Get Mystery Box with random crypto!

#ወንድምህ_ወዴት_ነው ?? አዋ ወንድምህ ወዴት ነው ? አላውቅም : ? እንዴት # እኔ የወንድሜ | አናሲሞስ

#ወንድምህ_ወዴት_ነው ??

አዋ ወንድምህ ወዴት ነው ?
አላውቅም : ?
እንዴት # እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝ ትላለክ ?
ካንተ በፈት ለወንድምክ የምቀድም ማነው ?
ካንተ በስቲያ ለወንድምክ የሚቀርብ አለ ?
እኸኸ ቆይ ልጠይቅህ
ምን አደረግህ ? ምንስ አደረከው
ጠላኸው
ገፋኸው
እስቲ ንገረኝ ሰደድከው
ገደልከው እንዴ
ምነው # የእቴ ልጅ
ወንድምህ የእናትህ ልጅ መሆኑን እንዴት አጣኸው ?
የአንድ አብራክ ክፋይ መሆንህን የአንድ ስጋ ፍላጭ
የአጥንትህም ቁራጭ መሆኑን ለምን አጣኸው ?
ለምንስ ብለክ ነው ጠልተክ የገፋኸው ?
ምንስ ልታተርፍ ነው አሳደ የገደልከው ?
ወዩው # ሰው ሰው መሆኑ ጠፋው !
እንኳን # የወንድምክ....ወንድምክ ራሱ ያንተ አልነበረምን ?
ሺ ዓመት ላትኖር ለምን ወንድምህን አጣኸው?
ብትፈልገው ላታገኝ ለምንስ አራከው?
እናትክ ኢትዮ እንዲህ ትጠይቅሀለች
የወንድምክ እናት ኢትዮ
ላንተም ለሱም በቅታ የምትተርፍ ኢትዮ እንዲህ ትጠየቅሀለች
የኢትዮ አምላክ እንድህ ይጠይቅሀል ?
ወንድምህ ወዴት ነው ?
የትስ አደረስከው ?
በቀለም : ቁመት በጎሳ
ዘር ሀረግ : በሀብትና ንብረት
በቋንቋ ንግርት
በታርክ ትውፊት
በትውልድ ሀገር
በምድር ቀመር
ለይተክ ቆጥረክ : ወንድምህን የት አደረስከው?

ሰወ መሆን ሰውነት
ሰወነት ነው ሰዕባዊነት
ሃይማኖት ክርስትና ዕምነት
መሠረት ነው ለመልካምነት
ቅዱስ ቃሉ የሀይማኖትክ መርህ
ወንድሞች በህብረት ብቀመጡ
መልካም ነው ይላል አስተምሮቱ
ወንድምነት ልኩ
ለዕውር አይን
ለአንካሳ እግር
ለደሀ አደጉ አባት መሆን ነው
የሰው ልጅ ለሰው ሰው መሆን ነው
ስማኝ ብንገርሀማ
ከነገድ ቋንቋ ከወገን ህዝብም
የተዋጀ ለአምላካችን መንግስትና
ካህን የሆነ ወድ ወንድም አለክ
ደግሜ ልንገርክ ስማኝ
የጥላቻ : ክፋት የአመፅና ደባ
ስይፋህን ወደ ሰገባው መልስና
በል ወንድምህን ወደድ ክፋትን አስወጣውና




Only @አናሲሞስ Click Now
---------------------------------------------------
ተወዳጁ ቻናላችንን ይቀላቀላሉ፦
ይ ቀ ላ ቀ ሉ

@Onesumos
@Onesumos