የጥሪ ማስታወቂያ #OdabultumUniversity በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱ | Oda Bultum University
የጥሪ ማስታወቂያ
#OdabultumUniversity
በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 10 እና 11 ይሆናል፡፡
ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-
የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦርጅናልና ኮፒ
የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጅናልና ኮፒ
ከ9-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪብት ኦርጅናልና ኮፒ
አራት ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም
አንሶላ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ www.obu.edu.et ወይም https://t.me/OBURegistrar ይጎብኙ
የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት
ተማሪ ነክ መረጃዎችን እንዘግባለን