Get Mystery Box with random crypto!

​​​​ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት በጽራሐ ጽዮን መ | ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች 📜

​​​​ጾመ ሐዋርያት/የሰኔ ጾም
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬

ጾመ ሐዋርያት ሐዋርያት በጽራሐ ጽዮን መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ወደ አገልግሎት ከመግባታቸውና ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከመበተናቸው በፊት የጾሙት ጾም ነው፡፡ የጾሙበትም ምክንያት በማርቆስ ፪፥፳ እና በማቴወስ ፱፥፲፬ ላይ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ይህን ጾም ሐዋርያት ጾመው በረከት ያገኙበት ከመሆኑ ባሻገር ጌታችን ጾሞ ጹሙ እንዳላቸው እነርሱም ደግሞ ተከታይዎቻቸውን ያንኑ መልዕክት የደገሙበት ነው፡፡ በክርስቶስ ደም መሰረት ላይ እና በሐዋርያት ትምህርትና ትውፊት ላይ የተመሰረተችው ቤተ ክርስቲያናችንም ይህንን ጾም በዐዋጅ እንድንጾመው ሥርዓት ሠርታልናለች፡፡

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ የጾሙት እንደመሆኑ መጠን ከጌታ ትንሣኤ ከሃምሳኛው ቀን በኋላ ማለትም ከጰራቅሊጦስ ዕሁድ ማግስት ሰኞ ጀምሮ በቅዱስ ጳውሎስና በቅዱስ ጴጥርስ በዓለ እረፍት መታሰቢያ በሆነው ሐምሌ አምስት ቀን ፍጻሜውን ያገኛል፡፡ የቀናቱ ብዛትም በዐቢይ ጾም መባቻ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ጾሙን የበረከት፣ የንስሐ ፣ ደዌን ማራቂያ፣ ዲያቢሎስን ድል መንሻ ያድርግልን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!

አቅራቢ ፦

https://t.me/+YZYAOpgOgns2Njdk

@EOTC_library
@EOTC_library_bot