Get Mystery Box with random crypto!

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በአዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ነባር የኮንክሪት | Safaricom Ethiopia

ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር በአዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ነባር የኮንክሪት ምሰሶዎች ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ኢንተርኔት አገልግሎት ማሰራጫ የአየር ላይ ገመድ ለመዘርጋት የሚያስችለንን የሦስት ዓመታት ስምምነት ተፈራርመናል፡፡ የአየር ላይ ገመዶች ለጥገና እና ለአገር አቀፍ ዝርጋታ አንጻራዊ ቅለት ያለው ነው፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና የሥራ አስፈጻሚ አኑዋር ሱሳ “አገልግሎቶቻችን በተለያዩ ደረጃዎችና ሂደት የምንጀምር ሲሆን ይህንን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር አብረን በመሥራታችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል፡፡ ይህ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የአጋርነት ስምምነት ለኔትወርክ ግንባታችን የሚያስፈልጉንን ትክክለኛ ግብዓቶች እንድናገኝ፣ ግንባታችንንም በጠንካራ መሠረተ ልማት ላይ እና ከልዩ ልዩ አጋሮች ጋር ለመሥራት ምሳሌ የሚሆን ድጋፍ ላይ ተመርኩዘን እንድንቀጥል ያስችለናል፡፡” ብለዋል፡፡

አዲስ ኔትወርክ እየገነባን በምንገኝበት በዚህ ወቅት፣ በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም ቤቶች እና የንግድ ሥራ ድርጅቶች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በመሠረተ ልማት እና በስትራቴጂክ አጋርነት ላይ ለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ቅድሚያ እየሰጠን እንገኛለን፡፡
#SafaricomEthiopia
https://t.me/OfficialSafaricom