Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና በ2030 አሜሪካን በመብለጥ የዓለም ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት እንደምትሆን ተተነ | NidaTube -ኒዳ ቲዩብ

ቻይና በ2030 አሜሪካን በመብለጥ የዓለም ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት እንደምትሆን ተተነበየ።
በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት የዓለም ቁጥር አንድ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ቻይና እንደምትሆን የምጣኔ ሀብት አማካሪ ድርጅቶች አስታወቁ።

አሁን ላይ የዓለም ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ቻይና በአውሮፓውያኑ 2030 ቁጥር አንድ በመሆን አሜሪካን ልትበልጥ እንደምትችልም ነው የተተነበየው።

የቻይና ኢኮኖሚ በመንግስት ኢንቨስትመንት ላይ ፣በትላልቅ የቴክኖሎጂ ላማትና በሀገር ውስጥ ፍጆታ ላይ ትኩረት በማድረግ የአሜሪካን ቦታ እንደሚረከብም ነው በስፋት እየተገመተ ያለው።

ከብሪታኒያው የኢኮኖሚና ቢዝነስ ምርምር ማዕከል ትንቢያ በተጨማሪም የብድር ኢንሹራንስ ኩባንያ የሆነው ኢዩለር ሄርሜስም ተመሳሳይ ትንቢያ ሰርቷል ተብሏል።

የቤጅንግ እና የዋሸንግተን የንግድ እሰጥ አገባ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና ማሳደሩ ተገልጿል።

በአውሮፓውያኑ 2020 የቻይና ጠቅላላ ኢኮኖሚ 15 ነጥብ 92 ትሪሊየን ዶላር እንደሆነ አይ ኤችኤስ የተባለ ኩባንያ ጠቅሷል። በቀጣዩ ዓመት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ18 ቢሊዮን እንደደረሰም ነው የተነገረው።የአሜሪካ ጠቅላላ ኢኮኖሚ ደግሞ 23 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑም ተገልጿል።

የቤጅንግ እና የዋሸንግተን ፉክክር ኢኮኖሚያዊ ቢመስልም አሁን አሁን ግን ወታደራዊ መልክ እየያዘ መምጣቱም እየተነገረ ነው። ሀገራቱ አሁን ላይ በምጣኔ ሀብት ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው በስፋት እየተወራ ሲሆን መሪዎቹ በጉዳዩ ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።

አል ዐይን