Get Mystery Box with random crypto!

መፅሐፍቶችን በpdf

የቴሌግራም ቻናል አርማ pdfffb — መፅሐፍቶችን በpdf
የቴሌግራም ቻናል አርማ pdfffb — መፅሐፍቶችን በpdf
የሰርጥ አድራሻ: @pdfffb
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.28K
የሰርጥ መግለጫ

"እንኳን ደህና መጣችሁ"Welcome!
በpdf(በሶፍት ኮፒ) ለማንበብ ራሳችንን እናስለምድ!
፨ተራ ነገር በመስራት የሚባክነውን ጊዜያችንን በንባብ ላይ ስናውለው ከራሳችን አልፈን ለብዙዎች የመለወጥ ምክንያት እንሆናለን፡የንባብ ባህላችንን እናዳብር! ባለንበት ራሳችንን በእውቀት እንገንባ!
፨በዚህ ቻናል የተለያዩ መፅሐፎች፣ጠቃሚ ሀሳቦች፣አፕልኬሽኖች፣አነቃቂ ምስሎች ቀርቦላችኋል አውርደው ይጠቀሙ።

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 08:31:48
7 views05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 11:10:14 #የጭንቀት #ምንጮች #ምንድን #ናቸው?

የጭንቀት ምክኒያቶች በርካታ ናቸው፡፡ ሆኖም በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ለይቶ ማየት ይቻላል፡-
1. ስነ ልቦናዊ መንስሄዎች
2. አካላዊ

1.#ከስነ #ልቦናዊ #ምንጮች፦ በስራ ቦታ በሚፈጠር የሥራ ጫና፣ የሥራ አሰራር ግልፅነት ማጣት፣ ከሚወዱት ሰው ጋር የሚፈጠር ችግር፣ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ግዴታዎችን መወጣት አለመቻል፡- ለምሳሌ የቤት ኪራይ፣ አስቤዛ፣ ወርሃዊ የመብራት ክፍያ ወዘተ…፣ ለአዳዲስ ነገሮች መዘጋጀት፡- ለምሳሌ ልጅ መወለድ፣ አዲስን ስራ መያዝ፣ የትራፊክ መጨናነቅ፣ ከፍተኛ ድምፅ…

2. #አካላዊ #መንስሄዎች፦ ህመም፣ ከፍተኛ የአየር ሁኔታ፡- ለምሳሌ ከባድ ሙቀት ወይም ከባድ ቅዝቃዜአካላዊ ህመም፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ከመጠን ያለፈ አልኮል መጠጣትና ሲጋራ ማጨስ በሰውነት ላይየሚፈጥሩት ጫና ወዘተ ናቸው።

የጭንቀት ውጤቶች ምንድን ናቸው?

የሰውነት ድካም
ከፍተኛ የራስ ምታት
ብስጭት
የምግብ ፍላጎት መዛባት
የማስታወስ ችሎታ መቀነስ
ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ወይም ክብር መቀነስ(low self-esteem)
ከማህበራዊ ህይወት መገለል
የ ደም ግፊት መጨመር
ትንፋሽ ማጠር
የወሲብ ፍላጎት መቀነስ
የእንቅልፍ መዛባት
የጨጓራና አንጀት ስርዓት መዛባት
የልብ ህመም
የቆዳ ችግር (skin disorders)

ጭንቀት ለስነልቦናዊ ቀውሶች ለምሳሌ፡- ለፍርሃትና ለድብርት ይዳርጋል፡፡

ጭንቀትን ለመቆጣጠር የሚከተሉትን መፍትሄዎች ይጠቀሙ።
በውስጣችን የሚያቆጠቁጠውን የተስፋ ቢስነት ስሜት ማወቅ
የቁጣ ስሜቶቻችንን መለየት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ
የሚወዱትን ሥራ መሥራት
አስቂኝ ፊልሞችንን መመልከት
ራስን አለማማረር
ባለሙያ ማማከር

ጤናማ እና ደስተኛ የሆነ ህይወትን ለመምራት፣ ጤናዎን ለመጠበቅ፣ ስላጋጠሞት የጤና እክል ምንነት እና መፍትሄ ለማግኘት ከስነ-ልቦና ባለሙያ ማማከር ከፈለጉ ዶክተር አለ 8809 ላይ እየደወሉ መፍትሄውን እንመካከር፡፡ሚስጥሮ 100% የተጠበቀ ነው!!!

(#የሥነ #ልቦና #ባለሙያ #ሃና #በየነ)
90 views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:04:40 #ካነበብኩት_05
#ድንቁ_መፅሐፍ በውስጡ ምን ምን ነገሮችን አካቷል?

-›ይህ መፅሐፍ የ5መፅሐፍቶች ስብስብ ሲሆን እነሱም
1.ምስጢሩ(secret)
2.ታላቁ ኃይል(the power)
3.ታላቁ ሚስጥር(magic )
4.ጀግና(hero)
5.ምስጢሩን መጠቀም(how to use the secrete)
ባጠቃላይ ደግሞ #ምስጢሩን_ማወቅ ተብሎ ተሰይሟል::
•በዋነኝነት ይህ ድንቅ መፅሐፍ ሚያትተው ስለ #ስበት_ሕግ #ወርቃማው_ሕግ ( #low_of_attraction) ይሆናል እናም ይህ ሕግ እንደ ስበት( #gravity) ሁሌም ይሰራል አወቅነውም አላወቅነውም ::
•ታዲያ ለምን ስለ ሕጉ አውቀን አንተቀምበትም? እናም ወዳጆቼ መፅሐፉ ውስጥ ያሉትን ጥቂት መርሆች በተለይ ደግሞ 3ቱን (መጠየቅ :ማመንና ማመስገን) በመከተል ካለንበት ሕይወት ወደተሻለ ሕይወት ከፍ ማለት ይቻላል::
•መጀመሪያ ምንፈልገውን እንጠይቃለን በማስከተልም እንደተሰጠን ራሳችንን እናሳምናለን (ከጥርጣሬ ነፃ) በመጨረሻም ለተሰጠን ነገር ምስጋና እናቀርባለን:: #ግን አስተውሉ ይህ ሁሉ ሚሆነው ነገርየው ከመሆኑ በፊት በ አእምሯችን(imagination) ውስጥ ነው! ከሁሉም በፊት ደግሞ ራስን ከቂም በቀለኝነት ነፃ ማድረግ ይገባል ያኔ ሁሉም የጠየቃችሁት ሁሉ በ እጃችሁ ይገባል!

•መፅሐፉም በ600ገፆች ተዋቅሯል
•ከስነ አእምሮ መፅሐፍቶች መካከል በዋነኝነት የምንም ጊዜ ምርጡና ተወዳጁ ነው

..ይህ አንተን ለምን ወደዚች ምድር እንደመጣህ የሚገልፅ ታሪክ ነው:: አንተ ልዩ የሚያደርግህ አንዳች ነገር አለ:: የተወለድከው ሌሎች ሰባት ቢሊየን ሰዎች ማድረግ የማይችሉትን እንድትከውን ነው:: እንድትኖረው የታለመ ህይወት: እንድትከተለው የተተመነ ጎዳና አለህ:: ይህ መፅሐፍ ሚያወራው ስለዚህ ጎዳና ነው::
4.ጀግና
ገፅ 393
መልካም ንባብ
148 views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:10:20
ልዩ ቅናሽ ሽያጭ ::

ሶስት መጻሕፍት በ 280 ብር ብቻ ::

በአካሉ ቢረዳ አማካኝነት ከእንግሊዝኛ ወደአማርኛ የተተረጎሙ ሶስት መጻሕፍትን በ280 ብር ብቻ እየሸጥን ነው ::

እነዚህ መጻሕፍት በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ዝናን ያተረፉ ሲሆኑ በአገራችን አንባቢያን ዘንድም የታወቁ የራስ አገዝ መጻሕፍት ጸሐፍት ናቸው ::

" በግል ጥረት ስኬታማ የሆነ ሰዎች ምስጥር " የተሰኘው መጽሐፍ በ አዳም ኩ የተዘጋጀ ሲሆን እንግሊዝኛውም " Secret of Self-Made Millionaire " ሲሰኝ በ 370 ገጾች የተቀነበበ ነው ::

2 , " ሰው ሁን " የተሰኘው መጽሐፍ በ ቤድሮስ ኩሊያን የተዘጋጀ ሲሆን በ 212 ገጾች የተቀነበበ ነው ::

3, " መሰናክልህን ውደደው " የተሰኘው የ በሪያን ሆሊደይ መጽሐፍ ሲሆን በ 200 ገጾች የተቀነበ ነው ::

ማስታወሻ :-

መጻሕፍቱ ጥቂት ቅጂዎች መጋዘን ላይ የተገኙ ሲሆን ሶስቱን መጽሐፍ በአንድ ላይ ለሚገዙ 280 ብር ነው ::

ለየብቻም መግዛት ትችላላችሁ :: ትርፋማ የምትሆኑት ግን አንድላይ ስትገዙት ነው ::

Self help መጻሕፍት ማንበብ ለምትወዱ ይህ መልካም አጋጣሚ አይለፋችሁ ::

ጃዕፈር መጻሕፍት ::
175 views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 08:07:07
150 views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:28:24
አስተማሪ ፈጠራ!
183 views05:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:27:40
174 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 08:27:30 ክረምትና:ንባብ:ምንና:ምን:ናቸው?
ያንገት:ኃብልና:የጆሮ:ጌጥ:ናቸው።

የኛ:የክረምት:ወራት:ዋነኞቹ:ኹለት:ብቻ:ናቸው:ሐምሌና:ነሐሴ።:ሌላው:የሰርገኛ:በረበሬ:ቀንጣሾች:ናቸው።ክረምትና:ንባብ:ምን:አቆራኛቸው?ከቁርኝታቸው:ዋና:ዋና:ምክኒያቶች:አንዱ:ዕረፍት:ነው:ተማሪም:የመንግሥት:ሰራተኛውም:ሌሎችም...ከገበሬ:በቀር:በሬ:ከሚገፋው:የምርት:ኃይል:ውጪ:አብዛኞቹ:መደባት:የምርት:ኃይሉ:ያመረተውን:ምርት:እየተቀለቡ:ዕርጥበት:ሳይነካቸው:ቁር:ሳይቆሮቁራቸው:ውሽንፍር:ሳያውቃቸው:ጣፋጭ:ሻያቸውን:ከጣፋጭ:ተረቶቻቸው:ጋር:እያጣጣሙ:እንደ:ዘንዶ:ጥቅልል:ብለው:ያሳልፉታል።
አጀብ!
የሚያሞቃቸው:ሻሂ:ቅጠል:ከጉመር:ይኹን:ከውሽውሽ:ከበርቴውም:ኾነ:ንዑሴ:ከበርቴው:ምንተዳው:ወንድሜ?
የሐምሌን:ንጭንጭ:በበውቀቱ:ወዛም:ቀልድ:ሶፋኽ:ላይ:ጋደም:ብለኽ:ትወዛለኽ።
የሰኔን:ነጎድጎድ:በሙሉጌታ:ሉሌ:ግጥም:በአበበ:ተካ:አባ'ቢ:ድምፅ:"እንደ:ሰኔ:ሠማይ"ን:እያደመጥኽ:ጭን:የሚያሞቀውን:'ሮዛን':ታነብባለኽ:የሰኔ:ሠማይ:አስገምግሞ:ሲበቃው:ባለፈር:ጃኬትኽን:ደርበኽ:በላዩ:ካፖርትኽን:ጣል:አድርገኽ:ሽርሽር:ትወጣለኽ።
የአዝርዕት:እህል:ማነስ:የማዳበሪያ:መወደድ:የመሬት:መለስለስ:የሠማይ:መጨከን:ሕማምኽ:አይደሉም:ምክኒያቱስ?
ከፍተኽ'ኮ:አይደለም:የካፒታሊስት:ሥርዓቱ:ነው:ባሻዬ!
167 views05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:07:29 “ለምን?” ብለህ ጠይቅ

ለመሻሻልና ለመለወጥ ከፈለክ፣ “ለምን?” ብለህ ከመጠየቅ አትረፍ!

• “አሁን የምኖረውን ኑሮ በዚህ መልኩ የምኖረው ለምንድን ነው?”

• “ገቢዬ ለምን በዚህ ብቻ ተወሰነ?”

• “አምኜ የተቀበልኩትን የሕይወቴን ሂደት ለምን ተቀበልኩት?”

• “የማደርገውን ነገር በዚህ መልኩ የማደርገው ለምንድን ነው?”

• “በሕይወቴ መሻሻል የሚችል ነገር አለ ወይ? ካለስ ለምን
አላሻሽለውም? እንዴትስ ላሻሽለው እችላለሁ?”

እነዚህና እነዚህን የመሳሰሉ ጥያቄዎችን መጠየቅ ይህ ነው የማይባል የአእምሮ መነቃቃት ያመጣል፡፡ የተለመደውን የኑሮውን ሂደት “ለምን?” በማለት የማይጠይቅ ሰው በአንድ ቦታ ለመርጋትና ሃውልት ለመሆን ራሱን ያዘጋጀ ሰው ነው፡፡

አንድ ሰው ለመሻሻልና ለመለወጥ አእምሮውን ሊያነቃቃና የተለመደውን የየእለት የኑሮውን ዑደት “ለምን?” ብሎ ሊጠይቅ ይገባል፡፡ ይህ ከተነቃቃ አእምሮ የሚነሳ ራስን የማሻሻልና የመለወጥ ጉዞ ባሉበት ሳይረኩ ከዛሬ ሁኔታ የተሻለ ነገር ውስጥ ለመግባት አስፈላጊውን ነገር ወደማድረግ ይወስደናል፡፡

እንዲሁ የመጣውን ሁሉ በመቀበልና በማስተናገድ በእድል ለመሻሻል ከመሞከር፣ አእምሮዬ እንዲሻሻል ማንበብ፤ የገቢዬ ምንጭ እንዲሻሻል ሙያዬንና ብቃቴን ማዳበር፣ ማሕበራዊ ኑሮዬ እንዲሻሻል ደግሞ ባህሪዬን ማጤንና ማሻሻልን ይጠይቃል፡፡

አንድን እውነታ መዘንጋት የለብኝም፣ የእኔነቴና የብቃቴ መሻሻል ዙሪያዬንና ሁኔታዎቼን ሁሉ ለመልካም የመለወጥ ብርታትና ተጽእኖ አለው፡፡ ስለዚህም፣ ማንነቴ፣ ብቃቴና ችሎታዎቼ መድረስ የሚችሉበት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ መጠየቅና መንቀሳቀስን አለማቆም ተገቢ ነው፡፡

አንዳንድ ዝም ብለህ ልትቀበላቸው የሚገቡህ ነገሮች የመኖራቸው እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሁሉንም ነገር ግን ዝም ብለህ በጭፍንነት አትቀበል - “ለምን?” ብለህ ጠይቅ!!!

ዶ/ር እዮብ ማሞ
226 views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ