Get Mystery Box with random crypto!

✝️ቅዱስ ኤልሻዳይ✝️አምላክ እልመክኑን✝️

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_utopia — ✝️ቅዱስ ኤልሻዳይ✝️አምላክ እልመክኑን✝️
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_utopia — ✝️ቅዱስ ኤልሻዳይ✝️አምላክ እልመክኑን✝️
የሰርጥ አድራሻ: @ortodox_utopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 446
የሰርጥ መግለጫ

#ክብርና_ምስጋና_አምልኮትና_ዉዳሴ_ለአጋእዝተ_አለም_ሥሉስ_ቅዱስ_ይሁን✝️
#አንድ_ጌታ ፣ #አንድ_ሃይማኖት ፣ #አንዲት_ጥምቀት #ኤፌ 4፥5
#ንቁ_በሃይማኖት_ቁሙ_ጎልምሱ_ጠንክሩ (1ኛ ቆሮንቶስ 16፥13)
በዚህ ቻናል የተለያዩ #የአባቶች_አስተምህሮ_እና_መንፈሳዊ_እይታ፣ #መንፈሳዊ_መጻሕፍት_መንፈሳዊ_መዝሙራት፣ #የቅዱሳን_ታሪክ_በጽሁፍ እና በፊልም እንዲሁም ሌሎች አስተማሬ ጽሁፎችን ታገኛላችሁ✝️

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-23 21:32:23 #ወደ_ላይ_መመልከትን_ልመድ

❖ አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ እየገባ ይሰርቃል ።

አንድ ቀን የግቢው ባለቤት ሲመራቸው ግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል።

ቀስ ብሎ ገብቶ ሌባው ዛፉ ስር ቆመ ፤ ከዛ ሌባው ዛፉ ስር እንደቆመ ቅኝት ይጀምራል ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ። ከዛም እንደለመደው ሊገባ ሲል ..ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት መታው ወደቀች ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ ሲመለከት ከቤቱ ባለቤት ጋርም ተፋጠጠ።

የቤቱ ባለቤትም፦ “ይህን ያደረኩት ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰዉ እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ ፈጠረን ወደ እግዚአብሔርም ወደ ላይም ማየት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።

#መልዕክት

እኛስ ህሊናችን ለመጥፎ ሀሳቦችና ሙያን ተገን አድርገው ለሚፈፀሙ ስርቆቶች ሲነሳ ፣ በተማርነው ሙያ ማገልገል አቅቶን የንፁሃን እንባ ሲበዛና ብዙዎችም ለርሃብ እና ማቆሚያ ለሌለው እንግልት ሲዳረጉ ፣ በእኛ አገልግሎት ብዙዎችን ስናሳዝንና ለሌሎቹም ለመውደቃቸው ምክንያት ስንሆን ፣ እጆቻችን የንፁኃንን ደም ለማፍሰስና የእኛ ያልሆነውን የሰዎችን የድካም ውጤት ለመዝረፍ ና ደካሞችንም ለማሳዘን ሲዘጋጁ ፣ እግሮቻችን ወደ ጣኦት ቤት ፣ ወደ ዳንስና ጭፈራ ቤቶች ፣ ወደ ዝሙት ቤት ወደ ሌላም ሌላም የርኩሰት ቦታዎች ሲገሰግሱ ፣ ጆሮዎቻችን ወደ ሀሜት ሲያዘነብሉ ፣ አይናችን የእኛ ያልሆነውንና ያልተፈቀደልንን ነገር ማየትና መመኘት ሲጀምር ፣ ይህ ነገ ፈራሽና በስባሽ የሆነው ገላችን በውበቱ መመካት ሲጀምርና የረከሰውን የርኩሰት ስራ ሲፈፅም ወደማን እንመልከት ????

የአንዳንዶቻችን ህይወት አብሮን የሚኖረው ባለእንጀራችን ሊያየን የማይችልበት ጊዜና ቦታ ወቅት እንዲሁም ጨለማ እስኪመጣ ድረስ በመጠበቅ ፀሀይዋ ስትወጣ (በምቾት እስካለን ድረስ) መልካም ጨዋዎች በሰዎች ዘንድም ፃድቅ እንመስልና የሚታይና የማይታየውን ፍጥረታት ፈጥሮ ከጥልቁ ከበርባሮስ እስከ ጽርሐ አርያም ድረስ በመንግስቱ ከብሮ ያለና የሚኖር ፀሀይን በቀን ጨረቃና ከዋክብትን በሌሊት ያሰለጠናቸው በእርሱ ዘንድ የቀንና የሌሊት መፈራረቅ የሌለበት ቅዱስ እግዚአብሔር የማያይ ይመስል ምሽት ሲመጣ (ፈተና ሲመጣ ማዕበል ሲነሳ) ከእስራቱ እንደተፈታና ከእናቱ ለመገናኘት እንደቸኮለ እንቦሳ ጥጃ ወደ ርኩሰት ግብር እንፋጠናለን ።

ግን ለምን ??? እስከመቼስ እንዲህ እንቀጥላለን ???


✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
1.4K viewsedited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 10:08:36 +++ የመነኩሴው ፈሊጥ +++


መጾም ያቃተውን ሰው ጹም፣ መመጽወት የተሳነውን መጽውት፣ መራመድ የማይችለውን ሩጥ የሚሉ መካሪዎች ብዙ ናቸው፡፡ መራመድ የማይችል እንዴት መሮጥ እንዳለበት ከማሳየት ይልቅ ቀንበር ማክበድ ጠባያችን ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳየው ቃሉ እንጂ ተግባሩ የተለየን መሆኑን ነው፡፡ በተግባር መግለጥ ብንችል ኖሮ፣ ማገዝ ቢያቅተን እናሯሩጠውና ሰውነቱ ሞቆ ተጋድሎ ሲጀምር እናፈገፍግ ነበር፡፡ እኛ ግን ልምድ የሌለውን ሁሉ ተሸከም ማለት ይቀለናል፡፡

ከባለ ግመሉ ከአባ ቆሪር ምክር ለመመጽወት የሄደ ክርስቲያን ግመሉ ከሚችለው በላይ ስለጫነው አንተ አቅም አጥተህ ምክር ለመቀበል መጥተህ ሳለ ግመሉን ካለ አቅሙ ለምን ጫንከው ተብሏል፡፡


ከዐቅማቸው በላይ ተሸክመው የከበዳቸውን ሰዎች በማገዝ ሸክሙ ሳይከብዳቸው፣ ከክርስቲያናዊ ተጋድሎ ሳያፈገፍጉ በእምነት እንዲኖሩ ማገዝ ከዘመናችን የሃይማኖት ሰዎች የሚጠበቅ መሆኑን ለማስታወስ የአባ ዳንኤልን ፈሊጥ በአብነት እጠቅሰዋለሁ፡፡

አንድ አባ ዳንኤል የሚባል መነኩሴ ነበር፡፡ የደከመ ባገኝ አግዛለሁ እያለ በጨረቃ ከበዓቱ ወጥቶ ገዳማውያን በሚገኙበት በረሓ ይዞር ነበር፡፡

በአንድ ወቅት የማትሠራው ኃጢአት ያልነበር፣ ከጽድቅ ተግባር የማትተዋወቅ ሴት አገኘ፡፡ አባ ዳንኤልም ሴቲቱን ወደ ሴቶች ገዳም ወስዶ ልብላ ካለች ትብላ፣ ልተኛ ካለች ትተኛ፣ የፈቀደችውን ሁሉ ታድርግ፣ የገዳሙ ሕግ አይፈቅድም በማለት ቀንበር አንዳታከብዱባት ብሎ ለእመምኔቷ አስረክቧት ሔደ፡፡

እመምኔቷም እንደታዘዘችው አደረገች፡፡ ሴቲቱ በፈለገች ጊዜ ትበላለች፣ ስትፈልግ ትተኛለች፡፡ ያሰኛትን ታደርጋለች፡፡ ግን ደስታ የላትም፤ አብረዋት የሚኖሩት መነኮሳት ቤተ ክርስቲያን አድረው፣ በሥራ ተጠምደው ሲኖሩ ተመለከተች፡፡ እሷ በልታ ይርባታል፡፡ እነሱ ሳይበሉ አይራቡም፣ እሷ ተኝታ ይደክማታል፣ እነሱ ቆመው ውለው፣ ቆመው አድረው ድካም አያውቁም፡፡ ቀስ በቀስ መገረም፣ ከዚያም በሕይወታቸው መቅናት ጀመረች፡፡


ምግብ ሲያቀርቡላት እስከ ሦስት ሰዓት ልቆይ ማለት ጸሎት አድርጋ መብላት ተለማመደች፡፡ ቆየችና እስከ ስድስት ልቆይ አለቻቸው ከዚያም እስከ ዘጠኝ፣ ከዚያም በ24 ሰዓት አንድ ጊዜ መመገብ ጀመረች፡፡ ከዚያም ከሳምንት አንድ ቀን ብቻ መቅመስ በመጨረሻም በዓቷን ዘግታ በሦስት ሳምንትም፣ በወርም በሕይወት ለመቆየት ያህል መቅመስ ደረሰች እንዲህ ድክመታችን ታግሠው ለክብር የሚያበቁን ባለ ፈሊጥ መምህራን ማግኘት ለዚህ ዘመን እንዛዝላ ተሸካሚ ከዕንቊ የበለጠ ስጦታ ነው እላለሁ፡፡

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
124 views07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 12:51:00 እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!


አንድ ካህን በሞቃታማ ዕለት ብቻቸውን ጭር ባለ ጎዳና ላይ ሲሔዱ አንድ መሣሪያ ያነገተ የሚያስፈራ ሰው ድንገት ከዛፎች መሃል ዘልሎ ወጣና ከፊታቸው ቆመ።

ቄሱ ላይ አፍጥጦ "እስካሁን ዘጠና ዘጠኝ ሰዎች ገድያለሁ አንተ መቶኛው ትሆናለህ!" አላቸው።

ካህኑም መልሰው "ለመሞት ዝግጁ ነኝ ፣ ነገር ግን በጣም ስለጠማኝ ትንሽ ውኃ ሥጠኝና ትገድለኛለህ" አሉት። ነፍሰ ገዳዩ ለአፍታ ግራ ከተጋባ በኋላ በቄሱ ላይ መሣሪያውን እንደደገነ በዛፎቹ መካከል ካለው ምሽጉ ውስጥ በኩባያ ውኃ አምጥቶ እንዲጠጡ ሠጣቸው።

ካህኑ ውኃውን እየጠጡ እያለ ግን ሽፍታው ድንገት በልብ ድካም ሕይወቱ አለፈች።

የዚህን ሰው ነፍስ ወደ ገነት ለመውሰድ መላእክት በመጡ ጊዜ አጋንንት ነፍሱ የእኛ ፈንታ ናት ብለው ተከራከሯቸው። "ይህ ሰው ዘጠና ዘጠኝ ሰዎችን የገደለ ሲሆን እጅግ ብዙ ትንንሽ ኃጢአቶችንም ፈጽሟል። ነፍሱ የሚገባው ለእኛ ነው" አሉ።

መላእክቱ ግን እንዲህ ብለው ለአጋንንቱ መለሱላቸው "ያደረገው እንዳለ ሆኖ ይህ ሰው ከሠራቸው ኃጢአቶች የበለጠ የሚመዝኑ በክርስቶስ ወንጌል የታዘዙ ሁለት ታላላቅ ተግባራትን ፈጽሟል።

የመጀመሪያው ዘጠና ዘጠኝ ሰው እንደገደለ ለካህን መናዘዙ ሲሆን :-
ሁለተኛው ለተጠማ ውኃ ማጠጣቱ ነው!" አሏቸው።

መልዕክት

የትኛውንም ያህል ቢደጋገም እንኳን ከእግዚአብሔር ምሕረት ሊበልጥ የሚችል ኃጢአት የለም!

ቅዱስ ኒኮላይ ቬሊሚሮቪች (St. Nicholai Velimirovich)

ምንጭ: Anicent Christian Wisdom

ትርጉም: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
274 views09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 21:50:11
ቡና ይጠጣል ወይንስ አይጠጣም ???
#አንብቡት

''አቅረብኩ ለከ እሳተ ወማየ ፤ደይ እዴከ ኀበ ዘፈቀድከ''
"እሳትና ውሃ አቀረብኩልህ እጅህን ወደ ፈለከው ስደድ" (ዘፍ. 2፥17)

ትክክለኛ ምንጮችን ማለትም #የሀሳብ_ስርዋጽ ያልተደረገባቸዉን የጥንቶቹን መጽሀፍት እየፈለጋችሁ አንብቡና ለነፍሳችሁ የሚሆናትን ያዙ ።

ለመብላት እና ለመጠጣት ምክንያት የምትፈልጉና ምክንያትንም የምታበዙ፣ ፣ ማስረጃ የሆኑት ቅዱሳት መጽሀፍት እንዲህ እያዘዙ አንሰማም ፣ መብል መጠጥ ደግሞ ምን ችግር አለው የምትሉ ከሆነ ደግሞ አማራጩ በእጃችሁ ነው ።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
2.0K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 20:49:26

አብ የማይጠልቅ ፀሐይ እንደሆነ፣ ወልድም ዘወትር በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ፀሐይ ነው። ወልድ ዘወትር በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ፀሐይ እንደሆነ ፣ መንፈስ ቅዱስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት ፀሐይ ነው።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
1.1K views17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 19:51:37
እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ

#ወዳጄ_ሆይ! #እግዚአብሔር ነዳያንን የሚልክልህ መስጠትን እንድትለማመድ ነው፡፡

ዛሬ በነዳያኑ አድሮ የሚለምንህ ለኋለኛይቱ ቀን #ስንቅ እንዲያስቀምጥልህ ወድዶ ነው፡፡

ታዲያ ንጉሥ ወደ ቤቱ መጥቶ የሚያባርር ሰው እንደ ምን ያለ ጎስቋላ ሰው ነው?

እንግዲያውስ ነዳያንን ስታይ ወደ አንተ የመጣው ንጉሠ ሰማይ ወምድር #ክርስቶስ እንጂ ሰው አይደለምና አትግፋው፡፡ በረከትህንም ከቤትህ አውጥተህ አትሸኘው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
1.3K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 19:23:04 ሰው ነህ ፤ ግን

ሰው ነህ፤ ግን ደግሞ እንደ እባብ መርዝ ትተፋለህ፡፡

ሰው ያውም ክርስቲያን ነኝ ትላለህ፤ ነገር ግን ከበረሀ አውሬ ይልቅ ስትደነፋ እመለከታለሁ፡፡

አንደበት የተሰጠህ ሰዎችን ከቁስለ ሥጋ ከቁስለ ነፍስ ታድንበት ዘንድ ነበር፤ ነገር ግን ወንድምህን ስታቆስልበት አያለሁ፡፡

ታድያ አንተን ማን ብዬ ልጥራህ?


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
151 views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 12:15:59
ለእኔ ያለቅስልኝ ዘንድ ፍጹም ጐስቋላው እኔ ለማን እናገራለሁ???


ጠላት ዲያብሎስ/ ከስንፍናዬ የተነሣ እርቃኔን አቁሞኛል፡፡ ከስስቴ የተነሣም ትግሥቴ ቀልጧል፡፡ ከትጋትና ከጸሎት እንድለይ አደረገኝ፡፡
በእኔ ላይ ወርቅና ብር መውደድን ተከለ፡፡
ዕንባዬን አደረቀ
ልቤንም አደነደነ
ለክርስቶስ ከሚገባው ትእዛዝም ለየኝ
ጨካኝ፣ ቀናተኛ፣ ወንጀለኛ እና አሸናፊነትን ወዳጅም አደረገኝ፡፡

በዓይኔ ውስጥ ያለውን ጉድፍ እንዳይ አላደረገኝም፣ በወንድሜ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ግን አቅርቦና አጉልቶ ያሳየኛል፡፡

ልቡናዬ ያሰበውን እሰውር ዘንድ ይመክረኛል፡፡ በስህተት ብወድቅም ዘወትር እንድናገራት ያደረገኛል፡፡

ትቢተኛ እንድሆንም አደረገኝ በልቦናዬም ስስትን አሳደረብኝ የፍትወትን ጣዕም፣ ስካርንና ነፍስ ማጥፋትን የምወድ አደረገኝ፤ በእኔ ዘንድም #እንደጥቅም አደረጋቸው።

የማጉረ መርም፣ ሰነፍ፣ ልማደኛ፣ ክፉና ተከራካሪ አደረገኝ፡፡ በማንበብ በመዘመር እደሰታለሁ፡፡ እጸልያለሁ፤ #የምለውን_ግን_አላውቀውም ይጠራኛል፤ ብዙ ጊዜ ግን አላውቅም #እግዚአብሔርን በሚፈሩ ሰዎችም ተመከርሁ፤ ትምህርታቸውን፣ ያማረና
የሚጠቅም ምክራቸውን ግን አልተቀበልሁም፡፡

ቃላቸውን እንደሕግ አድርጌ እይዛለሁ፤ ነገር
ግን አላደርገውም:: ጠላት ዲያብሎስ/ ይህን ሁሉ ጥፋት በእኔ ላይ ያመጣብኛል። ወደእኔ የማይመለሰው እስከመቼ ነው? #የፈጠረኝን_የማስቆጣ ከሆነ ወደ ማን እጠጋለሁ? በዚህች ክፋትስ እስከ መቼ እኖራለሁ? አምላክ በቸርነቱ ብዛት ያጐና ጸፈኝን ጸጋ ካድሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ከዲያብሎስና ከጥፋት ሥራው እሸሻለሁ፡፡


የቅዱስ ማርኤፍሬም ፀሎት
✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
169 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 09:49:49 ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
✞ አቡነ ሀብተ ማርያም ✞
=====================

ዳግመኛም ‹‹ሀገሬ የኖርኩባት አንጾኪያ ናት፣ በልጄ በዲዮቅልጥያኖስ ልብ ውስጥ አድሬ በውስጧ ብዙ ጊዜ ሥራ የሠራሁባት በመኳንንትም ሁሉ አድሬ በክርስቶስ ያመኑትን ክርስቲያኖችን ሁሉ በልጄ በዲዮቅልጥያኖስ አድሬ የገደልኳቸው እኔ ነኝ፤ ከእርሱም ዘንድ ወደ ሌላ ሀገር ሄጄ 47 ሺህ ሰማዕታትን አስገድዬ 9 ሺህ ሰማዕታትን አሳሰርኩ፡፡ ነገር ግን ቈስጠንጢኖስ የሚባል ደግ ንጉሥ በነገሠ ጊዜ ክርስቲያኖችን ከእሥር ቤት አውጥቶ ፈጽሞ አከበራቸው፤ እኔን ግን አዋረደኝ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ጤና አላገኘሁም፤ ልጄ ዲዮቅልጥያኖስ ከሞተ በኋላ ከንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ክብር የተነሣ መውጫ መግቢያ አጥቼ መከራን እየተቀበልኩ ስቅበዘበዝ ያን ጊዜ ‹ለምን ሥራ ትፈታለህ? ሥራህን ታስተምራቸው ዘንድ ወደ ኢትዮጵያ ሀገር ሂድ› የሚል ቃል ከጌታዬ ከዲያብሎስ ተነገረኝ፤ እንደምታየኝ ወደዚህ ሀገር መጣሁ›› ብሎ ለአባታችን ነገራቸው፡፡ አባታችንም እንደበፊቶቹ እንደሁለቱ አጋንንት መሬት አፏን ከፍታ እንድትውጠው ሊያደርጉት ሲሉ ያን ጊዜ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተ ማርያምን ‹‹በሚፈረድበት ገንዘብ የሚፈረድበት ጊዜ አልደረሰምና ይህንንስ ተወው›› አላቸው፡፡ ጌታችንም ይህንን በተናገረ ጊዜ ያ ሰይጣን ከአባታችን ዘንድ በኖ ጠፋ፡፡ አፏን ከፍታ የነበረችው ምድርም እንደ ቀድሞዋ ሆነች፡፡

አባታችን ወደ ደብረ ሊባኖስ ሄደው ሳለ አንዲት ወፍ በፊት ለፊታቸው ተቀምጣ እጅግ አምርራ ስታለቅስ አቡነ ሀብተ ማርያምም አብረዋት አለቀሱ፡፡ መነኮሳቱም አባታችንን ለምን እንደሚያለቅሱ ሲጠይቋቸው ወፏ የምታለቅስበትን ምሥጢር ነገሯቸው፡፡

አጋት የምትባለውም ባሕር አፏን ከፍታ በሰው አንደበት አባታችንን አናገረቻቸው ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሀብተ ማርያም ሆይ! የዚህች ሀገር ሰዎች የሚያደርጉብኝ በደል ተመልከትልኝ፣ ሌሊት ሌሊት በእኔ በባሕር ውስጥ ቆመው የሚያድሩ ቅዱሳን ሰውነታቸውን እየገረፉ ሲጸልዩብኝ በእነርሱ ደም ተቀድሼ አድራለሁ፣ ቀን ቀን ደግሞ ኃጢአተኛ ሰዎች ወደ እኔ መጥተው በዝሙት የረከሰውን ገላቸውንና ልብሳቸውን ያጥቡብኛል›› እያለች ነገራቻቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ባሕር ሆይ የእግዚአብሔር ፍርድ እስከሚደርስ ድረስ ታገሽ›› አሏት፡፡ ይህንንም የሰሙ ልጆቻቸው ሁሉ እጅግ አደነቁ፡፡

ዳግመኛም ሌላኛዋ ባሕር ‹‹ቅዱሱ ሆይ ፍረደልኝ አንድ ታላቅ ዘንድ የሀገሩ ሰዎች ያለ ዕውቀት የሚያመልኩት ሁልጊዜ እየመጣ ከእኔ ሲጠጣ በጣም አዝናለሁ›› አለቻቸው፡፡

ከዚህም በኋላ የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም ዕለተ ዕረፍታቸው በደረሰ ጊዜ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በታላቅ ምስጋና ወደ ብፁዕ አባታችን መጥቶ ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ሆይ! ዛሬ ወደ አንተ የመጣሁት ከድካም ወደ ዕረፍት እወስድህ ዘንድ ነው፣ ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡ ስለ ንጹሕ ድንግልናህ፣ ዓለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣ ስለ ፍጹም ምንኩስናህ፣ ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመጸለይህ፣ ስለ እኔ ብለህ ስለተራብክ፣ በጾም ስለተጋደልክ፣ ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትንና ትምክህትን በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህና ስለ ንጹሕ መሥዋዕትህ ነው›› ብሎ አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ትልቅ የምሕረት ቃልኪዳን ገባላቸው፡፡ ቃልኪዳንም ከገባላቸው በኋላ ጌታችን አባታችንን አፋቸውን ሦስት ጊዜ ሳማቸው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኔዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሣ ቅድስት ነፍሳቸው ከሥጋው ተለየች፡፡

ከአባቶቻችን ከ አባ አሞጽ ፣ከ አባ ቀጸላ ጊዮርጊስ፣ከ አባ ዮሐንስ ከማ እረድኤት በረከት ቃልኪዳን ተካፋይ ያድርገን የአባቶቻችንን በረከት ያሳድርብን አሜን::
የአቡነ አሞፅ እና አባ ቀፀላ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!!!
የቅዱሳን አባቶቻችን የሐዋርያው የቅዱስ ቶማስ፣ የአቡነ ሐብተማርያም፣ የአቡነ ኢየሱስ ሞዐና የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከታቸው በአማላጅነታቸው በምንታመን በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን!!!

ምንጭ ፡ ከገድላት አንደበት
=====================
✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
174 views06:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 09:48:31 ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
✞ አቡነ ሀብተ ማርያም ✞
=====================

አቡነ ሀብተ ማርያምም ይህን በተመለከቱ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹መስቀል ታሳልሟት ዘንድ ያችን ነፍስ ወደ መስቀል ለምን ወሰዳችኋት?›› ብለው ጠየቁት፡፡ መልአኩም ‹‹በትልቅም በትንሽም ነገር ክርስቲያናዊትን ነፍስ የሚቃወም ቢመጣባት ድል የምትነሳበትን በመስቀል ፍርድ ይታይላታልና ስለዚህ ነው፡፡ የሚከራከራት ቢኖር ግን እንዳየኸው ወደ መስቀል ባደረሷት ጊዜ የሚቃወማት ሰይጣን ፈጥኖ ይርቅላታል ዳግመኛም ሊከራከራት አይችልም›› አላቸው፡፡

ከአቡነ ሀብተማርያም በረከት ለመቀበል ብዙ ቅዱሳን ከሮም፣ ከግብፅ፣ ከአስቄጥስና ከሲሐት ገዳም ወደ አባታችን ዘንድ ይመጡ ነበር፤ ከየሀገራቸውም በአንበሳ ተቀምጠው የሚመጡ አሉ፤ ክንፍ ተሰጥቷቸው እንደ ንስር የሚበሩም አሉ፤ ብፁዕ አቡነ ሀብተ ማርያምም የቅዱሳኑን ብቃት አይተው ‹‹ሥራችሁ እንዲህ እንዲህ ሲሆን ለምን ወደኔ መጣችሁ?›› ብለው ሲጠይቋቸው ቅዱሳኑም ‹‹በማንኛውም ሥራ እግዚአብሔርን በለመነው ጊዜ በኢትዮጵያ የሚኖር እንደ ሙሴ ያለ ሀብተ ማርያም የሚባል ወዳጄ አለና ሁሉን ስለሚነግራችሁ ዘወትር እርሱን ጠይቁ ብሎ ስላዘዘን ወደ አንተ መጣን›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ቅዱሳኑን ከባረኳቸውና ከእነርሱም ከተባረኩ በኋላ አባታችን ለቅዱሳኑ የሚመጣውን እንዳለፈ የሚደረገውንም እንደተደረገ አድርገው ይነግሯቸዋል፡፡ ቅዱሳኑም ከልጅነታቸው ጀምረው እስከዚያች ቀን ድረስ የሠሩትን ሥራ ሁሉ ይነግሯቸዋል፡፡ እነርሱም እጃቸውን እየሳሙ በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡

እንደዚሁም አቡነ ሀብተ ማርያም ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል እየተራዱዋቸው ቀድሰው በሚያቆርቡ ጊዜ ተሰውረው የሚኖሩ 500 ስውራን ቅዱሳን መጥተው ሥጋ ወደሙን ከአባታችን እጅ ተቀበሉ፡፡ ቀድሰውም ወደበዓታቸው እንደገቡ እመቤታችን ተገልጣላቸው ‹‹በነገውም ዕለት ቅዳሴዬን ቀድስ፣ ይህም ቅዳሴ መዓዛ ቅዳሴ ነውና፡፡ የዓለም መሠረት ማርያም ወደኔ ነይ ብለህ በጠራኸኝ ጊዜ ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትዬ መጥቼ እባርክሃለሁ›› አለቻቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በነገው ዕለት ሌላ ተረኛ ቄስ ይቀድሳልና ይህ እንዴት ይሆንልኛል?›› አሏት፡፡ እመቤታችንም ‹‹ፈቃዴ ስለሆነ አንተ እንድትቀድስ አደርጋለሁ›› አለቻቸው፡፡ በነጋታው ተረኛው ቄስ ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ቸኩሎ እየተፋጠነ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገሰግስ ወድቆ ጥርሱ ደማና ስለ ሥጋ ወደሙ ቅዳሴ እጅግ ደንግጦ ወደ አባታችን መጥቶ ‹‹ቅዳሴው በእኔ ስም ከሚታጎል አንተ ቀድስልኝ›› አላቸው፡፡ አባታችንም አስቀድማ እመቤታችን የነገረቻቸውን ነገር አስበው እያደነቁ ሄደው ቀደሱ፡፡ እመቤታችንም ነቢያትን ሐዋርያትን አስከትላ መጥታ ባረከቻቸው፡፡

በወቅቱም በሀገራችን ላይ ሃይማኖቱ የቀና ደጉ ንጉሥ ዐፄ ናዖድ ነግሦ ሳለ በእርሱ ዘመን እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ሥራ በሀገሩ ተሠርቶ ነበርና ጌታችን ለአቡነ ሀብተ ማርያም የምሥጢር መጽሐፍን ሰጣቸውና ለንጉሡ ወስደው እንዲሰጡ አዘዛቸው፡፡ ወስደውም ለንጉሡ ሰጡትና መብረቅም ወርዶ ሀገሪቱን ሊያጠፋት መሆኑን ነገሩት፡፡ ዐፄ ናዖድ ይህን በሰሙ ጊዜ መልእክቱንም ካስተረጎሙ በኋላ እጅግ ደንግጠው አቡነ ሀብተ ማርያምን ‹‹ሀገራችንን በጸሎትዎ ታደጓት›› አሏቸው፡፡ በጸሎታቸውም እንዲያስቡት በወርቅ የከበረ መስቀል ሰጣቸው፡፡ አባታችንም ወደ በዓታቸው ተመልሰው በጾም በጸሎት ተወስነው እያለቀሱ ስለ ሀገራችን አጥብቀው ጸለዩ፡፡ ጌታችንም ተገልጦላቸው ‹‹ድካምህን አይቻለሁና በሀገርህ የታዘዘው መቅሰፍቴ ይርቃል ነገር ግን በቸነፈር ጥቂት ሰዎች ይሞታሉ›› አላቸው፡፡ አባታቸንም ደስ ተሰኝተው ይህንንም ሰምቶ ይደሰት ዘንድ ለንጉሡ መልእክተኛ ልከው ነገሩት፡፡

ከዚህም በኋላ አቡነ ሀብተማርያም በጸሎት ላይ ሳሉ ጌታችን መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ አባታችንን ‹‹የቆምክባትን ቦታ ምሥራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ›› አላቸው፡፡ አባታችንም እንደታዘዙት ሲባርኩ ሦስት አጋንንት በትይዩ ቆመው ታዩአቸው፡፡

ከኖኅ ዘመን ከተደረገው ማየ አይህ ተርፈን ብዙ ዘመን ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን? ሀብተ ማርያም ሆይ ታጠፋን ዘንድ መጣህን›› ብለው ጮኹ፡፡ አባታችንም ‹‹በሰው ላይ የምታደርጉትን የምታስቱበትን ብልሃታችሁን ነገሩኝ›› አሏቸው፡፡

ከእነርሱም ውስጥ አንዱ ‹‹እኔ ከጥንትም ጀምሮ አምላክ ነኝ እያልኩ ሳታልላቸው ኖርኩ፤ ክታብ መጻፍን፣ ቅጠል መበጠስን፣ ሞቶ ያደረውን ከብት መብላትን፣ የሰውን ሥጋ መብላትን፣ በወፍ ማሟረትን አስተማርኳቸው፡፡ በሚሞቱበትም ጊዜ ወደ ሲኦል አወርዳቸዋለሁ፡፡ በእንዲህም ሥራ ሳለሁ ክርስቶስ ተወለደና ሥራዬ የተገለጠ ሆነ፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ ተክለ ሃይማኖት የሚባል ኃይለኛ ሰው መጥቶ ከክርስቶስ በቀር ለእኔ እንዳይገዙ አደረጋቸው፤ እገድለውም ዘንድ ብዙ ጊዜ ሞከርኩ ነገር ግን እርሱ እጅግ በረታብኝ፤ ወገኖቼንም ቀማኝ፡፡ ሁለተኛ ወንድሜም ይውጠው ዘንድ በዘንዶ ተመሰለ ነገር ግን በመስቀል ባማተበበት ጊዜ ተሰንጥቆ ሞተ፡፡ እኔም ከእርሱ የተነሣ ስለነፈራሁ ሸሽቼ ተሸሽጌ መንደር ለመደንር ስቅበዘበዝ ኖርኩ ፈንታዬ የሆኑ ጥቂት ሰዎችንም አገኘሁ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹ያሳትካቸው እነማን ናቸው?›› ባሉት ጊዜ ሁሉንም ስማቸውን እየጠራ በዝርዝር ነገራቸው፡፡ ‹‹የእገሌ ኃጢአቱ ይህ ነው…›› እያለ የእያንዳንዱን የበደላቸውን መጽሐፍ አነበበላቸው፡፡

ዳግመኛም ሰዎች እርሱን የሚያሸንፉበትን ነገር ለአባታችን ሲነግራቸው ‹‹ነገር ግን ኃጢአት ሠርተው በደላቸውን ለካህን በመንገር ንስሓ ገብተው እኔ ልሰውረው ስወድ ምክሬን በገለጡብኝ ጊዜ ትቻቸው እሸሻለሁ›› አላቸውና እንዲያሰናብቱት ለመናቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ጌታችን አቡነ ሀብተ ማርያምን ‹‹ብዙ ቅዱሳንን አስቷልና አታሰናብተው፣ ከእግሩ በታች ያለውን መሬት ባርክና ምድር አፏን ከፍታ ትዋጠው›› አላቸው፡፡ አባታችንም ጌታችን እንዳዘዛቸው አድርገው ያንን እርኩስ መንፈስ ምድር አፏን ከፍታ እንትውጠውና ጽኑ ፍዳ ወዳለበት ወደ ሲኦል እንዲወርድ አደረጉት፡፡

ይህንንም ሲያዩ እዚያው ቆመው የቀሩት ሁለቱ አጋንንትም እጅግ ፈሩ፡፡ አንደኛውም ክንፍ ያለው እባብ ሆኖ ወደ አየር በበረረ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት በእሳት መንኰራኩር ራስ ራሱን ቢቀጠቅጡት አፏን ወደ ከፈተችው ምድር ወደቀና እንደ ጓደኛው ወደ ሲኦል ወረደ፡፡ የቀረው ሦስተኛው ግን አባታችንን ‹‹ሀብተ ማርያም ሆይ ያደረኩት ክፉ ነገር ሳይኖር ያለ ጊዜዬ እንዳታጠፋኝ በምታመልከው አምላክ ስም አምየሃለሁ፣ እኔ በዚህ ወር ነው ከዚህ ሀገር የደረስኩት›› እያለ ለመናቸው፡፡

=====================
✥ ✞ ✥
❖ ✥┈•◦●◈◎❖◎◈●◦•┈✥❖
98 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ