Get Mystery Box with random crypto!

ነጠላ ሠረዝ ( ፣ ) ”በሕይወት ውስጥ እንደዚህ ነው። ብዙ ነጠላ ሠረዞች አሉ። የሚታዩ | ፍልስፍና

ነጠላ ሠረዝ ( ፣ )

”በሕይወት ውስጥ እንደዚህ ነው። ብዙ ነጠላ ሠረዞች አሉ። የሚታዩ እንጂ የማይነበቡ። የሚሰሙ እንጂ የማይደመጡ።

የአንተ ችግር ነጠላ ሠረዙን ሁሉ ስለ ምታነብ ነው። ነጠላ ሠረዝ- ሰዎች፣ ነጠላ ሠረዝ ሐሳቦች፣ ነጠላ ሠረዝ -ድርጊቶች፣ ነጠላ ሠረዝ - ክስተቶች፣ ነጠላ ሠረዞች - ችግሮች ሞልተዋል። ሁሉም ግን ይታያሉ እንጂ አይነበቡም። ትዘላቸዋለህ።

ቢበዛ - ገታ - ያደርጉህና ፋታ ትወስድባቸዋለህ። ከዚያ በላይ ግን ቦታ አትሰጣቸውም። ትሻገራቸዋለህ። ነጠላ ሠረዞቹ ግን ለአነባበብህ ያስፈልጉሃል፤ በሕይወትህ ውስጥ ያሉ ነጠላ ሠረዞቹም የአኗኗርህን መንገድህን ይቀይሩልሃል።


ኑ! ሀገሬን እናዋልዳት
እና ሌሎች

(ገፅ፡64)
__
በ-ዳንኤል ክብረት

ከወደዱት ሼር ያድርጉት።

Join us
https://t.me/philosophyeth