Get Mystery Box with random crypto!

ማየት የማይችሉ ሰውዬ ከእግራቸው ጎን ጨርቅ አንጥፈው ይለምናሉ፡፡ ጨርቁ ላይ በብጣሽ ወረቀት “አይ | Peace tv amharic

ማየት የማይችሉ ሰውዬ ከእግራቸው ጎን ጨርቅ አንጥፈው ይለምናሉ፡፡ ጨርቁ ላይ በብጣሽ ወረቀት “አይነ ስውር ነኝ እባካችሁ እርዱኝ” የሚል ፅሑፍ ተፅፏል፡፡የተወሰኑ ሰዎች የሰውዬውን ሁኔታና የተፃፈውን ወረቀት እያዩ ጨርቁ ላይ ሳንቲም እየጣሉ ይሄዳሉ፡፡ቢሆንም ግን ጨርቁ ላይ በጣም ትንሽ ሳንቲም ነው የሰበሰቡት፡፡

አንድ ልጅ በዛው መንገድ እያለፈ ነበር፤ ከኪሱ ሳንቲም አወጥቶ ጨርቁ ላይ ከጣለላቸው በሗላ የተፃፈውን ወረቀት አንስቶት በግልባጩ የተወሰኑ ቃላቶችን ፅፎበት ሄደ፡፡ የፃፈውን ሰዎች እንዲያዩት ወረቀቱን ገልብጦ አስቀምጦት ሄደ፡፡

በትንሽ ጊዜ ውስጥ ጨርቁ በሳንቲም ይሞላ ጀመር፡፡ ለአይነ ስውሩ ከቅድሙ ይልቅ ብዙ ሰዎች ሳንቲም ይሰጡት ጀመር፡፡ በዛው ቀን ከሰዐት ወረቀቱን የቀየረው ልጅ በመንገድ ሲያልፍ የሰውዬውን ሁኔታ ሊያይ ይቀርባቸዋል፡፡ አይነስውሩ የልጁን አረማመድ ስላወቁ “ልጄ ወረቀቱ ላይ የተፃፈውን የቀየርከው አንተ ነህ?” ብለው ጠየቁት፤ ልጁም “አዎ እኔ ነኝ” አላቸው፡፡
ሰውዬው ካመሰገኑት በሗላ “ምን ብለህ ፅፈህበት ነው?” አሉት
ልጁ “ እኔ የፃፍኩት እውነታውን ነው፤ በሌላ መልኩ ቢሆንም ያልኩት እርሶ ያሉትን ነው” አላቸው፡፡
ልጁ የፃፈው “ ዛሬ የሚያምር ቀን ነው፤ ነገር ግን ላየው አልቻልኩም” የሚል ነበር፡፡ ሱብሃነላህ!!

የመጀመሪያውና ልጁ የፃፈው አንድ አይነት ይመስላሉ አይደል? በርግጥ ሁለቱም ፅሑፎች የሰውዬውን አይነስውርነት ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የመጀመሪያው ፅሑፍ ሰውዬው እውር መሆኑን ብቻ ነው የሚናገረው፤ ሁለተኛው ፅሁፍ ሰዎች እንደ ሰውዬው አይነስውር ባለመሆናቸው እድለኛ መሆናቸውን የሚጠቁም ነው፡፡

“እርሱም ያ መስሚያዎችንና ማያዎችን ልቦችንም ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፡፡ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡” (ሱረቱል ሙዕሚኑን ምዕራፍ 23 አንቀፅ 78)
አልሃምዱሊላህ!!
https://www.facebook.com/peacetvamharic/