Get Mystery Box with random crypto!

​​ | Nigat Inspire

​​<<ለ 7 ቢሊየን ሰው 1 ፀሀይ ነው የምትወጣው እንጂ ለሁሉም የተለያየ ፀሀይ አትወጣም
ፀሀይ ስራዋ መውጣት ነው መሞቅ ያንተ ፋንታ ነው፡፡
አንዳንዶች ፀሀይን በአግባቡ ሞቀዋት ስታይ ለኔ ጨልሞ እንዴት ለነሱ #ፀሀይ ሆነ አትበል እነሱ የተሳካላቸው ከፀሀይዋ አወጣጥ ሳይሆን ከቆሙበት ቦታ ነው፡፡

አዲሷ ፀሀይ አዲስ #እድል ... አዲስ #ተስፋ... አዲስ ስኬት ይዛ በማለዳው ህይወትህን ልታሞቀው ስትወጣ አንተ ዛሬም በትላንት መጥፎ ታሪክህ በእንባ ጥላ ተጠልለህ ሳታሞቅህ ዜናዋን ሳታበስርህ ትገባለች፡፡

ለሁሉም አንድ ፀሀይ ነው የምትወጣው ዛሬም በፍቅር ከመኝታህ ተነስ በፍቅር ውጣ የዛሬዋ ፀሀይ ያንተም ናትና በተስፋ ሙቃት

Share
Comment
@NigatInspire
@NigatInspire