Get Mystery Box with random crypto!

✝ ሐመረ ኖኅ✝

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthotek — ✝ ሐመረ ኖኅ✝
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthotek — ✝ ሐመረ ኖኅ✝
የሰርጥ አድራሻ: @orthotek
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.20K
የሰርጥ መግለጫ

☞ያልተበረዘ ትምህርት
☞ጣዕመ ዝማሬ
☞የመዝሙር ግጥሞች
☞የቤተክርስቲያናችንን ወቅታዊ ዜናዎች እናም
☞ለመናፍቃን የተለያዩ መልሶች እናቀርባለን !

@ORTHOTEK
@ORTHOTEK
@ORTHOTEK
:
አስተያየት ለመስጠት ጥያቄ ለመጠየቅ እናም ይሄ ፅሁፍ ቢቀርብ ያስተምረናል በዚህ ቻናል ይሄ ቢጨመር ይሄ ቢቀነስ የምትሉት ካለ @Benyaa_s ወይም @Mulexa ላይ መልዕክት አስቀምጡልን !

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 17

2022-08-11 10:37:56 መልክአ ማርያም

ዕብል ለኵርናዕኪ


ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
@Benyaa_s
@Mulexa
@YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!
431 viewsሙሉዓለም አየለ, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:37:20 መልክአ ማርያም

ለመዛርዕኪ


ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
@Benyaa_s
@Mulexa
@YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!
389 viewsሙሉዓለም አየለ, 07:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:24:05 ሱባኤ ክፍል ፪

ሱባዔ ለምን ያስፈልጋል?

የሰው ልጅ ኃጢአት በሚስማማው ሥጋው ዘወትር ፈጣሪውን ይበድላል፡፡ እግዚአብሔር አዋቂ አድርጎ የሰጠው በጎ ኅሊናው የፈጸመው በደል ትክክል እንዳልሆነ ይወቅሰዋል፤ በዚህም የተነሣ በሠራው ኃጢአት ምክንያት ይደነግጣል፡፡ ይህ በማንኛውም ሰብአዊ ፍጥረት ኅሊና ውስጥ የሚከሰት ሀቅ ነው፡፡ አምላኩን በማሳዘኑ ከሚመጣበት ቅጣት ለመዳን ንስሐ ገብቶ ሰውነቱን በጾምና በጸሎት በመጥመድ ራሱን በጽድቅ ሥራ ያሳትፋል፤ ይህም በጎ ሥራ እንዲሠራ ሱባኤ መግባት ያስፈልገዋል፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና… ነገር ግን በብልቶቼ ባለ በኃጢአት ሕግ የሚማርከኝ ሌላ ሕግ አያለሁ፡፡ እኔ ምንኛ ጐስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?» እንዳለ /ሮሜ.7፥22-25/፡፡

ከዚህ አንጻር በጥቂት ድካመ ሥጋ ያልተወሰነ ጸጋ እግዚአብሔር ለማግኘት ሱባዔ መግባት በኃጢአት ሸክም መንፈሱ ሲታወክ የነፍስና የሥጋ ሰላሙን ለመመለስ መጾምና መጸለይ ግድ ይሆንበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ሱባዔ ለምን ያስፈልጋል? ለምን ምላሻችን፡-

እግዚአብሔርን ለመማጸን ነው!

ሰው ሱባዔ ከምንይዝባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ እግዚአብሔርን ለመማፀን ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ሱባዔ ከመግባቱ በፊት የምገባው ለምንድን ነው? የማገኘውስ ጥቅም ለምንድን ነው? ለሚሉት ጥያቄዎች አስቀድሞ ከንስሐ አባቱ ጋር በግልጽ ተወያይቶ መልስ ማግኘት አለበት፡፡ ያለበለዚያ ምንም የሚጠይቀው ነገር ሳይኖር ሱባዔ ቢገባ የሚያገኘው መልስ አይኖርም፡፡ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔ በኋላ ምን እንደ ተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖር ሱባዔ በመግባታቸው የሚያገኙት ነገር የለም፡፡ ስለዚህ ሱባኤ ከመግባታቸው አስቀድሞ ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማኅፅኖ ሊኖረው ይገባል፡፡

ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ‹‹እግዚአብሔርን ለመማፀን የምፈልበው ለምንድን ነው?» በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ክርስቲያን በግል ሕይወቱ ዙሪያ ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ጓደኛው ጤና ወዘተ ጉዳዮች ላይ ፈጣሪውን ይማፀናል፡፡ በዚህ ጊዜ በግል ሕይወቱም ሆነ በሀገር ጉዳይ ለገባው ሱባዔ ወዲያውኑ መልስ ሊያገኝ ይችላል፤ እንዲሁም መልሱ ሊዘገይ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ከተሐራሚው ትዕግሥት /መታገሥ/ ይጠበቅበታል፤ «ለምን ላቀረብኩት ጥያቄ ቶሎ መልስ አልተሰጠኝ?» በማለት ማማረርና እግዚአብሔርን መፈታተን ተገቢ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሠራበትና ለሚማጸነውም መልስ የሚሰጥበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡

ይቀጥላል


ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
@Benyaa_s
@Mulexa
@YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!
434 viewsሙሉዓለም አየለ, edited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:20:43 ጾመ ፍልሰታ ክፍል ፫

ሞት በጥር፣በነሐሴ መቃብር

ቶማስም ሰበኗን ደብቆ ይዞ ሐዋርያት ካሉበት ደረሰ። ሐዋርያትንም የእመቤታችን ነገር ምን ደረሰ? አላቸው። ሐዋርያትም እመቤታችን ሱባዔ ገብተን ጌታችን አስከሬኗን ከዕፀ ሕይወት አምጥቶ ሰጥቶን በክብር ቀበርናት አሉት። ቶማስም መልሶ ሞት በጥር፣በነሐሴመቃብር?አላቸው።ሐዋርያትም መለሱለት ቶማስ አትጠራጠር። ቀድሞ ጌታችን በተገለጠ ጊዜ ትንሣኤውን ጣቶቼን በተቸነከሩ እጆችህ ካላስገባሁ ብለህ የደረሰብህን ታውቃለህ አሁንም የእመቤታችንን መቀበር አላመንክምን? አሉት። ቶማስ ግን ሐዋርያትን ይዞ ወደ መቃብሯ ሔደ። መቃብሯን ከፍተው ሲመለከቱ ሐዋርያት ደነገጡ። በዚህን ጊዜ ቶማስ አታምኑኝም ብየ ነው እንጂ እመቤታችን አርጋለች። ስታርግም በደመና ከሀገረ ስብከቴ ስመጣ ተገናኘን ለምልክቱም ይኸው የቀበራችሁበት ሰበን አላቸው።ሐዋርያትም ለበረከት ሰበኗን ተከፋፍለው ወደየሀገረ ስብከታቸው ሔዱ።

ይቀጥላል


ውድ የ ሐመረ ኖኅ ተከታታዮች ለ ሀሳብ አስተያየት እና ጥቆማ ይህን አድራሻ ይጠቀሙ
@Benyaa_s
@Mulexa
@YEAWEDIMERITE

ሐመረ ኖኅ!!!
530 viewsሙሉዓለም አየለ, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:23 ንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡

#ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/

ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራእይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ምንጭ:-Info:- Mk website
#ዓውደ ምህረት የኛ

@AwediMeherit
@AwediMeherit
1.1K views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:23 #የሱባዔ ዓይነቶች

#የግል ሱባዔ/ዝግ ሱባዔ/

የግል ሱባዔ አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ በቤትና በአመቺ ቦታ የሚይዘው ማንም ሰው ሳያየው በግሉ የጸሎት በኣቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው እንዲሰማው በኅቡዕ የሚፈጽመው ሱባዔ ነው፡፡ ማቴ.6፡5-13፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ አንድ ሰው ሱባዔ ሲገባ ዘጋ ይባላል፡፡ ዝግ ሱባዔ የያዘ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ይዞ ወደ በኣቱ ከተከተተ በኋላ ሱባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከሰው አይገናኝም፡፡ መዝ. 101-6-7፡፡

#የማኅበር ሱባዔ
የማኅበር ሱባዔ የሚባለው ካህናት፣ ምእመናን ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች በአንድ ሆነው በቤተ ክርስቲያንና አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው የሚገቡት ሱባዔ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ምእመናን ወደ እግዚአብሔር በመሄድ ይጸልዩ ነበር፡፡ 1ኛ ሳሙ.1፡9፤ መዝ.121፡1፤ ሉቃ.18፡10-14፡፡
በሐዲስ ኪዳንም የሐዋርያት ተከታዮች የኾኑ መነኮሳት፣ ካህናትና ምእመናን በገዳማት፣ በአድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ የጽዋ ማኅበርተኞች ስለ ማኅበራቸው ጥንካሬና ከማኅበርተኞቹ መካከል አንዱ ችግር ሲገጥመው የማኅበር ሱባኤ ይያዛል፡፡.

#የዐዋጅ ሱባዔ

የዐዋጅ ሱባዔ በአገር ላይ ድንገተኛ አደጋ፣ አባር ቸነፈርና ጦርነት ሲነደ እንዲሁም ለማኅበረ ምእመናን አስጊ የሆነ መቅሰፍት ሲከሰት፣ እግዚአብሔር መሽቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ ዓይነት ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ሱባዔ የነነዌ ሰዎችና በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ እስራኤላውያን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለሦስት ቀን ከመብል ከመጠጥ ተከልክለው በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔር መዓቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ አድርገዋል፡፡ ሌላው በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ አይሁድ በአስቴር ትእዛዝ የያዙት ሱባዔ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚያን ዘመን አርጤክስስ አይሁድ በያሉበት እንዲገደሉ በማዘዙ ከዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ለመዳን አይሁድ በዐዋጅ ሱባዔ ገብተዋል፡፡ አስቴር ገብታ ንጉሡን ስታናግረው ሌላው ሕዝብ በውጭ ዐዋጅ ዐውጀው ሱባዔ ገብተው ፈጣሪያቸውን ተማፅነዋል፡፡ አስቴር 4፡16 - 28፡፡
በአገራችንም ይህን የመሰለ የዐዋጅ ሱባዔ በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ተደርጓል፡፡ ፋሽስት ጣልያን አገራችንን በመውረር ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ድንበሯን አልፎ በመጣበት ወቅት ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፡- «ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ ርዳኝ» በማለት የዐዋጅ ሱባዔ መያዛቸው ይነገራል፡፡ በዚህም መሠረት በየገዳማቱ ምሕላ ተይዟል፤ ንጉሡም ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው ዓለምን እጅግ ያስደነቀ ጥቁሮችን ለነጻነታቸው እንዲነሣሱ የሚያስችል ፋና ወጊ የሆነ ድል አግኝተው አገራችንን ለቅኝ ግዛት ያሰበውን ፋሽስት ጣልያንን ማሸነፋቸው በከፍተኛ ስሜት የምናስታውሰው ነው፡፡

#ቅድመ ሱባዔ(ከሱባዔ በፊት) ዝግጅት

ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት አስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት አለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሐ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ አባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሐ አባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው አንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዐቅምንና ችሎታን አገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው ሱባዔ የሚገባው አጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በአጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሐራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በአጽዋማት ወቅት ብዙ አባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከአባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ አይያዝም» የሚል አቋም ለመያዝ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ከአጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የሚያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግ ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ አያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና አድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡

#ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/

በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀልኸ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሐራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማ
809 views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:22 #ሱባዔ ነቢያት

እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ ቀደምት ነቢያት በተነሡበት ዘመን ቅደም ተከተል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና ዳግም መምጣት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ሱባዔም ቆጥረዋል፡፡ ኢሳ.7.14፡፡ መዝ.49.3፡፡ ዘካ.13.6፤ ዘካ.14.1፡፡ የአንዱ ነቢይ ትንቢታዊ ንግግርና ሱባኤ በአነጋገርና በአቆጣጠር ከሌላኛው ነቢይ ጋር ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትንቢቱን ሲያናግር ምሳሌውን ሲያስመስል ጐዳናው ለየቅል በመሆኑ ነው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፡፡» እንዲል፡፡ ዕብ.1.1፡፡ የአቆጣጠር ስልታ ቸውና የሱባዔ መንገዳቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን አንድ ነው፡፡

#ሱባዔ አዳም

አዳም ትንቢት በመናገርና ሱባዔ በመቁጠር የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ምክንያቱም በገነት ሰባት ዓመት ከአንድ ወር ከዐሥራ ሰባት ቀን በተድላና በደስታ ከኖረ በኋላ ሕግ በማፍረሱና የፈጣሪውን ቃል በመጣሱ ያለምንም ትካዜና ጉስቁልና ከሚኖርበት ዔደን ገነት ተባርሯል፡፡ ዘፍ.3.24፡፡ እርሱም ፈጣሪው እንዲታረቀው፣ በዐይነ ምሕረት እንዲጐበኘው፣ ቅዝቃዜው ሰውነት ከሚቆራርጥ ባሕር ውስጥ በመቆም ለሠላሳ አምስት ቀን /አምስት ሱባዔ/ ሱባዔ ገብቷል፡፡ በባሕርዩ የሰውን ልጅ እንግልት የማይወድ ቸሩ ፈጣሪ የአዳምን ፈጽሞ መጸጸት ተመልክቶ «በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእቤዝወከ በመስቀልየ ወበሞትየኸ በአምስት ቀን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ ተስፋውን ሰጠው፡፡ አዳም የተሰጠውን ተስፋ ይዞ በዓለመ ሥጋ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ አመት ከኖረ በኋላ መከራና ችግር ከበዛበት ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
በወንጀል ተከሶ በወኅኒ የተፈረደበት ሰው ከእስር የሚፈታበትን ዕለት በማውጣት በማውረድ ወራቱንና ዓመታቱን እንደሚቆጥር፣ አዳምም በሞት ቢለይም በሲኦል የነፍስ ቅጣት ካለበት ሥፍራ ይኖር ስለነበር የተሰጠውን ተስፋ በማሰብ ሱባዔውን እየቆጠረ የተናገረውን የማያስቀር የማያደርገውን የማይናገር ጌታየ «እነሆ አድንኀለሁ» ብሎ የገባልኝ ዘመን ተፈጸመ፤ ሰዓቱ አሁን ነው፤ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ቸር አምላክ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ፡- «ተንሥኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሡ፤ ሰላም ለኩልክሙ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አዳምን በመከተል ልጆቹም አበው ቅዱሳን ነቢያት ሱባዔ በመግባት የተስፋን ዘመን በመቁጠር በመልካም ግብር ተከትለውታል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ነቢያት በተለያየ ስልት ሱባዔ ቆጥረዋል፤ እኛም ሱባዔ ከቆጠሩ ነቢያት የተወሰኑትን በዚህ ጽሑፍ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

#ሱባዔ ሔኖክ

ጻድቁ ሔኖክ፣ የያሬድ ልጅ ሲሆን፣ በትውልድ ከአዳም ሰባተኛ ነው፡፡ እርሱም በሕይወቱ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ቤት ንብረቱን በመተው በሱባዔና በትሕርምት እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡ ፍጹም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መልካም ግብር ተመስክ ሮለታል፡፡ «ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡» ዘፍ.5.22፡፡ ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የሱባዔውን ዋጋ ቅዱስ መንፈሱን በረድኤት ስለ አሳደረበት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ በሰማይ ተሰውሮ ሳለ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ፀሐይና ጨረቃ አመላለስ /ዑደት/ የሚተርክ በስሙ የተሰየመውን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘፍ.5 21-24፡፡ ይሁዳ ቁ.14፡፡ ሔኖክ 1.9፡፡
ሱባዔ ሔኖክ የሚባለው ነቢዩ ሔኖክ በመስፈርት የቆጠረው ሱባዔ ነው፡፡ መስፈርቱ /ማባዣ ቁጥር/ 35 ሲሆን 35'19 ሲበዛ በውጤቱ 685 ዓመት ይሆናል፡፡ 685'12 ስናባዛው 7980 ይሆናል፡፡ ይኸውም ሐሳብ የሚያስረዳው ስለክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን የደረስንበት ዘመን 7497 ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በ5500 ዓመት ላይ 1997 ዓመትን መደመር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ከላይ ያስቀመጥነውን 7497 ዓመት ይሰጠናል፡፡ በነቢዩ ሔኖክ አቆጣጠር መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ በ7980 ይሆናል፡፡ ከላይ ሔኖክ የቀመረውን ቁጥር ይዘን ከ7980 ዓመት ላይ አሁን ያለንበትን ዘመን /1997/ ስንቀንስ 483 ዓመት እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በሔኖክ ሱባዔ መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን 483 ዓመት ይቀራል፡፡

#ሱባዔ ዳዊት

ነቢዩ ዳዊት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ ንጉሥ ነበር፡፡ ዘመነ መንግሥቱ 1011-971 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደ ነበር ይታመናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ልበ አምላክ እንደ መሆኑ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ ይኽውም ቀመረ ዳዊት በመባል ይታወቃል፡፡ «እስመ ዐሠርቱ ምእት ዓመት በቅድሜከ፤ ከመ ዕለት እንተ ትማልም ኃለፈት፤ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትላንት ቀን»፡፡ /መዝ.89.4/ የሚለውን መምህራን ሲቆጥሩት 1140 ዓመት ይሆናል፡፡ ይኸውም በጌታ ዘንድ 1140 ዓመት እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ ይህም ለዳዊት ሱባዔ መቁጠሪያ /መሥፈሪያ/ ሆኖ አገልግሏል፤ 1140’7= 7980 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በ7980 ዓመት ክርስቶስ ዳግም እንደ ሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡

#ሱባዔ ዳንኤል

ነቢዩ ዳንኤል ምድቡ ከዐበይት ነቢያት ነው፡፡ እስራኤል ወደ ባቢሎን ሲማረኩ ተማርኮ ወደ ባቢሎን ወርዷል፡፡ እርሱም ስለ ክርስቶስ መምጣት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔም ቆጥሯል፡፡ «ሰብአ ሰንበታተ አድሞሙ ለሕዝብከ፤ ሰባ ሰንበት ወገኖችህን ቅጠራቸው፡፡» ይኸውም ክርስቶስ ከ490 ዓመት በኋላ ሰው መሆኑን የሚያመለክት ትንቢት ነው፡፡ እንዲሁም «እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ትትሐነፅ መቅደስ ወእምዝ ትትመዘበር፤ እስከ ንጉሥ ክርስቶስ ድረስ መቅደስ ትታነፃለች በኋላም ትፈርሳለች» ሲል ተናግሯል፡፡
የአቆጣጠር ስልቱም በዓመት ሲሆን ይኸውም ሰባቱን ዓመት አንድ እያሉ መቁጠር ነው፡፡ ይኽውም ሱባዔ ሰንበት ይባላል፡፡ ዳንኤል ሱባዔ ከቆጠረበትና ትንቢት ከተናገረበት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ሚወለድ 490 ይሆናል፡፡ መስፈርቱ /ማባዣው/ ሰባት ስለሆነ 7’70 ስናባዛው 490 እናገኛለን፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሱባዔ ከቆጠረና ትንቢት ከተናገረ ከ490 ዓመት በኋላ የክርስቶስን መወለድ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ቅዱሳን ነቢያት አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሱባዔ ገብተው በትሕርምት በመኖራቸው ድንቅ የሆነውን የክርስቶስን ልደትና ዳግም ምጽአት ለመተንበይ ችለዋል፡፡ ሱባዔ መግባት የራቀን ለማቅረብ የረቀቀን ለማጉላት ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስገኝ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

**** ይቀጥላል*****
502 views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:22 #ሱባዔ

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ቆየ ሰነበተ ዘገየ ሰባት ማለት ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጓሜውም ደግሞ አንድ ሰው ከዚህ ቀን እከዚህ ቀን ድረስ ፈጣሪዬን በጸሎት እገናኛለሁብሎ የሚያቅደው ዕቅድ ነው። ሰባት ቁጥር በእስራኤላዊያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር አረፈ እንዲል በጸሎት የሚተጉ ምዕመናንም በቀን ሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል ። ሱባዔ የተጀመረው ከመጀመሪያው ሰው አዳም ውድቀት በኋላ ነው ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዴት እንደሚጸለይ እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። ለአዳምም የጸሎት ጊዜያትን አስተምረውት አስተምረውት ነበርና ጥፈቱን አምኖ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔርም በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ገባለት ።



ሱባዔ ለምንምክንያት እንገባልን ቢሉ የመጀመሪያው የሚሆነው የሰው ልጅ በባህሪው ኃጢአት የሚስማማው ነው በሥጋ ሰውነቱ ፈጣሪን ይበድላል በፈጸመው በደል / ኃጢአት/ ሕሊናው ይወቅሰዋል በዚህም ያዝናል ይጸጸታል በሰራው ኃጢአትም ልቡ ይደነግጣል በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት ሲል ሲል ሱባዔ ይገባል ።እግዚአብሔርን ለመማፀን የሚገባ ሱባዔ አለ ። ማንኛውም ሰው ሱባዔ በገባ ቁጥር ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማጽኖ ሊኖረው ይገባል ምንም የምንለምነውና የምንጠይቀው ነገር ሳይኖር ሰባዔውን ብንገባ የምናገኘው ምንም አይነት መልስ አይኖርም
ስለዚህ ተማፅኖ ሊኖረን ይገባል ። ያለ ምንም ቅድመ ሆኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔው በኋላ ምን እንደተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖራቸው ሱባዔ በመግባታቸው የሚገኙት ነገር አይኖርም ይህን ተገንዝበው ከመግባታቸው በፊት የሚገቡበትን ምክንያት ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው ። ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶቻችን ደማቸውን ካፈሰሱበት አጥንታቸውን ከከሰከሱበት ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሰሩበት ቦታ ገዳማቸውና አድባራት ላይ የሚገባ ሱባዔ ከቅዱሳኑ ረድኤት ተካፋይ ይደርጋል ። ሱባዔ የተደበቀን ምሥጢር የሚገለጥበት ቁልፍ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ነው ቅዱሳን አባቶቻችን ያዩት እራይ ምሥጢሩና ትርጉሙ አልገለጥ ሲላቸው ሱባዔ ይገቡ ነበር እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነ ነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢሩንና ትርጉሙን ይገልጥላቸዋል ። ነቢዬ ዕዝራ የመጽሐፍታት ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ገባ እግዚአብሔር አምላክም ሁሉን ገለጸለት የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍታት ደግሞ ለመጻፍ ችሏል ይህ ምሥጢር የተገለጠለት በሱባዔ ነው ።

ከብሉይ ጀምሮ ያሉ የሱባዔ አባቶቻችን የገቡት ሱባዔ ሱባዔ አዳም ፣ ሱባዔ ሔኖክ ሱባዔ ነብያት
፣ሱባዔ ዳንኤል ሱባዔ ዳዊት በተጨማሪም የግል ሱባዔ የማኀበር ሱባዔ የአዋጅ ሱባዔ በመባል ይታወቃሉ በሐዲስ ኪዳን ከአራት ቀን በኋላ የምገባ ሐዋርያት የገቡት ሱባዔ ነው የፍልሰታ ሱባዔ በዚህ ሱባዔ ተሰውሮ የነበረውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋ የተገኘበት ትንሣኤዋ እንዲገለጥላቸው የተገባ ሱባዔ ነው ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን 14 ቀን ያክል በጻም በጸሎት ተማጽነው ትንሣኤዋን ገለጠችላቸው ። እንግዲህ ሱባዔ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል ወቅቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ስባዔ እንደ መሆኑ መጠን እኛም የሐዋርያቱን ፈለግ በመከተል በንጹሕ ልቦና በትሁት መንፈስ ሆነን የእናታችን ትንሣኤ ይገለጥልን ዘንድ በሱባዔው እንትጋ ። ለሐዋርያቱ በሙሉ የልባቸውን መሻት የፈጸመች የጌታችን እናት ድንግል ማርያም የእኛንም የልባችንን ትፈጽምልናለች። ወቅቱን የጾም፣የጸሎት፣የስግደት፣ የምጽዋት፣ ስለ ሀገራችን ኢትዮጲያ የምናለቅስበት ነው ። ስለዚህ ሁላችን በሱባዔው እንበርታ

“በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።”
— ሐዋርያት 2፥42
#ዓውደ ምህረት የእናንተ

@AwediMeherit
@AwediMeherit

.....ይቆየን.......
ምንጭ :-እናት ማህበሬ ምክሐ ደናግል ሰሌዴ መጽሔት ሐምሌ ና ነሀሴ2010ዓ.ም የተለጠፈ
421 views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:22
397 views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 22:22:22
ብንሰባሰብ እርሱ በመካከላችን እንደሚገኝ የገባልንን ቃል ኪዳን
መሠረት በማድረግ (ማቴ. ፲፰፥፳)፣ ዅላችንም በጾመ ፍልሰታ
ሳምንታት በጌታችን፣ በእመቤታችንና በቅዱሳን ሐዋርያት ስም በቤተ
ክርስቲያን ተሰባስበን ቅዱሳት መጻሕፍትን ከመማር ባሻገር ብንጾም፣
ብንጸልይ፣ ብናስቀድስ፤ እንደዚሁም ሥጋውን ደሙን ብንቀበል
በበረከት ላይ በረከትን፤ በጸጋ ላይ ጸጋን እናገኛለን፡፡ በኋላም
ሰማያዊውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ለመውረስ እንችላለን፡፡
ስለኾነም የእመቤታችንን ዕረፍትና ትንሣኤ በማሰብ ከልጇ ከወዳጇ
የሚገኘውን ጸጋና በረከት ተስፋ በማድረግ የአባቶቻችንንና
የእናቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በየዓመቱ ጾመ ፍልሰታን እንጾማለን፤
የምንችል ደግሞ ንስሐ ገብተን አስቀድሰን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር
ደሙን እንቀበላለን፡፡ ነገር ግን በሕግ የተከለከለ እስኪመስል ድረስ
በዚህ ወቅትም ኾነ በሌላ ጊዜ ሥጋውን ደሙን የሚቀበሉ ወጣቶች
ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህም አረጋውያንና ሕፃናት ብቻ ሳይኾኑ
ወጣቶችም ጭምር የመቍረብና የመዳን ክርስቲያናዊ መብት
እንዳለን በመረዳት ራሳችንን ገዝተን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውንና
ክቡር ደሙን በመቀበል መንግሥቱን ለመውረስ መዘጋጀት
ይኖርብናል፡፡ አምላካችን በማይታበል ቃሉ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ፤
ደሜንም የሚጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው›› በማለት ተናግሯልና
(ዮሐ. ፮፥፶፬)፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን የቅድስት
ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና በረከት
አይለየን፡፡

ምንጭ :-ዲያቆን ኤፍሬም የኔሰው
ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም( ማህበረ ቅዱሳን)
ዓውደ ምህረት የእናንተ

@AwediMeherit
@AwediMeherit

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
420 views ተርቢኖስ ሰብስቤ , 19:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ