Get Mystery Box with random crypto!

\\\\ ፍቅር ማለት ውዴ \\\\ ወደድኩህ ወደድኩሽ በቃል መባባሉ እምነቱን ጠብቆ ካልከበረ ቃሉ | ገፅ _ማህደር

\\\\ ፍቅር ማለት ውዴ \\\\
ወደድኩህ ወደድኩሽ በቃል መባባሉ
እምነቱን ጠብቆ ካልከበረ ቃሉ
በምላስ ቢዘመረ ቢከብድም ቢቀልም
እምነት ከተጣሰ ፍቅር አይባልም
ፍቅር ብሎ ማለት
በእውነተኛ ፍቅር መውደድ ካጣመረን
ጅምራችን አምሮ በአንድ ላይ ካኖረን
ጥንዶች እየተባልን ሁነን አቻ ለአቻ
የግሌ ስትሆኝ እኔም የአንች ብቻ
በውስጣችን እንከን ሳይኖረን ጥላቻ
ከውሸት ከቅናት ልባችን ከፀዳ
ያልከሽን ከሰማሽ ልብሽ ከተረዳ
ያልሽን እሽ ካልኩ እኔም ካልተቆጣሁ
ከሰው ያሉሽ ወሬ ሰምቼ ካልመጣሁ
በፍቅር አለም ውስጥ መንፈሴ ታድሶ
መንፈስሽ ታድሶ
እውነተኛ ፍቅር በልባችን ነግሶ
የነገ ተስፋችን ዛሬ ተደግሶ
አብሮን ሲዘልቅ ነው እስከ እድሜ ፍፃሜ
ፍቅር ብሎ ማለት እንድህ ነው አለሜ