Get Mystery Box with random crypto!

#ፈሳሽና_ጠረን አንዲት ሴት ልጅ ለአቅመ ኤዋን ከደረሰች በሰውነት ላይ የተለያዩ ለውጦችን ማሳየቷ | ላንቺ ብቻ

#ፈሳሽና_ጠረን

አንዲት ሴት ልጅ ለአቅመ ኤዋን ከደረሰች በሰውነት ላይ የተለያዩ ለውጦችን ማሳየቷ አይቀሬ ነው ። ከዚህ ውስጥ አንዱ የብልት ፈሳሽ በፓንቷ ላይ ማየት ነው ። ይህ ፈሳሽ ተፈጥሯዊ የሆነ እንደሆነ ይናገራሉ ። ግን የተለየ ባህሪ ተጓዳኝ ከሆነ የጤና እክል መሆኑን ይናገራሉ ።

ለምሳሌ ጤናማ ብልት ጠረን አለው ወይ ? መልሱ አዎ ነው ።

በዚህን ጊዜ በብልት ውስጥ ያለው የአሲድ ፒ ኤች መጠን ከፍ ካለ ብልት ውስጥ ያሉት ባክቴሪያዎች ይረበሻሉ ። በዚህም ምክንያት ጠረን ሊያመጣ ይችላል ። እንደሚሉትም ችግር ያለው ማሳከክ ፣ ማቃጠል ፣ ያለው ከሆነ ነው ።

ሁለተኛ ፓንት ላይ የሚታየው ፈሳሽ ተፈጥሯዊ ነው ወይ ? መልሱ አዎ የሚል ነው ።

ብልት የራሱ የሆነ መዋቅር አለው ። ከነዛም መካከል አንዱ ብልት እራሱን የሚያፀዳበትና የሚዘጋጅበት መንገድ ነው ። ብልትን የሚጎዱ ባክቴሪያዎች እንዳይባዙና ችግር እንዳይፈጥሩ ከማህፀን በር አንገት ጀምሮ እራሱን በማፅዳት ለምንም ነገር ዝግጁ ያደርጋል ። በዚህም አማካኝነት ብልት እርጥብ ሆኖ እንዲቆይ ያደርጋል ። ስለዚህ ፈሳሽ ማየቱ ተፈጥሯዊ ጤናማም ነው ። ነገር ግን ቀለሙ ቢጫ ፣አረንጓዴ ፣ ቡኒ ፣ ወፍራም ወተት የመሰለና ማሳከክ ማቃጠል እንዲሁም ጠረን ያለው ከሆነ ዶክተር ማማከር የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ መሆናችሁን ተረጂ ። መጨነቅ አያስፈልግም ።