የካዕባ ልብስ ኪስዋ በአዲሱ አመት መግቢያ ላይ ተቀየረ ስለካዕባ ልብስ ኪስዋ ትንሽ መረጃዎችን ላካፍላችሁ የካዕባ ልብስ ኪስዋ በየአመቱ የሚቀየር ሲሆን ከዚህ ቀደም በዙልሂጃ 9 ጠዋት ሀጃጆች ወደ አረፋ በተጓዙበት ወቅት ነበር የሚቀየረው:: አሁን ላይ ግን በአዲሱ አመት መግቢያ የመጀመሪያው ምሽት ሙሐረም 1 ላይ እንዲቀየር ተወስኗል:: የካእባ ልብስ ኪስዋ የአለማችን ውዱ ልብስ ነው:: የልብሱ ክብደት 850ኪ. ግ የሚመዝን ሲሆን አጠቃላይ የካዕባን ልብሱን ለማዘጋጀት የዘንድሮ ወጪው $6.5ሚሊዮን ዶላር ነው:: ይህ የካዕባ ልብስ በንጉስ አብዱልአዚዝ ኮምፕሌክስ የሚዘጋጅ ሲሆን ኪስዋውን ለማዘጋጀትም 200ባለሞያዎች ይሳተፉበታል:: በአለም ረጅሙ እና ኮምፒውተራይዝ የሆነው የስፌት ማሽን ይህን የካዕባን ልብስ ለማዘጋጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ሲሆን የስፌት ማሽኑም 16 ሜትር የሚረዝም ነው:: የከዕባ ልብሱ ኪስዋ 670 ኪሎ የሚሆነው ጥቁር ሀር ሲሆን በሀሩ ላይ ለሚፃፈው የቁርኣን አንቀፆችም 120 ኪሎ 21ካራት ወርቅ እና 100ኪሎ ብር አገልግሎት ላይ ይውላል:: በልብሱ ላይ የሚፃፈው የቁርዓን አንቀፆችም በሰዎች እጅ በጥንቃቄ የሚጠለፍ ነው: የዘንድሮ አመት 1444 የካእባ ልብስ ኪስዋ የመቀየር ስነ ስርዓትም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቀጥታ የቴሌቭዢን ስርጭት ተከታትለውታል @osmanethiopia @osmanethiopia 277 views04:36