Get Mystery Box with random crypto!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ አስመረቀ። ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ464, | Oda Bultum University

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ያስገነባውን ዘመናዊ የመምህራን መኖሪያ አስመረቀ።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ከ464,000,000 ብር (አራት መቶ ስልሳ አራት ሚሊዮን ብር) በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባው የመምህራን መኖሪያ አፓርታማ በዛሬው ዕለት በመመረቅ ላይ ይገኛል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር በከፊልም ቢሆን ለማቃለልና በተለይም መምህራን በዩኒቨርስቲው አቅራቢያ ሆነው በተረጋጋ ሁኔታ መደበኛ ስራቸውን ለማከናወን እንዲያግዛቸው ታስቦ በዩኒቨርሲቲው አቅራቢያ በጉብሬ ክፍለ ከተማ የተገነባ ነው።

ግንባታው በ1719 ካሬ ላይ ያረፈ ሲሆን አራት ብሎኮች አሉት። ባለ ሁለት መኝታ ያላቸው 72 ቤቶችን፤ ባለ አንድ መኝታ ቤት ያላቸው 120 ቤቶችን እና 60 እስቱዲዮዎች ሲሆኑ በድምሩ 252 አባወራዎችን የሚያስተናግድ የመኖሪያ ክፍሎች ያሉት ነው።

በተጨማሪም ደረጃውን የጠበቀ የኪችን ካቢኔት የተገጠመለት፤ ነዋሪዎችን የዋይፋይ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመስመር ዝርጋታ የተደረገለት፤ የራሱ የሆነ ትራንስፎርመር ተገጥሞለት የተሟላ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ለማድረግ የሚያስችል ሆኖ የተገነባ ፤የውሃ እጥረት እንዳይከሰት በማሰብ የራሱ የሆነ ጥልቅ የመጠጥ ጉድጓድ ውሃ የተቆፈረለት ጭምር ነው።

ለህንጻው ነዋሪዎች አገልግሎት የሚሰጡ 24 ሱቆች ( በእያንዳንዱ ብሎክ 6 ሱቆች) ፤ 4 ካፍቴሪያዎች ( በእያንዳንዱ ብሎክ 1 ሱቅ) ፤ 4 ሱፐር ማርኬት (በየብሎኩ 1 ሱፐርማርኬት)፤ አንድ ፋርማሲ ያለው ሆኖ ለዘመናዊ የአኗኗር ዘዴ አመቺ ሆኖ መገንባቱን ከዩኒቨርስቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine