Get Mystery Box with random crypto!

#ሰኔ_12 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት | የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች

#ሰኔ_12

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም

ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣ መታሰቢያው የሚከበርበት በዓል እና #ቅዱስ_ባህራንን የረዳበት ዕለት ነው፡፡ ዳግመኛም በዚህች ቀን #የቅድስት_አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ሆነ፣ የተባረከና የተመሰገነ #የኢትዮጵያ_ንጉሥ_ላሊበላ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ፣ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ዮስጦስ አረፈ፣ ስልሳ ሰባተኛ የሆነው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት #አባ_ቄርሎስ አረፈ።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን፤ የከበረ መልአክ ሚካኤል የረድኤቱ ኃይል ሁላችን የክርስቲያን ወገኖችን ይጠብቀን ለዘላለሙ አሜን።