Get Mystery Box with random crypto!

ተዋህዶ መልስ ናት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxe19 — ተዋህዶ መልስ ናት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodoxe19 — ተዋህዶ መልስ ናት
የሰርጥ አድራሻ: @ortodoxe19
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.64K
የሰርጥ መግለጫ

✟✟✟ በዚህ ቻናል የመናፍቃንን እና የአህዛብን ጥያቄ እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ መልስ እንሰጣለን✟✟✟
ለሌሎች ሼር በማድረግ እውነቱን ለሁሉም እናድርስ ተዋህዶ መልስ ናት 🔊🔊🔊
@Ortodoxe19
የተሰወረውን ሁሉ የሚያቅ ባሕረ ጥበባት ልዑል እግዚአብሔር ጥበቡንና ማስተዋሉን ይግለጽልን!!!
በዚህ ቻናል እንዲመለስ ምፈልጉትን ጥያቄና አስተያየት በዚ ላኩልን @Eyasues በዚህ ላኩልን

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-12 19:30:09 " አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጉም የለም፡፡"

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዐሠርቱ ወአምስቱ ዓመተ ምሕረት፡-
ጷጉሜን ፬ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
-በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
-ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣
-የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
-በሕመም ምክንት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
-እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤት የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵውያት በሙሉ!
የዓመታትና የአዝማናት ባለቤት የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለአዲሱ ዓመት ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት ዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችሁ !!

“ወዓመቲከኒ ለትውልደ ትውልድ፣ ዓመቶችህ ለልጅ ልጅ ናቸው” (መዝ. ፻፩፥፳፬)፡፡

ይህንን ቃለ እግዚአብሔር የተናገረው እግዚአብሔር በቅብእ ቅዱስ አማካኝነት ሀብተ ትንቢት ወመዝሙር ያሳደረበት ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ነው፤ የቃሉ መሠረተ ሐሳብም ዓመታት የእግዚአብሔር ስጦታ መሆናቸውን፣ እንደዚሁም የተሰጡት ለሰው ልጆች መሆናቸውን ይገልፃል፡፡ በእርግጥም ዓመታት ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተሰጡ ሀብቶች ናቸው፤ ዓመታት፣ ወራት፣ ዕለታት፣ ቀናት፣ ሰዓታት የሚያስፈልጉት ለሰው ልጅ እንጂ ለእግዚአብሔርና በመንፈሳዊ ዓለም ለሚገኙ ፍጡራን አይደለም፤ ምክንያቱም ሰው በደካማው ዓለም የሚኖር ደካማ ፍጡር ስለሆነ ለኑሮው ጊዜያት የግድ ያስፈልጉታል፤ በመንፈሳዊ ዓለም የሚገኙ ፍጡራን ግን፣ ድካም የሌለባቸው ትጉሃን ስለሆኑ፣ ዓመትም ቀንም ሰዓትም ወዘተ አያስፈልጋቸውም፤ የሰዓት መለኪያ ብርሃንም የላቸውም፤ ምክንያቱም ያሉበት ዓለም ሁሌም ብርሃን እንጂ ጨለማ ስለማይፈራረቀው፣ እንደዚሁም ተለዋዋጭ አየርም ሆነ ዕድሜ ስለሌላቸው ማለት ነው፤ ለሰው ግን የጊዜ መለኪያ የሚሆኑ ብርሃናትና አዝማናት ወዘተ የተመደቡለት ስለሆነ፣ በእነሱ እየተመራ ጊዜያትን ይለካል፤ ዓመታትን ወራትንና ቀናትን ወዘተ ይቈጥራል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡-

ዓመታት ከእግዚአብሔር ለእኛ የተሰጡን ያለምክንያት አይደለም፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ሁሉ ክብርም ጥቅምም አለውና ልናከብረውና ልንጠቀምበት እንጂ፤ ሁላችንም እንደምንገነዘበው ጊዜ ትልቁና ቀዳሚው የሥራ መሣሪያ ነው፡፡ እህልን ዘርተን የዓመት ምግባችንን የምናገኘው ወርኃ ክረምት ስለተሰጠን ነው፤ ይህ ወቅት ባይኖር ኖሮ የእርሻ ሥራ ሠርተን ራሳችንን መመገብ እንደማንችል የምንስተው አይሆንም፡፡ ከዚህ አንጻር ዓመታትንና ወቅቶችን እንደ አመቺነታቸው እየተጠቀምን ልንሠራባቸው እግዚአብሔር አመቻችቶ ሰጥቶናል ማለት ነው፤ ስለዚህ በብሂለ አበው “ጊዜ ሳለ ሩጥ ….” እንደሚባለው ሁሉንም በጊዜው ጊዜ መሥራትና ተጠቃሚ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሰውም ሆነ ጊዜ ለሥራ የተፈጠሩበት ምክንያት መክበርም መዳንም ማግኘትም ማደግም መልማትም በሥራና በሥራ ብቻ የሚገኝ ከመሆኑ የተነሣ እንደሆነ ለጥያቄ የሚቀርብ አይደለም፤ “ብላዕ በሐፈ ገጽከ፤ በፊትህ ላብ እንጀራህን ብላ” የሚለው አምላካዊ ትእዛዝም ይህንን ይገልጻል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፡-

እግዚአብሔር አምላክ ያለመታከት ሠርተን ራሳችንን በራሳችን የምናስተዳድርባት በሀብትና በጊዜ የተዋበች ምድር አስረክቦናል፤ ምድሪቱንም ለእኛ በሚመች አኳኋን አበጅተን እንድንጠቀምባት የሚያስችል አእምሮና ጉልበትም ከጤና ጋር ሰጥቶናል፤ ሐቁ ይህ ከሆነ ታድያ ለምንድን ነው በምድራችን ስጋትና ጭንቀት፤ ረኃብና እርዛት፣ የሀብት እጥረትና የእርስ በርስ ግጭት በስፋት የሚታየው የሚለውን ጥያቄ ሰው ሁሉ በጥልቀት ሊያጤነው ይገባል፡፡ እግዚአብሔር የሰጠን ምድር አሁንም ለፍጡራን የሚበቃ የተትረፈረፈ ሀብት ያለጥርጥር አላት፣ የአጠቃቀም ጉዳይ ካልሆነ በቀር ሀብት የሌለው የምድር አካባቢ ፈጽሞ የለም፡፡ ይህም ከሆነ ሁሉም ወደሥራና ሥራ ብቻ ተሠማርቶ ጥረቱን ከቀጠለ የሚያጣው ነገር የለም ማለት ነው፣ ሰው ጤና ዕውቀትና ሰላም ካለው ሀብታም ነው፤ ምክንያቱም እነዚህ ከተሟሉለት ሌላው ሁሉ እግዚአብሔር ከሰጠው ምድር ሠርቶ የሚያገኘው ነው፡፡ ሰላም ከሌለ ግን ነገሩ ሁሉ ጨለማ ይሆንበታል፤ አካላዊና አእምሮአዊ ጤናውም ይደፈርስና ሳያጣ ያጣ ወደ መሆን ይቀየራል፡፡ ዛሬ በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን እየተከሠተ ያለው ሐቅ ይኸው ነው፡፡

ይህ የሰላም እጦት በሀገራችን በኢትዮጵያ በርከት ላሉ ዓመታት እየተደጋገመ በመከሠቱ፣ በዚህ ጠንቅ ሕዝባችን ሳያጣ ያጣ ሆኖአል፤ ኢትዮጵያን በመሰለች ለምና ምድራዊት ገነት ተቀምጠን፣ በዓለም ውስጥ የድህነት ተምሳሌት ሆነን መገኘታችን፣ የሁላችንም ኅሊና ሊኰረኲረው ይገባል፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት

በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን ሁሉ በአጽንዖት የምንመክረው ዓቢይ ምክር በግጭት ችግሮቻችንን መፍታት በፍጹም አንችልም፤ በመራራቅም ማደግ አንችልም፤ በተለያየን ቊጥር ድህነታችንን ከማስቀጠልና ደካሞች ከመሆን በቀር የምናገኘው አንዳች ፋይዳ የለም፤ እውነቱ ይህ ከሆነ ከገባንበት ያላስፈላጊ ግጭት በፍጥነት ወጥተን ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት ወደሚያስችል ወደ ምክክርና ውይይት እንግባ፤ አዲሱ ዓመት እውነተኛ አዲስ ዓመት ሊሆን የሚችለው ይህንን ያደረግን እንደሆነ ነው፡፡ አሮጌውን አስተሳሰብ እንዳለ ተሸክመን ለመቀጠል እየዳዳን ከሆነ አዲስ ዓመት ማለቱ የአፍና የጆሮ ቀለብ ከመሆን በቀር የሚሰጠን አንዳች ትርጉም የለም፡፡ ስለሆነም አዲሱን ዓመት አዲስ የሆነ የሰላምና የዕርቅ የስምምነትና የአንድነት የይቅርታና የምሕረት የፍትሕና የእኩልነት መርሕ አንግበን ፍጹም ሰላምን ለማንገሥ በቊርጥ ማሰብና መነሣሣት አለብን፣ ይህንንም ለማሳካት በአንድ አዳራሽ፣ በአንድ ጠረጴዛ ተገናኝተን ችግሮቻችንን በውይይትና በምክክር እንድንፈታ በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

በመጨረሻም

አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የበረከት የዕድገት የሃይማኖትና የልማት ዓመት እንዲሆንልን ወደ እግዚአብሔር በመጸለይና በብሩህ ተስፋ እንድንቀበለው መልእክታችንን በድጋሚ በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር መልካም አዲስ ዓመት ያድርግልን !
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ !!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን !!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
መስከረም ፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓመተ ምሕረት
አዲስ አበባ  ኢትዮጵያ፡፡
450 views✟Mentesenhot✟, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:46:29
እንካን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አዲስ አመት በሰላም በፍቅር በጤና በእምነት በተስፋ አደረሳችሁ አደረሰን
@Ortodoxe19
(መዝሙረ ዳዊት ምዕ. 65)
----------
11፤ በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።

12፤ የምድረ በዳ ተራሮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።

እግዚአብሔር አምላካችን እድሜን ለንስሀ ሰቶን በቸርነቱ በምህረቱ አዲስ አመትን ተጨማሪ እድሜን ሰቶን ለዚ ስላደረሰን ስሙ የተመሰገነ ይሁን
አዲሱን አመት በአዲስ ልብ በአዲስ መንፈስ በአዲስ ሕሊና በአዲስ ማንነት በአዲስ ሰውነት እንድንቀበለው እና ንስሀ ገብተን ቅዱስ ስጋውን ክቡር ደሙን የምንቀበልበት ወደ ሚስጥሩ የምንጠጋበት የስም ሳይሆን የተግባር ክርስትያን የምንሆንበት ከክፋት ከተንኮል የምንርቅበት እግዚአብሔርን መበደል ማሳዘን የምንተውበት የንባብ ልምዳችንን በበለጠ የምናጠነክርበት የስኬት የደስታ የፍቅር የጤና የተቀደሰ የተባረከ አመት ይሆንልን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።
" የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 4:3

#ያለፈው #ዘመን #ይበቃናል


ዘመን ተሰጠን ለምስጋና ዘመን ተሰጠን ለውዳሴ ተመስገን ሥላሴ


ምንተስኖት


@Ortodixe19
339 views✟Mentesenhot✟, 18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:26:01 እንኳን አደረሳችሁ!!!

እኔስ ምን ልተውልህ?

ጴጥሮስ መረቡን ተወልህ: ማቴዎስም ቀረጡን በርተሎሜዎስም ግብርናውን ሌላውም ሽመናውን ተዉልህ እኔስ ምን ልተውልህ? ምን ልጣልልህ?

ኒቆዲሞስ ትዕቢቱን ሳምራዊቷም እንስራዋን ዘኬዎስም ዛፉን ማርያም ዘናይን ዝሙቷን ተዉልህ እኔ ባሪያህ ምን እተውልህ ይሆን? ከኔ የሚጣልና የሚወድቅ ሀጢአት እጅግ ብዙ ነው ቤቴ የከረፋ በደለኛ ልጅህ ምን እጥልልህ ይሆን?

ሰኞ ያጣኸኝ በለስ ፤ አርብ የቀረሁ ሐዋርያ፤ የሸጥኩህ ይሁዳ፤ መቅደስህ ሲቃጠል ዝም ያልኩ ጲላጦስ ፤ አላቅህም ያልኩ ጴጥሮስ፤ ቁስሌ ሳይደርቅ የረገጥኩህ መጻጉዕ እኔ ነኝ!

ጌታዬ ሆይ ቅጠል ብቻ የሆንኩ ፍሬ አልባ ሆንኩብህ! በሞትህ ቀን ያጣኸኝ ሐዋርያ እኔው ነኝ ፤ ቤ/ክ መከራ ሲደርስባት ዘብ ያልቆምኩላት እኔ ነኝ! ሰኞ ፍሬ ያጣህብኝ ምግባር አልባው ደንዳናው ልጅህ እኔ ነኝ

ቤቴ እንደሆን ከጣሪያው የማያስገባህ ላንተ የማይገባ አደፍ ቤት ለዘመናት የተዘጋ ቤት ድር እንደሚበዛው ልቤም አንተን አጥቶ ሀጢአት ደርቶበታል ...እናም ሁሉን ክፋት ጥዬ ልከተልህ በዕውቀት ሳይሆን በሕይወት ልከተልህ ስለ አንተ ሳይሆን አንተን ልወቅህ ልቅረብህና ሰው አርገኝ ......ብቻ ካንተ ያለያዩኝን ስንፍናን፤ ተንኮልን፤ክፋትን፤ግዜ ማባከንን፤ወገንተኝነትን፤አለመከባበርን ፤አለመተሳሰብን፤ ትርፍ የሌለውን ከንቱ ተግባርን ልጣልና ልከተልህ።

ስንት ጊዜ ልትፈልገኝ መጣህ? መቼ በቀንህ ተገኘሁ? ስትቀርበኝ የራቅኩ ስትፈልገኝ የጠፋሁ ሽፍታ እኔ ነኝ! በጾሙ ወራት በሕማሙ ሳምንት ማን ነኝ? በእኔ ውስጥ አንተን መስክሬ ይሆን? የታጣሁ ፍሬ ልጅህ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ

ከቤ/ክንህ መከራ ሳልሳተፍ ከሀገሬ ቁስል ሳልጋራ ለነፍሴ ሳልተጋ ዓመታት ተቆጠሩ ዘንድሮም ከቁጥር ደረስኩ እስከ አሁን የታገስከኝ ይቺን ዓመት ተወኝ፡፡


ጥላዬ ግብሩ
የ2015 ዋዜማ
@ ሐረር

@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
@Ortodoxe19
321 views✟Mentesenhot✟, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 19:46:40
@Ortodoxe19
420 views✟Mentesenhot✟, 16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:15:10 + ዝም ብለን የምንጠላው ሰው +

ከሩቅ የምናውቀው አንዳንድ ሰው የለም? ብዙም አናውቀውም:: ቀርበን አውርተነው አናውቅም:: ስናየው ግን እንዲሁ ደስ የማይለንና ያለ ምክንያት የምንጠላው ሰው የለም?

"እሱን ሰውዬ ጥሎብኝ አልወደውም"

"አይ እሱን ልጅ ቀልቤ ትከሻዬ አልወደደውም"

"እኔ እንጃ ለምን እንደሆነ ባላውቅም አልወዳትም:: ምክንያቴን አትጠይቀኝ ግን በቃ እንዲሁ አልወዳትም"

ምንም ምክንያት ሳይኖረን እንዲሁ የምንጠላው ሰው አለ::

እግዚአብሔር ግን
"አንድያ ልጁን እስኪሠጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአል" (ዮሐ 3:16)

ጠላቶቹ ሳለን በልጁ ሞት አዳነን እንደሚል እርሱ እኛን ለመጥላት ብዙ ምክንያት ነበረው:: እርሱ ግን እንዲሁ ወደደን:: ከእኛ ምንም ባያገኝም ስለ እኛ ያለው ፍቅር የእንዲሁ ፍቅር (unconditional love) ነበረ:: እርሱ እንዲሁ ወዶናል እኛ ግን እንዲሁ ሰው እንጠላለን::
ያለ ምክንያት መውደድ ቢያቅተን እንኳን ያለ ምክንያት መጥላታችን (unconditional hate) ቢቀር ምናለ?
የሚያሳዝነው ያለ ምክንያት የጠላናቸውን ሰዎች የበለጠ ለመጥላት በልባችን እስር ቤት ውስጥ በጥላቻ ሰንሰለት እናስራቸውና የበለጠ ለመጥላት ስለእነርሱ ክፉ ክፉ ማስረጃ ለመስማት እንተጋለን:: ጥሩ ነገራቸውን ለመስማት አንፈልግም:: ክፉ ስንሰማ ግን "እኮ እኔ እኮ ዝም ብሎ ትከሻዬ ይነግረኝ ነበር" ብለን በደስታ እንፈነድቃለን:: እንዲሁ የጠላነውን ሰው በምክንያት ለመጥላት በመቻላችን ደስ ይለናል::

እኛ ሰውን ለመጥላት ምክንያት የምንፈልገውን ያህል እንዲሁ የወደደን እግዚአብሔር ግን እኛን ለመማር ሰበብ ይፈልጋል:: ትንሽ በጎነት ቅንጣት ቅንነት ሲያገኝ እጅግ ይደሰታል:: ባለቅኔው "እግዚአብሔር መንግሥቱን በርካሽ ዋጋ ሸጠው:: በቀዝቃዛ ውኃ በዘለላ ዕንባ እና ማረኝ በሚል የወንበዴ ጩኸት!" እንዳሉት እሱ እኛን ይቅር ለማለት የሚታይ በጎነት ቢያጣ ልባችን ውስጥ ገብቶ ትንሽ መጸጸት ካለ ይፈልጋል:: እንዲሁ ወዶናልና እንዲሁ ሊተወን አይፈልግም::

"እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳን በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሠጠን"
ኤፌ 2:4

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
379 views✟Mentesenhot✟, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:14:17
#ማቴዎስ 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
¹⁴ ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።
@linkortodoxe21
269 views✟Mentesenhot✟, 19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:13:04 "እገድልሐለሁ ያልከኝ እውነትም ገደልከኝ።"

.በአንድ ወቅት ከቤ/ክን አገልጋይ ከነበረ ሰባኪ ሲመሰከር ከሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ላካፍላችሁ። አንድ እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያገለግል ዲያቆን
ነበር። የዚህ ዲያቆን ጎረቤት የሆነ ሠውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ይህን ዲያቆን በጣም ጠምዶ ይዞት ነበር። በመንገድ ላይ ባገኘው ቁጥር በጣም አስጸያፊ ስድብ ከመስደብ ጀምሮ ቆሻሻ ውሐ በላዩ ላይ እስከመድፋት እንዲሁም ካልደበደብኩት እያለ በገላጋይ ነበር የሚለመነው ዲያቆኑ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን "እግዚአብሔር ይባርክህ ያስብህ" ከማለት ውጪ ምንም የክፋት ቃል ከአንደበቱ አይወጣም ነበር። ከእለታት በአንዱ ቀን ግን ዲያቆኑ ምርር ብሎት ሠውየውን "እገድልሐለሁ።" ብሎት ይሄዳል። ሠውየውም ይሄ ዲያቆን እገድልሐለሁ ያለኝ ምን ገዝቶ ነው ቦንብ ነው? ሽጉጥ ነው? ዱርየ ነው? በማለት መጨናነቅ ይጀምራል።

. ከእለታት በአንዱ ቀን ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ ዲያቆኑ ከቅዳሴ ወጥቶ ወደ መኖሪያ ቤቱ ሲሔድ መንገድ ላይ ሕዝብ ተሰብስቦ ያያል። ጠጋ ብሎ ምን እንደተፈጠረ ይጠይቃል። ሠዎቹም አንድ ተሽከርካሪ አንድ ሕጻን ልጅ
ገጭቶ እንዳመለጠ ይነግሩታል። ጠጋ ብሎ ሲያይም የተገጨው የዚያ እርሱን የሚሰድበውና የሚያዋርደው
ሠውየ ልጅ መሆኑን ይረዳል። በኋላም ልጁን ከነደሙ ይሸከምና ኮንትራት ታክሲ ጠርቶ ልጁን ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ይወስድና ያሳክመዋል። የልጁ አባትም ሥራ ቦታ ነበርና ልጁ ተገጭቶ ወደ
ዘውዲቱ ሆስፒታል መወሰዱ ተደውሎ ይነገረዋል። ሠውየውም ዘውዲቱ ሆስፒታል ሔዶ ልጁ የተኛበት ክፍል
ሲገባ ልጁ ጉሉኮስ ተሰክቶበት ተኝቶ አጠገቡ ደግሞ ያ አልወደውም ጠላቴ እያለ የሚሰድበው ዲያቆን ? ሲያስታምመው ያያል። በአካባቢው የነበሩ ጎረቤቶቹም ልጁ በመኪና እንደተገጨና ያ ጠላቴ የሚለው ዲያቆን
አምጥቶ እያሳከመው እንደሆነና እሱ ባያሳክመው ልጁ ሊሞት ይችል እንደነበር ነገሩት። ሠውየውም ዲያቆኑን ጠርቶ "እገድልሐለሁ ያልከኝ
እውነትም ገደልከኝ። አሁን ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? " ሲለው
ዲያቆኑም "እኔ ምንም አልፈልግም ከነ ቤተሰቦችህ ንስሐ ግባ ሥጋ ወደሙ ተቀበል። እኔ የምመኝልህ ይህን ብቻ
ነው።" ብሎ አለው።

.በኋላም ዲያቆኑን የሚያውቁት ሰዎች "ለመሆኑ ሠውየዉን እገድልሐለሁ ያልከው ለምንድን ነው? " ብለው
ሲጠይቁት ዲያቆኑም "እኔ እኮ እገድልሐለሁ ያልኩት ሠውየውን
አይደለም እኔ እገድልሐለሁ ያልኩት በሰውየው ላይ አድሮ የሚረብሸኝን ዲያብሎስን ነው። እግዚአብሔርም
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያትና ጥበብ እንዲሰጠኝ ስጸልይ ነበር። ልጁ የተገጨውም እግዚአብሔር ለእኔ
ዲያብሎስን መግደያ ምክንያት ሊሰጠኝ ነው። እኔም የሰጠኝን ምክንያት ተጠቀምኩና እንደዛትኩት ዲያብሎስን
ገደልኩት።" ብሎ አላቸው። ግሩምና በጣም ጣፋጭ ትምህርት ነው። እኔ እራሴን ታዘብኩት እናንተስ? ከዲያቆኑ ምን ተማራችሁ?

(ይሄን ፁሑፍ የትም ልታነቡት ትችላላችሁ ዋናው አንብባችሁ መማር መቻላችሁ ነው)
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
246 views✟Mentesenhot✟, 19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-05 22:12:31 ልብህ ሞልቷል

አንድ ወጣት ወደ አንድ መነኩሴ ዘንድ ይሄድና ክርስትናን ማወቅ እፈልጋለው ስለ ክርስትና ንገሩኝ አላቸው ። ና ልጄ ውስጥ ሻይ እየጠጣን እናውራ ብለው ወደ ባዕታቸው ይዘውት ገቡ ።ከዛ ማንቆርቆሪያቸውን ጥደው ሻዩ እስኪፈላ መጠበቅ ጀመሩ ። ልጁም በሚገርም የወሬ ፍጥነት አባ ክርስትና እንዲ ነው አይደል ፡አባ ክርስትና እንደዛ ነው አይደል ? ሰዎች እኮ ነግረውኛል እያለ ከሰዎች የሰማውን ይቀባጥራል

መነኩሴውም ዝም ብለው ሲሰሙት ቆዩና ሻዩ ሲፈላ ብርጭቆ አምጥተው ይቀዱለት ጀመረ ። ብርጭቆው ሞልቶ እየፈሰሰም ዝም ብለው ይቀዳሉ ። ከዛ ልጁም አንተ መነኩሴ ያምሀል እንዴ ? ብርጭቆውኮ ሞልቷል ። አንተ ለምትጨምርበት ሻይ ቦታ የለውም አላቸው ። መነኩሴውም አየህ ልጄ አንተም እንደዚ ብርጭቆ ነህ ። ስለ ክርስትና ማወቅ ትፈልጋለህ ነገር ግን ልብህ ሌሎች በነገሩህ አሉባልታ ተሞልቷል እኔ የምነግርህን ነገር የምትቀበልበት ቦታ በልብህ ውስጥ የለም

ብነግርህም ታፈሰዋለህ ። ስለዚህ አሁን ሂድ ልብህ ባዶ ሲሆን ተመልሰህ ና ያኔ እነግርሃለው አሉት። እኛስ ዛሬ ልባችንን የሞላው ምንድነው ? ፍቅር ? ሰላም ? መቻቻል ? ታምኝነት ፣ ህብረት አንድነት ነው ወይስ አስቀድሞ ልባችን በተንኮል ፣ በሟርት ፣ በቅናት፣በሴሰኝነት ፣ በዘረኝነትና በጎጠኝነት ስለተሞላ ለመልካም ነገሮች ቦታ የለውም ? እስቲ እራሳችንን እንፈትሽ ልባችንን ሞልቶት እየፈሰሰ ያለው ምንድነው ?

@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
@linkortodoxe21
232 views✟Mentesenhot✟, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 20:10:08
@Ortodoxe19
264 views✟Mentesenhot✟, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-04 20:06:49
@Ortodoxe19
261 views✟Mentesenhot✟, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ