Get Mystery Box with random crypto!

' በዚህ ሕገ ወጥ ሂደት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የተከበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥቃትና፣ | ዝማሬ ዳዊት - Zimare Dawit

" በዚህ ሕገ ወጥ ሂደት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የተከበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥቃትና፣ የባህልና የሃይማኖት ቅርሶችን ስርቆትና ዘረፋን ለመከላከል ኃላፊነት ያለበት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የሚመራው መንግሥት ነው"
የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኀበራት ምክር ቤት

የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለሁለት ለመክፈል ታስቦ በሕገ ወጥ መንገድ ቀኖና ሳይጠብቅ የተከናወነውን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት በመቃወም መግለጫ አውጥቷል።

የሰሜን አሜሪካን የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤት የተሞከረውን መፈንቅለ ሲኖዶስ በጽኑ በማውገዝ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ በአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ከሚመራው ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አጋርነታችንን እናረጋግጣለን ብሏል መግለጫው።

በተጨማሪም የሲቪክ ማኅበራት ምክር ቤቱ በዚህ ሕገ ወጥ ሂደት የሰው ሕይወት መጥፋት፣ የተከበሩ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ጥቃትና፣ የባህልና የሃይማኖት ቅርሶችን ስርቆትና ዘረፋን ለመከላከል ኃላፊነት ያለበት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሚመራው መንግሥት መሆኑን አስታውሶ። ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና ለዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ በዚህ ፈታኝ ጊዜ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚቆም በመግለጫው ጠቅሷል። መረጃው የኢኦተቤ ቴቪ ነው፡፡