Get Mystery Box with random crypto!

መናሄ በግእዙ- እፀ መናሂ 1. ጆሮው ለመገለ አፍንጫው መጥፎ ጠረን ላለውጉሮሮው ለተዘጋ የስሩ | 🌿🌿መርጌታ ንጉስ የባህል ህክምና አገልግሎት መስጫ🍀🍀

መናሄ በግእዙ- እፀ መናሂ
1. ጆሮው ለመገለ አፍንጫው መጥፎ ጠረን ላለውጉሮሮው ለተዘጋ የስሩን ቅርፍትና ከወርቅ በሜዳ ጋር በቅቤ አንጥሮ በአፍንጫው ማድረግ ነው፡፡
2.ለብብት ቅርናት የእፀመናሂን ስር በቅቤ አንጥሮ መቀባት ወይም ብቻውን መቀባት ነው፡፡
3.ለልብ ደዌ ከአሚራ ጋር በመጠጫ መሳብ ነው ፡፡
4 .ለቁርጥማት ለውጋት ለራስ ህመም ለሆድ ደዌ ከቅቤ ጋር አንጥሮ መጠጣት ነው፡፡
5.ለማንኛውም ደዌ ሥራይ ከወርቅ በሜዳ ጋር ወቅጦ በቅቤ አንጥሮ በባዶ ሆድ መጠጣት ነው ፡፡
6.ለራስ ፍልጠት ከሺነት ቅርፍት ጋር ወቅጦ ሲያመው ዱቄቱን በአፍንጫው ይሳብ፡፡
7.ለመካን እሴት ከወተት ጋር እያፈላች ደጋግማ ትጠጣ ፡፡
8.ለፎረፎር ከደረጭ መረጭ ጋር በቅቤ ለውሶ በፀሐይ ማቅለጥ የቀለጠውን ንጥር ቅቤ መቀባት ነው ፡፡
9.ለሥጋ ደዌ እከክ ለመሰለው የእፀመናሂና የጠንበለል ቅጠላቸውን በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው ፡፡
10.እንደ እከክ ሰውነቱን ለሚያሳክከው የጠንበለል የዋጊኖስ የእፀመናሂ ሥራቸውን ወቅጦ በቅቤ ለውሶ መቀባት ፀሐይ መመታት ታጥቦ አንደገና ተቀብቶ እሳት መሞቅ አለበት፡፡
11.ጉሮሮው ለአበጠ ከወርቅ በሜዳ ጋር ደቁሶ በቅቤ ለውሶ መቀባት ነው፡፡
12.ለመፍትሔ ለሥራይ ለቁመኛ ለቡዳ ሥሩን ከግሜ አረግ /ግምአረግ/ ሥር ጋር ወቅጦ ዘፍዝፎ መታጠብ ፡፡ለሰባት ቀን ያህል መጠመቅ አለበት፡፡

መጽሐፈ ፈውስ