Get Mystery Box with random crypto!

በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ. | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።

ዛሬ በነበረው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ የሕግ አማካሪዎች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚህም ሹመት የሰጡት በቀድሞ ስማቸው “አባ ኤዎስጣቴዎስ”፣ “አባ ዜና ማርቆስ”፣ “አባ ሳዊሮስ” እና እነርሱ በሕገ ወጥ መልኩ ሾመናችኋል ብለው ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጪ አስኬማ ያቀዳጇቸው 25 ግለሰቦች እንዲሁም አቶ ኃይለ ሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 156 መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ግቢ እንዳይገኙ በጊዜያዊነት አግዷቸዋል። ይህንን እግድ የተላለፈ ማንኛውም አካል የወንጀል ተጠያቂነት ይኖርበታል። በሀገሪቱ የሚገኙ የሕግ አስፈጻሚ አካላት እግዱን እንዲያስፈጽሙ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። ቤተ ክርስቲያኗ በቀጣይ በሰብአዊ መብት፣ በአስተዳደር፣ በወንጀልና በፍትሐ ብሔር ለደረሰው ኪሣራ ተጠያቂዎችን በመለየት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት በሕግ ትጠይቃለች።

በዚህም በሕገ ወጡ ሹመት ላይ የተሳተፉ የቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳትና ግለሰቦች ከዛሬ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት እንዳይገቡ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አግዷል።