Get Mystery Box with random crypto!

​​#አትንኩን ✞ አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል(፪) የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን( | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

​​#አትንኩን ✞

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል(፪)
የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን(፪

ጥቂቶች ሆነን ተነስተን ነው
እንዲሁ ምድርን የመላነው
ልጣል ከውሃ ከእሳት
ጽኑ ነው የያዝነው እምነት

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል(፪)
የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን(፪)

ድሆች ስንባል ባለጸጋ
ሁሉን የያዘ ነው ከእኛ ጋ
ብርቱውን ጎልያድ የጣለ
በወንጭፋችን ጠጠር አለ

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የክርስቶስ ሰምራ የአርሴማ ልጆች ነን

በሕይወት በቃል አስተማረን
አምላካችን ነው የነገረን
የዚህ ዓለም ጨው ተብለናል
አልጫውንም አጣፍጠናል

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የቅዱስ መርቆሬዎስ የማርቆስ ልጆች ነን

እንደ ደመና የከበቡን
የእግዚአብሔርን ቃል የነገሩን
ስላሉን ብዙ ምስክሮች
ደካሞች ሲሉን ነን ኃይለኞች

አትንኩን ስትነኩን ቁጥራችን ይበዛል
የቅዱስ ጊዮርጊስ የጳውሎስ ልጆች ነን
የተክለሃይማኖት የጴጥሮስ ልጆች ነን

ቤተክርቲያን እማማ
ዝናሽ በዓለም ይሰማ

"እስካረጅም እስክሸመግልም ድረስ
ለሚመጣ ትውልድም ሁሉ ክንድህን
ኃይልህንም ጽድቅህንም እስክነግር
ድረስ አቤቱ አትተወኝ"

ሊቀ መዘምራን ዲያቆን
ቴዎድሮስ ዮሴፍ

"አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር"
ሐዋ ፲፮፥፭

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur