Get Mystery Box with random crypto!

#​​​​ጾመ ፍልሰታና ሥርዓቱ በዝግጅት ክፍሉ የተወደዳችሁ የድረ ገጻችን ተከታታዮች! በዚህ ዝግጅ | ዝማሬ ዳዊት ወ ማኅሌተ ያሬድ

#​​​​ጾመ ፍልሰታና ሥርዓቱ
በዝግጅት ክፍሉ

የተወደዳችሁ የድረ ገጻችን ተከታታዮች! በዚህ ዝግጅታችን ጾም ምንድን ነው? እንዴትና ለምን እንጾማለን? መጾም ምን ጥቅም ያስገኛል? ባንጾምስ ምን ጉዳት አለው? የሚሉ ጥያቄዎች በቤተ ክርስቲያን መምህራን ምላሽ እንዲያገኙ አድርገናል፡፡

በተጨማሪም ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ የኾነው የፍልሰታ ጾም በደመቀና በተለየ ኹኔታ የሚጾምበት ምክንያት ምን እንደ ኾነና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ይዘን ቀርበናል፡፡

ከምላሾቹ በኋላም ጾመ ፍልሰታን እንዴት ማክበር እንደሚገባን ለመዳሰስ ሞክረናል፡፡ መልካም ንባብ!

የጾም ትርጕም

‹‹ጾም›› ማለት ‹‹ጾመ – ተወ፤ ታቀበ፤ ታረመ፤›› ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ሲኾን የቃሉ ትርጕም ደግሞ ምግብ መተው፣ መከልከልና መጠበቅ ማለት ነው ሲሉ ዲያቆን ቃኘው ወልዴ በ፲፱፻፺፭ ዓ.ም ባዘጋጁት ‹‹ጾምና ምጽዋት›› በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ ፰ ላይ ገልጸውታል፡፡

የኪዳነ ወልድ ክፍሌ መዝገበ ቃላትም የሚያትተውም ይህንኑ ሐሳብ ነው፡፡ ጾም ጥሉላትን፣ መባልዕትን ፈጽሞ መተው፣ ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ እንደዚሁም ከሌላውም ክፉ ነገር ዅሉ መጠበቅ፣ መግዛት፣ መቈጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እርሱንም ደጅ መጥናት ማለት ነው፡፡

ሊቀ ማእምራን ደጉ ዓለም ካሣ እና ቀሲስ ስንታየሁ አባተ የሚሰጡት ማብራርያም ይህንኑ ትርጕም የሚያጠናክር ነው፡፡

በቀጣይ የጾም ስርዐቱ እና ጥቅሙን እንመለከታለን

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!

@mahibertsadikan
@mahibertsadikan
@mahibertsadikan