የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረትን በ #ፕሬዝዳንትነት እንዲመራ ተመረጥ
የቀድሞ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ #ኦሊ_በዳኔ የስራ ጊዜያቸውን በማጠናቀቃቸው እንዲሁም ከዚህ በፊት በሟሟያ ምርጫ ተመርጦ የነበረው ስራ-አስፈፃሚ የስራ ጊዜውን በመጨረሱ ህብረቱ በትላንትናው እለት በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተካሄደው 41ኛ የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት መደበኛ ጉባዔ ላይ ምልዐተ ጉባዔው ለቀጣይ ሁለት አመታት ህብረቱን የሚመሩ አዳዲስ ስራ-አስፈፃሚዎችን በመመሪያው መሰረት አወዳድሮ መርጧል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት እያደረገ ባለው 41ኛ መደበኛ ጉባዔ የ #ወልቂጤ_ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ #ሚካኤል_ያቦነሽ የኢትዮጲያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።
ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
@ethiouniversity1bot
Share share
ለተጨማሪ መረጃ
╔═══════════╗
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
@ethiouniversity1
╚═══════════╝