Get Mystery Box with random crypto!

ዱአና ፀሎት ''''''''''''''' አላህ የፈጠረኝ እኔም የሰላም ሰው፤ እግዜር የፈጠረህ አንተም | ኑ እናንብብ

ዱአና ፀሎት
"""""""""""""""
አላህ የፈጠረኝ እኔም የሰላም ሰው፤
እግዜር የፈጠረህ አንተም የሰላም ሰው፤
ለምን ማን እንዳሻው?
ከልባችን ኩሬ ፍቅርን ያደፍርሰው፤
ለምን ማን እንዳሻው?
የእውነት ዋንጫችን ውሸት ይበርዘው፤
ለምን ማን እንዳሻው?
የእምነት ገመዱን ገዝግዞ ይበጥሰው፤
በል ክንዴን ተንተራስ
እኔም ተጠግቼ ክንድ'ን ልንተራሰው!

ተጣብቀን እንኑር
እቅፍ አርገኝ ጓዴ......
....... እቅፍ ላርግህ ጓዴ፤
እንዲህ ባንሆን ኖሮ
በኛ ደም ከባሪ ሊፈጀን ወንበዴ!

ማንም ከቀመረው
አንገት ብሎ ደፊ የነገር ካራቴ፤
ማንም የሆድ መሪ
ሰውነቴን ትቶ መድቦኝ በእትብቴ፤
በዘር ጎጥ ከፋፍሎ
የትብታቡን ገመድ ቢከተው ባ'ንገቴ፤
ዱአዬ ሸሸገህ
ፀሎትህ መሸገኝ
አወጣኝ እምነትህ አወጣህ እምነቴ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


@getem