Get Mystery Box with random crypto!

#የማህጸን #በር ካንሰር (#cervical #cancer) ************************* | ላንቺ ብቻ

#የማህጸን #በር ካንሰር (#cervical #cancer)
************************************
የማህፀን በር ካንሰር የሚከሰተው የመሀጸን በር ላይ ያሉት ህዋሶች ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲያድጉ ነው፡፡ የመሀፀን በር የምንለው ከታችኛው ከመሀጸን ክፍል ወደ ሴት ብልት የሚከፈተው የሲሊንደር ቅርፅ ያለው ህብረህዋስ ነው፡፡


የማኅጸን በር ካንሰር ምልክቶች
በበሸታው የመጀመርያ ጊዜያት ውስጥ ምልክቶቹ ጎልተው አይታዩም፡፡
የግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚፈጽሙበት ጊዜ ህመም
ያልተለመደ የሴት ብልት ደም መፍሰስ ፣ ለምሳሌ ከወሲብ በኋላ ፣ በወር አበባ ጊዜ፣ ከወር አበባ በኋላ ፣ ወይም ከእርግዝና ምርመራ በኋላ
ያልተለመደ የሴት ብልት ፈሳሽ
ክብደት መቀነስ እና የምግብ ፍላጎት ማጣት
የአጥንት ህመም
የሆድ ህመም
ድካም
የጎን እና ጎን ህመም
በማረጥ ጊዜ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ለመሀጸን በር ካንሰር ተጋላጭ የሚሆኑት እነማን ናቸው

HPV (human papilloma virus) በተደጋጋሚ የሚጠቁ ሰዎች ከተለያዩ ሰዎች ጋር የግብርስጋ ግንኙነት መፈፀም .
የሰውነትን የበሸታ የመከላከል አቅምን የሚቀንሱ በሸታዎች ሲኖሩ ለምሳሌ ፡ ኤች.አይ.ቪ
ሲጋራ ማጨስ .
ለረጅም ጊዜ በአፍ የሚዋጡ የወሊድ መቆጣጣጠሪያዎችን መጠቀም
ከ14 አመት እድሜ በላይ የሆኑ ሴቶች
3 እና ከዛ በላይ ልጆችን መውለድ
በለጋ እድሜ የግብረስጋ ግንኙነት መጀመር ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡


የበሸታው ምልክቶቹ ምንድን ናቸው???
በበሸታው የመጀመርያ ጊዜያት ውስጥ ምልክቶቹ ጎልተው አይታዩም፡፡
ከመሀፀን ደም መፍሰስ
ከግንኙነት በኃላ የደም መፍሰስ
መጥፎ ጠረን ያለው ከመሀፀን የሚወጣ ፈሳሽ
የጎን እና ጎን ህመም
ደም የቀላቀለ ፈሳሽ ወይም ሽንት
በማረጥ ጊዜ ደም መፍሰስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡


ህክምናዎቹ ፡- እንደ ደረጃው ቢለያይም
ቀዶ ጥገና
የጨረር ህክምና እና
የመድሀኒት ህክምና ናቸው፡፡

@onlyfemaleb