Get Mystery Box with random crypto!

ወዴት ወድቆ ይሆን የበገና ዝማሬ እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

ወዴት ወድቆ ይሆን
የበገና ዝማሬ

እንክርዳድ ኑፋቄን ገበሬው ለይቶ
መልካም ዘር ሲዘራ ወደ ማሳው ወጥቶ
ለአጨዳው ምጽአት ለበጋው አዝመራ
ወዴት ወድቆ ይሆን ክረምት የተዘራ /2/

ዘወድቀ ውስተ ፍኖት ሲዘራ ያለቀው
አእዋፍ ሰማይ መሳጤ ነጠቀው
ዘወድቀ ዲበ ኮክሕ ጥልቅ አፈር ከሌለው
በደስታ እየሰማ በችግር የካደው
ዘወድቀ ውስተ ሦክ ተጨንቆ እንዳይወጣ
በዓለም ትካዜ በስፍጠተ ብዕል ታንቆ ፍሬ አጣ

ውስተ ምድር ሠናይ የወደቀም ነበር
ዘወሀበ ፍሬ ሰምቶ ሚተገብር
ጌታዬ ከአራቱ ስፍራዎች በምሳሌ ካልከው
ወዴት ወድቆ ይሆን ከእኔ ልብ የላከው
እባክህ ጎተራ አበጅተህ ለአጨዳ ስትመጣ
ከፍሬያማው ክምር ዕድል እንዳላጣ

ከእሾህ ከጭንጫ ላይ ከመንገድ እንዳልቀር
ልቤ ልብ አግኝቶ በምግባር እንዲኖር
ራሴን መስማት ትቼ ላንተ ፈቃድ ልደር

ዲ/ን ቀዳሜጸጋ
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur