Get Mystery Box with random crypto!

ቅያሜው ይቅርና ቅያሜው ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን አንተ ስለራከን ሞት ነው የከበበን /2/ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ቅያሜው ይቅርና

ቅያሜው ይቅርና አምላክ ሆይ ታረቀን
አንተ ስለራከን ሞት ነው የከበበን /2/

እስከመቼ ድረስ ህዝብህ ተጎሳቁሎ
በረከሰ መንፈስ በርኩሰት ተጥሎ
ምድር እያለቀሰች ደም እየሸተታት
እባክህ አምላኬ ኢትዮጵያን ታረቃት
እባክህ አምላኬ ሀገሬን ታረቃት

የዘመኑ ጣዖት ገንዘብ እያሳተን
ይህ ደካማ ስጋ አምላክን አስተወን
ግብዝነት ሞልቶት ፈራሹ አካል
በነፍስ በሽታ ህዝባችን ታሟል /2/

ክንፋችን ተመትቶ መብረር አቅቶናል
በመንፈስ በሽታ ህዝባችን ታውኳል
ራዕይ የሌለው ተራ ሰው ስለሆን
እባክህ ጌታችን በፍጥነት ታረቀን /2/

ጸጋህ የተለየን ባዶነት የሞላን
ፍቅር የተነፈግን ሰላም የጎደለን
ሆነን ስለቀረን እግዚአብሔር ታረቀን
ጽድቅን አድለን ጽድቅ እንደተመኘን/2/

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur