Get Mystery Box with random crypto!

የ መልክተኛው ﷺ የሀጀቱል ወዳዕ (የመሰናበቻዋ ሀጅ ) ላይ ያስተላለፉት ውብ መልዕክት ሰዎች ሆ | Osman Ethiopia

የ መልክተኛው ﷺ የሀጀቱል ወዳዕ (የመሰናበቻዋ ሀጅ ) ላይ ያስተላለፉት ውብ መልዕክት

ሰዎች ሆይ ከዚህ አመት በኋላ ከመካከላቹ እንደገና መገኘቴን አላውቅምና ልብ ብሎ የሚያዳምጥ ጆሮዋቹን አውሱኝ።
ዛሬ የምነግራችሁን ቁም ነገር በጥሞና አዳምጡኝ በዚህች እለት ከመካከላቹ ላልተገኙም መልክቴን አድርሱ።

ሰዎች ሆይ !! የዛሬው ቀን ፤ይህ ከተማ የተቀደሱና የተከበሩ መሆናቸውን የምታውቁትን ያህል የያንዳንዱን ሙስሊም ህይወትና ንብረትን በክብር እንድቲዙ አደራ ተጥሎባቹሀል።

በእጃችሁ የሚገኙትን የአደራ እቃዎች ለባለቤቶቻቸው መልሱ ! ማንም ሰው እንዳይበድላቹ ማንንም አትበድሉ!

ያለምንም ጥርጥር ፈጣሪያቹ ዘንድ በግንባራቹ ተደፍታችሁ እንደምትቀርቡ አትዘንጉ።

የብድር ወለድ ተግባራችሁንም መክፈል ከንግዲህ ቡሀላ እርም ተደርጎባቹሀል።

ዲናቹን ለመንከባከብ ከ ሸይጧን ተጠንቀቁ!
በትልልቅ ጉዳዮች እናንተን አሳስቶ በዱንያ ላይ እናንተን አዘቅት ውስጥ ለመጣል የሚያደርገው ሙከራ ተስፋ ስላስቆረጠው በጥቃቅን ጉዳዮች ተከታዩ እንዳትሆኑ እራሳችሁን ጠብቁ።

ሰዎች ሆይ !!በሴቶቻቹሁ ላይ የተወሰነ መብት ያላቹ መሆኑ እርግጥ ነው... ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብት አላቸው! በናንተ ቁጥጥር እስካሉ ድረስ እነሱን መመገብ ፣ማልበስና በእዝነትና በርህራሄ የመያዝ ግዴታ ይኖርባቹሀል።

ሴቶቻቹ የኑሮ ጓደኞቻቹና የቅርብ ደጋፊያቹ ናቸው!በርህራሄና አግባብ ባለው መንገድ ተንከባከቧቸው። እናንተ ከማትፈልጉት ሰው ጋር ጓደኝነት እንዳይመሰርቱ ቤታቹ በጭራሽ እንዳይፈርስ ማድረግ ይኖርባቹሀል።

ሰዎች ሆይ !! በሚገባ አድምጡኝ አላህን ተገ፣ በቀን አምስት ጊዜ ሰላታቹን ስገዱ፣ የረመዳንንም ወር ፁሙ፣ ከንብረታቹም ዘካን ስጡለት፣ እንዲሁም ከተቻላቹ ሀጅንም አድርጉ።

እያንዳንዱ ሙስሊም ለሌላው ሙስሊም ወንድም መሆኑንን ታቃላቹ!? ሁላቹም እኩል ናችሁ።
ማንም ሰው ከሌላው ሚበልጥበት መንገድ የለም !!... አላህን መፍራትና በመልካም ተግባሩ ቢሆን እንጂ ።

አስታውሱ !! አንድ ቀን ጌታቹ ፊት ቀርባቹ ስለሰራቹት ስራ ትጠየቃላቹ! ስለዚህም ተጠንቀቁ እኔ ካለፍኩኝ ቡሃላ አላህን ከመፍራት ጎዳና እንዳታፈነግጡ ።

ሰዎች ሆይ !! ከኔ ቡሃላ አዲስ ነብይ አይመጣም!
አዲስ እምነትም አይወለድም!
በሚገባ እውቀትን ፈልጉ።

ህዝቦች ሆይ !! የማስተላልፈውን መልክት በትክክል ተረዱ። ከኋላዬ ሁለት ነገርን ቁርዓንንና ሱናን ትቼላቹ አልፋለው እሱን ከተከተላቹ ስህተት ላይ ከመውደቅ ትድናላቹ።

ያዳመጠኝ ሁሉ መልክቴን ላልሰሙት ያስተላልፍ!
እነርሱ ደሞ በተራቸው ለሌሎች ያዳርሱ።

የመጨረሻዎቹ አድማጮችም ከኔ አንደበት ከሰሙት ይልቅ ይበልጥ የሚገባቸው ይሁን።

አላህ ሆይ መልዕክትህን ለህዝቦቼ ማድረሴን ምስክሬ ሁን።
.
.
.
ይህንን መልክት ካስተላለፉ በኋላ ቀጣዩ አመት ሀጅ ከመድረሱ በፊት ታላቁ ተወዳጁ ነብይ እንደተመኙትም ወደ ጌታቸው እዝነት ሄዱ።
صلى الله عليه وسلم

ቢአቢ አንተ ወ ኡሚ ያረሱለላህ
ጁምዓ ጀሚል
ሰሉ ዓለይሂ አፍደሉ ሰላት