Get Mystery Box with random crypto!

ጳልቃን የማኀደረ ጻድቃን ሰ/ት/ቤት የቴሌግራም ገፅ (ቻናል)

የቴሌግራም ቻናል አርማ palkanmahderetsadqan — ጳልቃን የማኀደረ ጻድቃን ሰ/ት/ቤት የቴሌግራም ገፅ (ቻናል)
የቴሌግራም ቻናል አርማ palkanmahderetsadqan — ጳልቃን የማኀደረ ጻድቃን ሰ/ት/ቤት የቴሌግራም ገፅ (ቻናል)
የሰርጥ አድራሻ: @palkanmahderetsadqan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 203
የሰርጥ መግለጫ

እነሆ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት የሻ/ደ/አ/አ/ተክለሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን ማኅደረ ጻድቃን ሰ/ት/ቤት "ጳልቃን" ዘ ማኅደረ ጻድቃን። የተሰኘ የሰንበት ትምህርት ቤቱ ይፋዊ የቴሌ ግራም ገፅ ነው።

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 06:49:18
62 viewsቤንጃሚን, 03:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 19:37:35 ༺༒༻ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሚካኤል ༺༒༻

እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!! ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ የሌሊቱ ቃለ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።

፩. ነግሥ / ሰላም ለጒርዔክሙ /

ሰላም ለጒርዔክሙ ስቴ አንብዓ ሰብእ ዘኀሠሠ፤
ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤
እመ ትትሀየዩኒሰ ኢትኀድጉኒ ጽኑሰ፤
ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ፤
ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ፡፡

ዚቅ፦

ኢይጽሕቅ ዘይመክሮ ወኢየኀሥሥ ዘይረድኦ፨ አልቦቱ ጥንት ወኢተፍጻሜት ፨ ኢየኃልቅ መንግሥቱ ወአልቦ ዘይክል መዊዓ ኃይሉ ፨ ወአልቦሙ ኍልቍ ለሠራዊተ መላእክት እለ ይትለአክዎ ፨ አንተ ውእቱ አቡሃ ለጥበብ ገባሬ ኲሉ ፍጥረት ወገባሬሃ ለሕግ፡፡

፪. ነግሥ / ሰላም ለልሳንከ /

ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤
አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ፦

አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ ፨ በደብረ መቅደስየ አሜሃ ፨ ይትነሥኡ ሙታን ፨ ይትፌሥሑ መላእክት በዕርገቱ፨ በፍሥሐ ወበሰላም ፨ አእኰትዎ ለንጉሠ ስብሐት ።

፫. ሰላም ለዝክረ ስምከ / መልክአ ሚካኤል/

ሰላም ለዝክረ ስምከ ምስለ ስመ ልዑል ዘተሳተፈ፤
ወልደ ያሬድ ኄኖክ በከመ ጸሐፈ ፤
ሶበ እጼውዕ ስመከ ከሢትየ አፈ፤
ረዳኤ ምንዱባን ሚካኤል በከመ ታለምድ ዘልፈ፤
ለረዲኦትየ ነዓ ሰፊሐከ ክንፈ፡፡

ዚቅ፦

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ፨ ዓቢተነ በመድኃኒትከ ፨ ጸግወነ ንጸውዕ ስመከ ፨ ኖላዊነ ኄር ትጉህ ዘኢትነውም ሰላመከ ሀበነ፡፡

ወረብ፦

ሀበነ ሰላመከ ንጸውዕ ስመከ፤
ዘኢትነውም ትጉህ ኖላዊነ ኄር ኖላዊነ ኄር።

፬. ሰላም ለአስናኒከ / መልክአ ሚካኤል/

ሰላም ዕብል ለአስናኒከ ዘመንፈስ፤
ዘኢይረክቦን ጥረስ፤
ሚካኤል ረዳኢ ለእለ ውስተ ባሕር ወየብስ፤
እስመ ረሰየከ ካህነ ምሥዋዑ ክርስቶስ፤
መፍትው ሊተ ትተንብል ቀሲስ፡፡

ዚቅ፦

ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ ምስሌሁ፨ ርኢክዎ ለሚካኤል ወስእንኩ ጠይቆቶ ፨ ዮም ሰማያዊ በምድር አስተርአየ ፡፡

ወረብ፦

ባሕራንኒ ይቤ ዘነገደ ባሕረ፤
ርኢክዎ ለሚካኤል ወስዕንኩ ጠይቆቶ ጠይቆቶ ስዕንኩ።

፭. ሰላም ለእስትንፋስከ /መልክአ ሚካኤል/

ሰላም ለእስትንፋስከ ቊሱላነ ነፍስ ለአጥዕዮ፤
ዘይነፍሕ ፄና አንህዮ፤
ሚካኤል ነዓ ኲናተከ በተረስዮ፤
ለገቢር ከመ ቀዳሚ ለአርዌ ዓመፃ ደርብዮ፤
እስመ ኢኀደገ እንከ ዘትካት እከዮ፡፡

ዚቅ፦

ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል ፨ እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ ፨ ወእሰብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጺውዋን ፨ ወእፈውሶሙ ለቍሱላነ ልብ፨ ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ ፨ዝኬ ውእቱ ዘተነግረ በመዋዕለ ትካት ለእሥራኤል ፨ ኅብስተ መና ዘአውረደ በገዳም ፨ ወርእየቱ ከመ ተቅዳ፨ ወከመ አያያተ መዓር ጥዑም ፈድፋደ ፡፡

ወረብ፦

ወከሢቶ ረከበ ወከሢቶ ረከበ ኀበ ይብል እዜንዎሙ ለነዳያን ፈነወኒ፤
ወእስብክ ሎሙ ግዕዛነ ለጺውዋን ወእስምዮ ለባሕራን ኅሩየ።

፮. ሰላም ለአጻብዒከ / መልክአ ሚካኤል /

ሰላም ለአጻብኢከ መጽሐፈ እለ ለክዑ፤
ዕጒለ አባግዕ እምኖሎት በጊዜ ተመልዑ፤
ሚካኤል አንተ ለንጉሠ ነገሥት ካህነ ምሠዋዑ፤
አሣዕነ መድኀኒት ለእገርየ አጻብዒከ ይቅጽዑ፤
ከመ በፍናውየ የኀዝ ለሰላም ቅብዑ፡፡

ዚቅ፦

ቅዱሳት አጻብዒከ ለጽሒፈ መጽሐፍ እለ ተቀንያ፨
ወብፁዓት አዕይንቲከ ምሥጢረ መለኮት ዘርእያ፧
ሚካኤል መልአክ ወሐዋርያ ፡፡

ወረብ፦

ምሥጢረ መለኮት ዘርእያ አዕይንቲከ፤
ሚካኤል መልአክ መልአክ ወሐዋርያ ሚካኤል መልአክ።

፯. አምኃ ሰላም / መልክአ ሚካኤል /

አምኃ ሰላም አቅረብኩ ለመልክእከ ኲሉ፤
ለለ አሐዱ አሐዱ ዘበበክፍሉ፤
ሚካኤል ክቡር ለልዑል መልአከ ኃይሉ፤
ተወኪፈከ አምኃየ እምኑኀ ሰማያት ዘላዕሉ፤
ዕሴተ ጸሎትየ ፈኑ ወአስብየ ድሉ፡፡

ዚቅ፦

መልአከ ሰላምነ ሊቀ መላእክት ሚካኤል ፨ ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ፨ አዕርግ ጸሎተነ ቅድመ መንበሩ ለንጉሥ ዓቢይ ።

ወረብ፦

መልአከ ሰላምነ መልአከ ሰላምነ፤
ሊቀ መላእክት ሚካኤል ሰአል ወጸሊ በእንቲአነ።

°༺༒༻°   አንገርጋሪ °༺༒༻°

አመ ይስቅልዎ አይሁድ ለእግዚእነ ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ
ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ፡፡

°༺༒༻° ምልጣን  °༺༒༻°

ወሪዶ እመስቀሉ አብርሃ ለኲሉ።

  °༺༒༻° አመላለስ °༺༒༻°

አመ ይሰቅልዎ አይሁድ ለእግዘእነ፤
ሚካኤል አርመመ ወገብርኤል ተደመ።

  °༺༒༻°  እስመ ለዓለም  °༺༒༻°

ሞዖ ለሞት እግዚኡ ለሚካኤል ተንሥአ ወልድ በሣልስት ዕለት፤ ፈጺሞ ሥርዓተ አርቲዖ ሃይሞኖተ ፤ ኀበ አቡሁ ዓርገ ሰማያተ፤ ጰራቅሊጦስሃ መንፈሰ ጽድቅ አውረደ። 

°༺༒༻°  አቡን በ ፩ ሃሌ °༺༒༻°

ዓቢይ ስሙ ወዓቢይ ኃይሉ ለእግዚአብሔር፤ ወይቤሎ ለሚካኤል ተንስእ ንፋሕ ቀርነ፤ በደብረ ሲና በደብረ ጽዮን፤ በሀገር ቅድስት፤ በዓቢይ ስብሐት ይሴብሕዎ መላእክት።

  °༺༒༻° አመላለስ °༺༒༻°

በሀገር ቅድስት በሀገር ቅድስት፤
በዓቢይ ስብሐት ይሴብሕዎ መላእክት።

   °༺༒༻°   ዓራራት  °༺༒༻°

ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአርዳኢሁ አዓርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ኀበ እስእል ምሕረተ፨ በእንተ እሊአየ አዓርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ፨ ኀበ አዕላፍ መላእክት ፨ (አዓ)ኀበ ሚካኤል ወገብርኤል ፨ (አዓ) ኀበ ሱራፌል ወኪሩቤል፨ (አዓ) ኀበ ዑራኤል ወሩፋኤል( አዓ) ኀበ ራጉኤል ወሳቁኤል፨ አዓርግ ሰማየ ኀበ አቡየ ዘፈነወኒ ፨ውእቱ የዓቢ እምኲሉ።

°༺༒༻°  ሰላም  °༺༒༻°

አመ ይነፍሕ ሚካኤል ቀርነ በደብረ መቅደስየ አሜሃ ይትነሥኡ ሙታን ይትፌሥሑ መላእክት በዕርገቱ በፍሥሐ ወበሰላም አእኮትዎ ለንጉሠ ስብሐት ።

°༺༒༻° ተፈጸመ °༺༒༻°

የቅዱስ ሚካኤል ፍጹም ልመናው ፤ የጸሎቱ ረድኤትና አማላጅነቱ ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ይኑር በእውነት አሜን!!!

ሰኔ ፲፪/ ፳፻፲፬ ዓ.ም
193 viewsቤንጃሚን, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 22:44:00
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?! በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ትምህናት ቤት ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ሐዋርያቱ በቅጽበት የዓለም ቋንቋ ተምረው የተመረቁባት ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡

ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምዕመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
184 viewsቤንጃሚን, 19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 22:26:29
"የአምላካችን ቤት ከቶ አንተውም!!!" {መጽ.ነኅ.10፥39 }
ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲካሄድ የነበረው 11ኛው ዓለም አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ !!!

በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በየዓመቱ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ሰንበት የሚከናወነው ይኸ ጉባኤ ከየአህጉረ ስብከቱ የተወከሉ አባላት የታደሙበት እና በሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት እና የአገልግሎት ሂደት ላይ ሲመክር የቆየ ጉባኤ ነው።
ጉባኤው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ለሁለት ቀናት የተካሄደ ሲሆን ሰኔ 5/2014 ዓ.ም በጉባኤው ፍጻሜ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
59 viewsቤንጃሚን, 19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:47:19 ጌታችን አምላካች መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማያርግበት ጊዜ የተስፋውን ቃል መንፈስ ቅዱስን በአንድ ቦታ ይጠብቁ ዘንድ ነገራቸው ሐዋ 1:4 እነሱም እመቤታችንን ይዘው በጸሎት እየተጉ መቶ ሀያ ሆነው የተስፋውን ቃል ይጠባበቁ ነበር ።በአንድነት ሆነው በመትጋታቸውም በዛሬው እለት መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው።
ዛሬም እንደ ሐዋርያት ቃሉን አክብራችሁ በቤቱ የተገኛችሁ ፤በቤቱ ለተገኙትም ባዶዋቸውን ይመለሱ ዘንድ መልካም አይደለም ብላችሁ ምግብ መንፈሳዊን በመመገብ ለተጋችሁ በሙሉ የህይወትን ቃል ያሰማልን።
አምላካችን ሐዋርያትን መንፈስ ቅዱስን እስኪቀበሉ ወዴትም እንዳይሄዱ ያዘዛቸው ወዲያ ወዲህ ከአንዱ ወደ አንዱ ሲሉ ቅዱሱ መንፈስ እንዳያመልጣቸው ብሎ ነበር
ምክንያቱም አባቶቻችን ከነገሩን ምክንያቶች አንዱ መንፈስ ቅዱስ በአንድ ቦታ ይወረዳልና ነው .....እዲሁም ወዲያ ወዲህ ሳትሉ መንፈስ ቅዱስን በተመላች ቤተክርስቲያን ውስጥ የተገኛችሁ ሁሉ ቃሉን አክብራችሁ መታችኋልና......እሱም ፈጣሪ ቃሉን ይረሳ ዘንድ አመጸኛ አይደለምና ደስ ይበላችሁ
በርሃግብር ለመሩልን ለጤና አዳምና ለአሮን
ወጉን ላወጋችን ለእህታችን ምህረት
ትምህርተ ወንጌሉን ላስተማሩን ለቀሲስ አክሊሉ
በዝማሬና በወረብ ላደመቁን ለዘማርያን
በተውኔታዊ ትረካ ለመከሩን ለአዳጊ ህጻናት ኪነጥበብ ክፍል እና ለታዳጊ ናትናኤል እዲሁም ለሁላችሁም "የአባቴ ቡሩካን ወደኔ ኑ"ያለውን ቃል ያሰማልን
62 viewsyabu Enat, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-05 21:36:34 ክርስትናና የጊዜ አጠቃቀም
በቀደመው ትምህርት የክርስትና የጊዜ አጠቃቀማችን ምን እንደሚመስል ችግሮቻችንን በማንሳት በወንድማችን በዲያቆን ማማሩ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ተምረን ነበር ። ዛሬ ደሞ ላወቅናቸው ችግሮቻችን እነሆ ተብለናል።
የክርስትና የጊዜ አጠቃቀማችን ደካማ የሆነው
1 ስለክርስትና ያለን ዕውቀት በቂ ስላልሆነ ነው።
ይህም አንድ ክርስቲያን ክርስቶስ የከፈለለትን ውለታ አለማወቁ የሚያመጣው ችግር ነው። ብዙ ቅዱሳን እሳቱን ስለቱን ያልፈሩት እነ ጊዮርጊስ በወፍጮ የተፈጬት በምጣድ የተጠበሱት በመጋዝ የተሰነጠቁት እና ቆዳቸው የተገፈፈው ይሄን ፍቅር ስላወቁት ነው ...ስለ አምላካችን ፍቅር ማወቅ ይህን ሁሉ መከራ እንደሚያስረሳ በቅዱሳን ህይወት አይተናል።
አንድ ሊቅ ሲናገር ...... ክርስቲያን ስለ 3 ነገር ክርስቲያን ይሆናል
ሀ/ ለራሱ ፦ ይህም የተለያዩ ፍጥረታት መፈጠራቸው ለራሳቸው ጥቅም ሳይሆን አብዛኛዎቹ ለሰው ማወቂያ መማሪያ መመራመሪያ ለመሆን ነው ..ለምሳሌ የጸሐይ መመላለስ ለእርሷ አንዳች ጥቅም የለውም የከዋክብትና የጨረቃ በለሊት መድመቅ እኛ አንደምናውቀው ስለሰው እንጂ ሌላ ምን ምክንያት አላቸው። ነገር ግን እኛ ብናገለግል ፣ንስሐ ብንገባ ፣ብንቆርብ፣ ብናስቀድስ ለኛው ጥቅም ነው እንጂ ለማንም አይደለም......
ለ/ለሌላው፦ይህም ክርስቲያን በማስተማር በመዘመር በአጠቃላይ በአገልግሎት ለሌላው ለመትረፍ ክርስቲያን ይሆናል።
ሐ/ለሌላው፦ይህ ደግሞ ሰው ከእረፍቱ በዋኋላ በህይወቱ ሳለ በሰራው ስራ በሚሰጠው ቃል ኪዳን ለሰዎች ሲተርፍ ነው። ይህም በቅዱሳን በጸሎታቸው ተማምነን በፀበላቸው መፈወሳችን እምነቱን ተቀብተን መዳናችን እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ማግኘታችን ክርሰቲያን ለሌላው ሲተርፍ ነውና።
2 ይደርሳል በማለት፦ማቴ 6÷33 በሰው ልጅ ህይወት ወስጥ የማይደርሰው የክርስትና ህይወት ነው .....መመገብ በኋላም ይደርሳል በምግብ ዕጦት ብንሞትም መሞት አይቀርም ፣ ሀብትም ነገ ከነገ ወዲያ ይደርሳል ብንደኸይም የሀብታምም የደሃ መንገዱ አንድ ነው እራቁታችንን መጣን እራቁታችንን እንሄዳለንና አያስደንቀንም ፤ነገር ግን ክርስትና አይደርስም ሁሌም ዛሬ ነው ምክንያቱም ነገ የምንሆነውን አናውቅምና ። ሁሌም ነዌን እና አልአዛርን እናስታውሳቸው የአብርሃም እቅፍና እሳቱ ትዝ ይበለን ።
3/ስጋዊ ምልክቶችን እንፈልጋለን፦ማቴ 12÷39ምን ጊዜም እንደሰለስቱ ደቂቅ አምላካችን ያድነናል ባያድነን እንኳን አንተ ለቆምከው ምስል አንሰግድም ልንል ይገባል ። አምላካችንን በስጋዊ አዕምሮ ልንገምተው አይገባም ....ምክንያቱም ምልክት ፍለጋ አሁን አንዳለንበት ዘመን ለማይረባ አዕምሮ ያሰጣል። ይህም ለፈውስ ሳር መጋጥ ፣በካልቾ መመታ ፣ሰውን አስነጥፎ በላዩ ላይ መራመድ ሁሉ የደረሰብን ከዚህ ፍለጎታችን ነውና ልንተጋ ያስፈልገናል። 28/9/2014
76 viewsyabu Enat, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 08:50:54 " ወደ ሰማያት ዐረገ ክብርን ለበሰ እርሱን እናመስግን ለእርሱም እንገዛ ስለእኛ ወደ ሲኦል ወርዶ ኅያሉን ረግጦ ወደ ሰማያት በዕልልታ ዐረገ " ቅዱስ ያሬድ
219 viewsቤንጃሚን, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 08:50:46
207 viewsቤንጃሚን, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 21:01:58 የጊዜ አጠቃቀም
በእለተ እሁድ 21/9/2014 አዳራሽ የተሰጠ ክፍል አንድ ህይወት ተኮር ትምህርት
ትምህርቱ ሰው ለፈጣሪው በሚሰጠው ጊዜ ላይ የሚያጠነጥን ነበር።ይህንንም በ5 ነጥቦች ከፋፍሎ ወንድማችን ዲያቆን ማማሩ በደብ አድርጎ አስተምሮናል ።እነዚህም የክርስትና የጊዜ አጠቃቀማችን የሚከተሉትን ይመስላሉ
1 ለክርስትና ጌዜን ይሰጣሉ ነገር ግን የታሰበበት አይደለም
2ለክርስትና ጊዚዜ ይሰጣሉ ነገር ግን አስተማማኝ አይደለም
3 ለክርስትና ጊዜ ይሰጣሉ ነገር ግን እንደኪሳራ የሚቆጥሩ
4 ለክርስትና ጌዜን ይሰጣሉ ነገር ግን የሚሰጡት ጊዜ በፈተና የታጠረባቸው
5 ለክርስትና ምንም የተመደበ ጊዜ የሌላቸው
ማንኛውም ክርስቲያን ከእነዚህ ውስጥ እራሱን ያገኛል። እኛም ለክርስትናችን/ለፈጣሪያችን/ የምንሰጠው ጊዜ በህይወታችን ውስጥ ወሳኙ ጉዳይ ነውና የምንደራደርበት አይደለም ።ስለዚህ በ28/9/2014 በእለተ እሁድ በሰንበት ትምህርትቤቱ አዳራሽ በመደበኛ መርሃ ግር ላይ በመገኘት ለራሳችን መፈትሄን እንስጥ ። እንዳያመልጠን።
80 viewsyabu Enat, 18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 16:28:51 "#እባክህን_ከእሳቱ_ላይ_አትውረድ"

አንድ ወንድም አባ ጴሜንን "ምከረኝ" ብሎ ጠየቀው። አባ ጴሜንም "ድስት በእሳት ላይ እያለ ምንም አይነት ተባይ ሊቀርበውና ሊያበላሸው አይችልም። ከእሳት ወጥቶ ሲቀዘቅዝ ግን ነፍሳት ሁሉ ለመግባትና ለማበላሸት ይቻላቸዋል። ክርስቲያንም ከመንፈሳዊ ተግባር ካልራቀ ጠላት የድቀት ምክንያት አያገኝበትም" አለው።

ወዳጄ ሆይ ሕይወት ቀዝቅዛብሃለችን? ከእሳቱ ወደ መሬት ወርደህ በርደሃልን? የሕያውነትህ ሙቀት እሳት በማጣት ተንዘፍዝፏልን? ድስት የተባለ ሰውነትህ ክረምት የሚያህል ጉድን ተሸክሟልን? ዙሪያ ገባህ ፀሐይ እንደማትወጣበት ምእራብ ጨለማን የሚጠራ ሆኗልን? ማንነትህ እሳት እንዳጣ ምግብ ጥቃቅን ነፍሳት በተባሉ ኃጢአቶች (ቁጣ፣ ቸልተኛነት፣ ስስት፣ አልታዘዝ ባይነት፣ ጭንቀት፣ ሁሉን የመናቅ ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ...) ተወርሮ፣ መዓዛ ቅድስና ተለይቶት እጅ እጅ ብሏልን? ሞቅ የሚያደርገው አጥቶ በዓለማዊነት ሻግቷልን? የተባዮች መጫወቻ፣ የተውሳኮች መቀለጃ ሆኗልን? እንግዲያውስ በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ወዳጄ ሆይ ሃይማኖት በተባለችና ከሰማይ በወረደች ልዩ እሳት (ሉቃ.12፥49) ላይ ተቀምጠህ የድስትነትህን ሙቀት መልስ፡፡ እምነት፣ ተስፋና ፍቅር (1ቆሮ.13፥13) በተባሉ ሦስት ጉልቻዎች ላይ በምቾት ተጥደህ የሕይወትህን የኃጢአት ብርድ አስወግድ፡፡ ንስሐ በተባለች ነበልባል ውበትነት የክረምትህን ጽልመት በምስራቃዊ በጋነት ድል ንሳ፡፡ በሥጋ ወደሙ ፍምነት ድስት የተባለ ሰውነትህን በከዊነ እሳትነት ቀድስ፡፡ እባክህን በቶሎ ወደ እሳቱ ውጣ፡፡

ሃይማኖት የተባለ እሳትን ተባይ አይቀርበውም፡፡ እምነት ተስፋና ፍቅር የተሰኙ ጉልቻዎችን ተውሳኮች ሽቅብ አይወጡአቸውም፡፡ የነበልባለ ንስሐን ብርሃንና ሙቀት ነፍሳተ ጽልመት መቋቋም አይችሉም፡፡ ስለዚህ በእሳቱ ላይ እስካለህ ድረስ (በመንፈሳዊ ተግባራት እስከጠነከርክ ድረስ) አንተ ሁሌም ከተባይና ከነፍሳት ብልሽት (ከአጋንንት) የራቅክ ነህ፡፡

ወዳጄ እባክህን ከእሳቱ ላይ አትውረድ፡፡ እሳቱ በደንብ ይነድ ዘንድ ጾም፣ ጸሎት፣ ስግደት የተባሉ እንጨቶችንና ምጽዋት የተባለ ጋዝን መጨመርህን እንዳትዘነጋ፡፡ እንዲህ ከሆነ ዘንዳ ድስትነት ሁሌም የሞቀ ይሆናል፡፡ እጅ እጅ ከማለት፣ ከመሻገትና የተባይ መጫወቻ ከመሆን ትድናለህ፡፡

ወዳጄ ሆይ እባክህን ከእሳቱ ላይ አይትውረድ፡፡

በኃጢአት "እጅ እጅ '' ከማለትና በበደል ከመሻገት እግዚአብሔር ይሠውረን! አሜን!

(ሕሊና በለጠ ዘኆኅተብርሃን)
76 viewsDagi Ararsa, 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ