Get Mystery Box with random crypto!

( ሙሽሮቹ መልካም ጋብቻ ) የትእግስት ዋጋ እውነትም ትልቅ ነው ክብርን ከፍ አድርጎ ተክሊል የሚ | የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮችና ትምህርቶች

( ሙሽሮቹ መልካም ጋብቻ )

የትእግስት ዋጋ እውነትም ትልቅ ነው
ክብርን ከፍ አድርጎ ተክሊል የሚሰጥ ነው።
ሙሽሪት ሙሽራው ያበራል ፊታቸው
ጌታ መንፈስ ቅዱስ ገብቶ ከቤታቸው!

ቤተ ክርስትያን ሆይ እንኳን ደስ አለሽ
ሙሽሪት ሙሽራው በስጋ ወደሙ ተዋሃዱልሽ
ሙሽራው ሙሽሪት እንኳን ደስ አላችኹ
በስጋ ወደሙ ሆነ ጋብቻችኹ!

ሙሽሪት ሙሽራው!
እስኪ ንገሩን ምስጢሩ ምድር ነው
ለዚኽ ክብር መብቃት ምን ብታደርጉ ነው!?
እንዴትስ ብትተጉ ጸሎታችኹ ሰምሮ ለዓለም የታየው
በቅድስቷ ቦታ ክብር ተሹማችኹ
የተፈጸመበት መልካም ጋብቻችኹ
እጅግ የሚደንቀው !

የማይሳነው አምላክ ድንቅ መካር ሐያል
እናንተን ያጸና በማይናወጥ ቃል
የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዓለም ይመስገን!

ሚስት ለባሏ ዘውድ ናት !
ባል ለሚስቱ ንጉስ ነው !

የኪነጥበብ ቤተሰብ ይሁኑ !
https://t.me/Ortodox_Tewaahdo
የሰንበት ት/ቤት ኪነጥበብ ክፍል !