፍ ሰውን ይመስላል።”
  — ማቴዎስ 7፥26

                       
468 viewsNave, edited  16:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 13:23:25 ፍልስፍና-Philosophy pinned «#በራሳችሁ_እመኑ! ማንም ሰው ባያምንባችሁም... እናንተ ግን በራሳችሁ እመኑ! ኮኖሱኬ ማትሱሺታ ... ጃፓናዊ ነው! (Panasonic) እኤአ ከ1894-1989 የኖረ... የኤሌክትሪክ መሰኪያ ሶኬት ከመስራት ሀሳብ... ተነስቶ በዓለም ዙሪያ የሚታወቅ ትልቅ የቢዝነስ ድርጅት ለማቋቋም ችሏል። እንዴት?! ለሚለው ሙሉውን ታሪክ አንብቡት https://lamprosmagazine.blogspot.com/2023/01/blog…»
10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 13:00:46 የዚህ ቻናል ትልቁን ውጤት እለቅላችኋለሁ ካስፈለገ
472 viewsMY STRUGGLE, edited  10:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ