Get Mystery Box with random crypto!

፮. በመግለጫው የመጨረሻ አንቀጽ ላይ '..ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ሀ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

፮. በመግለጫው የመጨረሻ አንቀጽ ላይ "..ችግሩን ለማባባስና በሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ሀገርን ወደፈተና ለማስገባት በሚጥሩ አካላት ላይ መንግሥት ሕግ የማስከበር ሥራውን እንደሚሠራ በዚሁ አጋጣሚ ያሳውቃል" በማለት ያስቀመጠውን በተመለከተ፡-

፮.፩. ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የበላይ አካል ከሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ አንስቶ እስከ ታችኛው የአስተዳደር መዋቅር አልፎም እስከ ተከታይ ምዕመኖቿ ድረስ የሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም የሕዝቧ አንድነት እና የሕግ የበላይነት ጉዳይ ለድርድር እንደማታቀርብ በድጋሚ እያስታወስን ስልጣንን ተገን በማድረግ የቤተ ክርስቲያንችንን ሕጋዊ ጥያቄ በግድያ፤ በእስር፤ በማዋከብ እና በማስፈራራት ሊፈታ የማይችል ይልቁንም መንግሥት የተጣለበትን መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለ አድሎ መፈጸም ሲችል ብቻ መሆኑን ቤተ ክርስቲያናችን ዳግም በጽኑ ቃል ለማሳሰብ ትወዳለች፡፡

በመጨረሻም መንግሥት ይህንን መግለጫ ሲያወጣ በጥር ፳፯ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑን ስንመለከት የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል።

ስለሆነም መንግሥት ሕገ ወጥ አካላትን ድጋፍ ከመስጠት እና የእነርሱ ልሳን ሆኖ በመቅረብ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልእልና ከሚያንኳስስ ሕገ ወጥ ድርጊት እንዲታቀብ እያሳሰብን ሕገ ወጡ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊትም የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ እንዲያቆም እናሳስባለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምንጭ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ