Get Mystery Box with random crypto!

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች

የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_tewaahdo — የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች
የቴሌግራም ቻናል አርማ ortodox_tewaahdo — የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች
የሰርጥ አድራሻ: @ortodox_tewaahdo
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.87K
የሰርጥ መግለጫ

✞ በዚህ Channel ላይ የኦርቶዶክስ የመምህራን ትምህርቶችና ትክክለኛ መዝሙሮች ይተላለፉበታል ኑ በአንድነት እንዘምር እናመስግን።
አንደበት ያላችሁ
ለእግዚአብሔር ዘምሩ
የተከበረ ነው በሰማይ በምድሩ!
"ድምፁ መልካም በሆነ ፀናፅል አመስግኑት እልልታ ባለው ፀናፅል አመስግኑት"ሃሄ ሉያ፨ መዝ ፻፶፥፭ (150፥5)
●●◎◉••••••• ✞ •••••••◉◎●●
ፍቅር ይኑረን
@ZebbeneLEMA

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-24 08:50:08 ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
864 views05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 07:48:24


† † †

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬



---------------------------------------------------

ቀዳም ሥዑር [ የተሻረች ቅዳሜ ]

---------------------------------------------------

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት ፦

ቀዳም ሥዑር ፡-

በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር [ የተሻረች ] ተብላለች፡፡ በዓል መሻርን አይመለከትም፡፡ በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡ በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

---------------------------------------------------

ለምለም ቅዳሜ ፦

ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል [ ቃለዓዋዲ ] እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር ፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር ፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

[ የቄጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

---------------------------------------------------

ቅዱስ ቅዳሜ ፡-

ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

[ ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ]


▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
https://t.me/Ortodox_Tewaahdo

2.3K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:56:46 መዝሙር 69
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።

²¹ ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።

²² ማዕዳቸው በፊታቸው ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤

²³ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውም ዘወትር ይጕበጥ።

²⁴ መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።

²⁵ ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤

²⁶ አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥ በቍስሌም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩብኝ።

²⁷ በኃጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥ በጽድቅህም አይግቡ።

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
899 viewsedited  04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:55:57 መዝሙር 69
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።

²¹ ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።

²² ማዕዳቸው በፊታቸው ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤

²³ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውም ዘወትር ይጕበጥ።

²⁴ መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።

²⁵ ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤

²⁶ አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥ በቍስሌም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩብኝ።

²⁷ በኃጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥ በጽድቅህም አይግቡ።
መዝሙር 69
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ ነፍሴ ስድብንና ኃሣርን ታገሠች፤ አስተዛዛኝም ተመኘሁ አላገኘሁም፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።

²¹ ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።

²² ማዕዳቸው በፊታቸው ለወጥመድ ለፍዳ ለዕንቅፋት ትሁንባቸው፤

²³ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፥ ጀርባቸውም ዘወትር ይጕበጥ።

²⁴ መዓትህን በላያቸው አፍስስ፥ የቍጣህ መቅሠፍትም ያግኛቸው።

²⁵ ማደሪያቸው በረሃ ትሁን፥ በድንኳኖቻቸውም የሚቀመጥ አይገኝ፤

²⁶ አንተ የቀሠፍኸውን እነርሱ አሳድደዋልና፥ በቍስሌም ላይ ጥዝጣዜ ጨመሩብኝ።

²⁷ በኃጢአታቸው ላይ ኃጢአትን ጨምርባቸው፥ በጽድቅህም አይግቡ።

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
687 views04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:52:57
መዝሙር 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯

¹² ብዙ በሬዎች ከበቡኝ፥ የሰቡትም ፍሪዳዎች ያዙኝ፤

¹³ እንደ ነጣቂና እንደሚጮኽ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።

¹⁴ እንደ ውኃ ፈሰስሁ አጥንቶቼም ሁሉ ተለያዩ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፥ በአንጀቴም መካከል ቀለጠ።

¹⁵ ኃይሌ እንደ ገል ደረቀ፥ በጕሮሮዬም ምላሴ ተጣጋ፥ ወደ ሞትም አሸዋ አወረድኸኝ።

¹⁶ ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፤ የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።

¹⁷ አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ፤ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።

¹⁸ ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።


https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
587 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:52:57 ዓለም ትደንቃለች ዓለም ትደንቃለች
እሁድ በዘንባባ በምንጣፍ አክብራ
አርብ በመስቀል ላይ ጌታዋን ሰቀለች
ዓለም ትደንቃለች...

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
578 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:52:57 በፈቃዱ ለሕማም ተሰጠ
እየሞተ ታሪክን ለወጠ
ሕሙማንን ያድን ዘንድ ታመመ
አማኑኤል መስቀል ተሸከመ

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
548 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:52:57 በደል ሳይኖርብህ
ጥፋት ሳይኖርብህ
ስለኛ ተገረፍክ
ስለኛ ተሰቀልክ

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
543 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 07:52:57 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ዋለ በዓደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
ሕይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድነው

https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
534 views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ