Get Mystery Box with random crypto!

'ሽማግሌ ስሆን' (ኑዕማን ኢድሪስ) እቴ... ላገባሽ አስቤ ሽማግሌ ብለክ እነዚያ አዛዉንቶች | Nuiman Edris Official

'ሽማግሌ ስሆን'
(ኑዕማን ኢድሪስ)

እቴ...
ላገባሽ አስቤ
ሽማግሌ ብለክ

እነዚያ አዛዉንቶች
ቆንጅናሽን አይተዉ
አሉብሽ ልክክ

ድሮም ሽማግሌ
ገንዘብም ስላላቸዉ
በስሜት የጋሉ

ወጣት ቆንጆ ሲያዩ
ቀና ያለች ሲያዩ
ምርኩዝ ያደርጋሉ

እኔ ሚስኪን ወጣት
ወይ ገንዘብ የለኝ

ሽማግሌ ስሆን
ፍሉሱን ስይዘዉ
ልምጣ መሰለኝ